2023 (እ.አ.አ)
ኢየሱስ ማዕበሉን ጸጥ አደረገ
መጋቢት 2023 (እ.አ.አ)


“ኢየሱስ ማዕበሉን ጸጥ አደረገ፣” ጓደኛ፣ መጋቢት 2023 (እ.አ.አ)፣ 46–47።

ወርኃዊ የጓደኛ መልእክት፣ መጋቢት 2023 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ ማዕበሉን ጸጥ አደረገ

ደቀ መዛሙርቱ ባህሩን በመመልከት ላይ እያሉ ኢየሱስ በመርከቡ ውስጥ ተኝቶ

ሥዕል በኤፕርል ስቶት

አንድ ምሽት ኢየሱስ ክርስቶሰና ደቀመዛሙርቱ ባህሩን በጀልባ ይሻገሩ ነበር። ኢየሱስ ደክሞት ሰለነበር አንቀላፋ።

ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ የነበሩበትን ጀልባ ማዕበል ሲያወዛውዘው

አውሎ ንፋስ መጣ። ማዕበሎቹ እየበዙ ሄዱ! ደቀመዛሙርቱ ፈርተው ነበር፡፡ ኢየሱስን ቀሰቀሱትና ማዕበሉን ጸጥ እንዲያደርግ ጠየቁት

ኢየሱስ ማዕበሉን ጸጥ ሲያደርግ

ኢየሱስ ቆመ እና እንዲህ አለ፣ “ዝም በል፥ ጸጥ በል።” ንፋሱ ቆመ። ባህሩም ተረጋጋ።

ትንሽ ልጅ እጆቹን አጥፎ አይኖቹን ሲጨፍን

በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለኝ እምነት ሰላም ሊያመጣልኝ ይችላል። በምፈራበት ጊዜ፣ ኢየሱስ መረጋጋት እንዲሰማኝ ሊረዳኝ ይችላል።

የሚቀባ ገፅ

ስለኢየሱስ መማር እወዳለሁ

ስለኢየሱስ የሚተርክ መፅሀፍን የምትመለከት ህጻን ሴት ልጅን የሚያሳይ የሚቀባ ገፅ

ስዕል በፓትሻ ጋይስ

ስለ ኢየሱስ ምን ታውቃላችሁ?