“እግዚአብሔር አልማን እና አሙሌቅን ነፃ አወጣቸው፣” ጓደኛ፣ ሰኔ 2024 (እ.አ.አ)፣ 26-27።
ወርሃዊ የጓደኛ መልእክት፣ ሰኔ 2024 (እ.አ.አ)
እግዚአብሔር አልማን እና አሙሌቅን ነፃ አወጣቸው
አልማ እና አሙሌቅ አሞኒሀ ወደምትባል ከተማ ሄዱ። ሠዎችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አስተማሩ። ነገር ግን ሰዎቹ ስላስተማሩት ነገር ተናደው ነበር። አልማን እና አሙሌቅን አሠሯቸው።
ሰዎቹ በአልማ እና በአሙሌቅ ላይ ጉዳት አደረሱ። ለብዙ ቀናት እስር ቤት ውስጥ ነበሩ።
አልማ እና አሙሌቅ ጸለዩ እና ጥንካሬን ለማግኘትም ጠየቁ። በእግዚአብሔር እምነት ነበራቸው። እጃቸው የታሠረበትን ገመድ እንዲበጥሱ ሃይል ሰጣቸው።
ከዚያም ምድር ተንቀጠቀጠ። የእስር ቤቱ ግድግዳዎች ፈረሱ! እግዚአብሔር አልማን እና አሙሌቅ ነጻ በማውጣት ረዳ። ሌሎች ሰዎችን ስለኢየሱስ ክርስቶስ ለማሥተማር ከአሞኒሃ ወጥተውሄዱ።
© 2024 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። የMonthly Friend Message, June 2024 ትርጉም። Amharic. 19289 506