“የሕይወት ዛፍይወት ዛፍ ፣ ጓደኛ ፣ ” ጥር 2024(እ.አ.አ)፣ 26_27።
ወርሃዊ የጓደኛ መልእክቶች፣ ጥር 2024 (እ.አ.አ)
የሕይወት ዛፍ
ሌሂ ነቢይ ነበር። እግዚሐብሔር፣ ቤተሰቦቹን ወደቃልኪዳኗ ምድር እንዲወስድ ነገረው። በሚጓዙበት ጊዜም ስለ አንድ መልካም ዛፍ ህልም አይቶ ነበር። የሕይወት ዛፍ ይባል ነበር።
ዛፉም ጣፋጭ ነጭ ፍሬ አፈራ። ሌሂ ከእርሱ በበላ ጊዜ ደስታ ተሰማው። ቤተሰቦቹም እንዲሞክሩት ፈለገ።
ሌሂ ወደ ዛፉ የሚመራውን የብረት በትርም አይቶ ነበር። ሰዎቹም ወደ ዛፉ ለመሄድ እና ፍሬውን ለመብላት በትሩን ያዙ።
በሌሂ ህልም ውስጥ የነበረው የሕይወት ዛፍ የእግዚሐብሔር ፍቅር ነው። በትሩም ቅዱሳት መፃሕፍት ናቸው። ቅዱሳት መጽሃፍትን ስናነብ ወደ ሰማይ አባታችን እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንቀርባለን።
© 2024 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Friend Message, January 2024 ትርጉም። Language. 19273 506