“ኢየሱስ መንገዱን አሳይቶናል፣” ጓደኛ፣ ነሐሴ 2023 (እ.አ.አ)፣ 4–5.።
ወርሃዊ የጓደኛ መልእክት፣ ነሐሴ 2023 (እ.አ.አ)
ኢየሱስ መንገዱን አሳይቶናል።
ኢየሱስ ክርስቶስ የሰማይ አባት ልጅ ነው። አንድ ቀን ወደ ሰማይ አባት እንዴት እንደምንመለስ ሊያሳየን ወደ ምድር መጣ። ኢየሱስ ተጠምቆ ነበር። እኛም መጠመቅ እንደሚገባን አስተምሯል።
ኢየሱስ እንዴት እንደምንኖር አስተምሮናል። ሁላችንንም ወዶናል እንዲሁም ረድቶናል። እንድንከተለው ይፈልጋል።
ኢየሱስ ሕመማችን ሁሉ ተሰምቶታል እንዲሁም ስለሐጢያቶቻችን ተሰቃይቷል። ከዚያም ለእኛ ሲል ሞተ፡፡ ይህም የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ይባላል። ከሞት ተነሥቷል። ያ ማለት አሁንም በህይወት ይኖራል ማለት ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ከሞትን በኋላ እንደገና በህይወት እንኖራለን።
ኢየሱስ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ያደረገው ስለሚወደን ነው። በእርሱ ምክንያት አንድ ቀን ከሰማይ አባታችን እና ከቤተሰቦቻችን ጋር መኖር እንችላለን።
በመጠመቅ ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል እንችላለን። ሌሎችን በመውደድ እና በመርዳት እንዲሁም ትዕዛዛቱን በመጠበቅ በየቀኑ ልንከተለው እንችላለን።
© 2023 (እ.አ.አ) በ Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved። በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Friend Message, July 2023 (እ.አ.አ) ትርጉም። Language. 19046 506