“የመጀመሪያው ቅዱስ ቁርባን፣ ”ጓደኛ፣ ሰኔ 2023 ፣ (እ.አ.አ) 46–47።
ወርሃዊ የጓደኛ መልዕክቶች፣ ሰኔ 2023 (እ.አ.አ)
የቅዱሳት መጻሕፍት ታሪኮች
የመጀመሪያው ቅዱስ ቁርባን
ከመሞቱ በፊት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐዋርያቱ ጋር ተገናኘ። የክህነት ስልጣንንም ሰጣቸው።
ኢየሱስ ዳቦውን ቆረሰና ሰጣቸው። ህይወቱን ለእነርሱ አሳልፎ እንደሰጠ ለማስታወስ እንዲረዳቸው እንዲበሉት ጠየቃቸው።
ከዚያም ኢየሱስ ጽዋውን ሰጣቸው፡፡ ከእርሱ እንዲጠጡም ጠየቃቸው፡፡ እርሱን እንዲያስታውሱ ይረዳቸዋል።
ኢየሱስ ከሐዋሪያቶቹ ጋር በማይኖርበት ጊዜ እንኳን፣ ቅዱስ ቁርባኑ እርሱን እንዲያስታውሱ ረዳቸው። ፍቅሩ ተሰምቷቸዋል እንዲሁም ትእዛዛቱን መጠበቅን ማስታወስ ችለዋል።
© 2023 Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved። በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። ወርሃዊ የጓደኛ መልእክቶች፣ ሰኔ 2023 (እ.አ.አ) ትርጉም። Language. 19026 000