“የጣቢታ ተአምር፣” ጓደኛ፣ መስከረም 2023 (እ.አ.አ)፣ 46–47።
ወርሃዊ የጓደኛ መልእክት፣ መስከረም 2023 (እ.አ.አ)
የጣቢታ ተአምር
ጣቢታ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ ነበረች። ልብስና ካፖርት ሰፍታ ለሌሎች ብዙ መልካም ነገሮችን ታደርግ ነበር።
ነገር ግን ጣቢታ ታማ ሞተች። ብዙ ሰዎች አዝነው ነበር።
ነቢዩ ጴጥሮስ ወደ ጣቢታ ሄደ። ኢየሱስ ክርስቶስ በሰጠው ኃይል እርሷን ከሞት አስነሳት።
ጣቢታ እንደገና በህይወት ኖረች! እሷም እንደገና መስፋት እና ማገልገል ትችል ነበር። ይህም ተአምር ነበር።
© በ2023 (እ.አ.አ) Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Friend Message, September 2023 ትርጉም። Language. 19047 506