“አሮን ንጉሱን አስተማረ፣” ጓደኛ፣ ሐምሌ 2024 (እ.አ.አ) 26-27።
ወርሃዊ የ ጓደኛ መልእክት፣ ሐምሌ 2024 (እ.አ.አ)
አሮን ንጉሱን አስተማረ
አሮን ከሞዛያ ወንድ ልጆች አንዱ ነበር። እሱ ሚስዮናዊ ነበር። በምድሪቱ ሁሉ ላይ የላማናውያንን ንጉሥ አስተማረ።
አሮን በእግዚአብሔር ያምን እንደሆነ ንጉሱን ጠየቀው። አሮን እግዚአብሔር እውን እንደሆነ ከነገረው፣ንጉሱ እንደሚያምን ተናገረ። ስለ እግዚአብሔር የበለጠ እንዲነግረው አሮንን ጠየቀው።
አሮን ለንጉሱ ቅዱሣት መፃህፍትን አነበበለት። ስለ ምድር አፈጣጠር አስተማረ። ስለ እግዚአብሄር እቅድ አስተማረ። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ለንጉሱ ነገረው።
ከዚያም በኋላ፣ ንጉሱ ጸለየ። አሮን ያለው እውነት እንደሆነ እግዚአብሔርን ጠየቀው። እውነት እንደሆነም ንጉሱ መልስ ተቀበለ።
ንጉሡ አሮን ያስተማረውን አመነ። በቤተሰቡ ውስጥ ያሉትም ሁሉ አመኑ። ተጠመቁ እና ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል መረጡ።
© 2024 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Friend Message, July 2024. ትርጉም። Amharic. 19348 506