ጓደኛ
ጸሎት ምንድን ነው?
ሚያዝያ 2024 (እ.አ.አ)


“ጸሎት ምንድን ነው?” ጓደኛ ሚያዝያ 2024 (እ.አ.አ)

ወርሃዊ የጓደኛ መልእክት፣ ሚያዝያ 2024 (እ.አ.አ)

ጸሎት ምንድን ነው?

አንዲት ሴት ልጅ አልጋ አጠገብ እየጸለየች

ሥዕል በኤፕርል ስቶት

ጸሎት ከሰማይ አባት ጋር የምንነጋገርበት መንገድ ነው።

ወንድ ልጅ በመጫወቻ ሜዳ ላይ እየጸለየ

በማንኛውም ሰዓት፣ በየትኛውም ቦታ መጸለይ እንችላለን። የሰማይ አባት ሁልጊዜም ይሰማናል።

ወንድ ልጅ በመጀመሪያ ክፍል እየጸለየ

ስንጸልይ ፍቅርንና አክብሮትን የሚያሳዩ ቃላትን እንጠቀማለን።

ወንድ ልጅ ከቤተሰቡ ጋር እየጸለየ

የሰማይ አባትን ስለበረከቶቻችን እናመሰግነዋለን። እንዲሁም እርሱ እንዲረዳን ልንጠይቀው እንችላለን።

አንዲት ልጅ አልጋ ላይ እየጸለየች

በጸለይኩ ቁጥር የሰማይ አባት ፍቅር ይሰማኛል!

የሚቀባ ገፅ

ለሰማይ አባት ለመጸለይ እችላለሁ

alt text here

ሥዕል በአደም ኮፎርድ

ስለ ምን ትጸልያላችሁ?