2022 (እ.አ.አ)
ሙሴና መና
ሚያዝያ 2022 (እ.አ.አ)


”ሙሴና መና፣“ ወርሃዊ የጓደኛ መልእክቶች፣ ሚያዝያ 2022 (እ.አ.አ)

“ሙሴና መና”

ወርሃዊ የጓደኛ መልእክቶች፣ ሚያዝያ 2022 (እ.አ.አ)

ሙሴና መና

ሙሴና የእስራኤል ልጆች

ሥዕል በኤፕርል ስቶት

ሙሴ ነቢይ ነበር። የእግዚአብሔርን ሕዝብ ወደ ቃል ኪዳን ምድር መራ። ለብዙ ቀናት ተጓዙ።

መና ከልጆች ጋር

ሰዎቹ ተርበው ነበር። ምግብ አልነበራቸውም። እግዚአብሔርም ምግብን ከሰማይ ላከላቸው። ይህም መና ይባል ነበር።

ልጅ እና እናት መና ሲያዘጋጁ

በየማለዳው፣ ሰዎቹ ለመብላት መና ይሰበስቡ ነበር። ግን በሌሊት ትኩስ አይሆንም። በማግስቱ ተጨማሪ መሰብሰብ ነበረባቸው።

ኢየሱስ ክርስቶስ ከልጆች ጋር

መና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድናስታውስ ያደርጋል። እግዚአብሔር ሕዝቡን ለማዳን መና ላከ። እኛን ለማዳን ኢየሱስንም ወደ ምድር ላከው። በየቀኑ ምግብ እንደሚያስፈልገን ኢየሱስን በየቀኑ እንፈልጋለን።

ህጻናት የኢየሱስ ክርስቶስን ምስል እየተመለከቱ

ኢየሱስን እከተላለሁ። እርሱ ብርታት ይሰጠኛል እናም በየቀኑ ፍቅሩን እንድሰማ ይረዳኛል።

የሚቀባ ገፅ

ኢየሱስን በየቀኑ እንፈልጋለን

ኢየሱስ ክርስቶስ ከልጆች ጋር

ለማውረድ ስዕሉ ላይ ጠቅ ያድርጉ።

ሥዕል በኤፕርል ስቶት

ኢየሱስ እንዴት ይረዳሃል?