“ጆሴፍ ለከባድ ጊዜያት ተዘጋጀ፣” ወርሀዊ የ ጓደኛ መልእክቶች፣ የካቲት 2022 (እ.አ.አ)
“ጆሴፍ ለከባድ ጊዜያት ተዘጋጀ”
ወርኃዊ የ ጓደኛ መልእክት፣ መጋቢት 2022 (እ.አ.አ)
ጆሴፍ ለከባድ ጊዜያት ተዘጋጀ
ጆሴፍ ነብይ ነበረ። በግብፅ ውስጥ ይኖር ነበር። የግብፁ ንጉሥ ፈርኦን በአንድ ምሽት የተለየ ህልም አለመ። የህልሙን ትርጉም ጆሴፍን ጠየቀው።
እግዚአብሔር ህልሙን እንዲገነዘብ ጆሴፍን እረዳው። ለሰባት ዓመታት፣ ህዝቦች ብዙ ምግብ ይኖራቸዋል። ከዛ ለሰባት ዓመታት፣ በቂ ምግብ አይኖራቸውም። ጆሴፍ ለፈርኦን ነገረው።
አሁን ምግብ ማጠራቀም እንዳለባቸው ጆሴፍ ተናገረ። ከዛ ለከባድ ጊዜያት ዝግጁ ይሆናሉ። ፈርኦን ለጆሴፍ ምግብን እንዲያጠራቅም ሃላፊነት ሰጠ። ጆሴፍ ጠንክሮ ሰራ።
የሰባት አመቱ ረሃብ ሲመጣ፣ ህዝቦቹ የሚመገቡት በቂ ምግብ ነበራቸው። ለሌሎች የሚያካፍሉት እንኳን በቂ ምግብ ነበራቸው።
አሁን መዘጋጀት እችላለው። ከእግዚአብሔር እርዳታ ጋር፣ ከባድ ጊዜያትን ማለፍ እችላለው።
© 2022 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Friend Message, March 2022 ትርጉም። Amharic። 18296 506