“ያዕቆብ እና ኔፊ ኢየሱስን አዩ፣” ጓደኛ፣ መጋቢት 2024 (እ.አ.አ)፣ 26–27።
ወርኃዊ የጓደኛ መልእክት፣ መጋቢት 2024 (እ.አ.አ)
ያዕቆብ እና ኔፊ ኢየሱስን አዩ
ያዕቆብ የኔፊ ታናሽ ወንድም ነበር። የተወለደው ቤተሰባቸው ከኢየሩሳሌም ከወጡ በኋላ ነበር። ያዕቆብ በልጅነቱ ወደ ቃል ኪዳኑ ምድር መጣ።
ሁለቱም ያዕቆብ እና ኔፊ ኢየሱስን አዩ። ስለ ኢየሱስ እንዲያውቁ ለመርዳት ምስክርነታቸውን ለቤተሰቦቻቸው አካፈሉ።
የነቢዩ የኢሳይያስን ቃላትም አካፍለዋል። ኢሳይያስም ኢየሱስን አይቶ ነበር እንዲሁም ስለ እርሱ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ጽፏል። ያዕቆብ እና ኔፊ ቤተሰቦቻቸውን ስለ ኢየሱስ ለማስተማር የኢሳይያስን ቃላት ከቅዱሳት መጻህፍት ተጠቅመዋል።
ኢየሱስ ወደምድር እንደሚመጣ አስተምረዋል። ይሞታልም በድጋሚም በሕይወት ይኖራል። ቤተሰቦቻቸው የእርሱን መምጣት በጉጉት እንዲጠብቁ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነታቸውን አካፍለዋቸዋል።
© 2024 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። የ Monthly Friend Message, March 2024 ትርጉም። Amharic. 19287 506