ወርሀዊ የጓደኛ መልእክቶች፣ የካቲት 2022 (እ.አ.አ
አብርሐም እና ሣራ
ወርሃዊ የጓደኛ መልእክቶች፣ የካቲት 2022 (እ.አ.አ)
አብርሐም እና ሣራ
አብርሐም ነቢይ ነበር። እግዚአብሔር ከአብርሐም እና ከሚስቱ ሣራ ጋር ቃል ኪዳን ገባ።
እግዚአብሔር እንደሚባርካቸው ቃል ገባ ልጆች እንደሚወልዱ ነገራቸው። አብርሃም እና ሣራ እግዚአብሔርን እንደሚከተሉ ቃል ገቡ።
አብርሐም እና ሣራ ቃል ኪዳናቸውን አከበሩ። ነገር ግን ለረጅም ጊዜ ምንም ልጆች አልነበራቸውም። በእድሜ እየገፉ ሄዱ።
በመጨረሻም፣ በአብርሐም 100 አምቱ እና በሣራ 90 አመቷ ላይ፣ ወንድ ልጅ ወለዱ። ስሙንም ይስሀቅ ብለው ሰየሙት። እግዚአብሔር እንደባረካቸው አውቀው ነበር።
እኔ እግዚአብሔርን አምናለሁ። አንዳንዴ በረከቶች ወዲያውኑ አይመጡም። ነገር ግን ጌታ ሁል ጊዜ ቃል ኪዳኖቹን ይጠብቃል።
© 2022 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. Printed in USA. እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Friend Message, January 2022 ትርጉም። Amharic። 18313 506