“ብላቴናዎቹ ተዋጊዎች፣” ጓደኛ፣ ነሐሴ 2024 (እ.አ.አ)፣ 26–27።
ወርሀዊ የጓደኛ መልእክት፣ ነሐሴ 2024 (እ.አ.አ)
ብላቴናዎቹ ተዋጊዎች
ስዕል በአንድሩ ቦዝሊ
አሞን እና ወንድሞቹ ያስተሟሯቸው ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ፈለጉ። መሳሪያቸውን ቀበሩ እና እንደገና እንደማይዋጉ ለእግዚአብሔር ቃል ገቡ፡፡
ነገር ግን ወድያውኑ ቤተሰባቸውን ለመጠበቅ ፈለጉ። መሳሪያቸውን የቀበሩት አባቶች ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸውን ቃል ኪዳን ለመስበር አልፈለጉም። ስለሆነም ልጆቻቸው በእነሱ ምትክ ለመዋጋት ተዘጋጁ። እነሱ ሁለት ሺህ ብላቴናዎቹ ተዋጊዎች ተብለው ይጠሩ ነበር። ብላቴና ማለት “ወጣት” ማለት ነው።
ብላቴናዎቹ ተዋጊዎች በውጊያ ውስጥ ተፋልመው አያውቁም ነበረ። ነገር ግን እናቶቻቸው እንዲዘጋጁ አገዟቸው እናም እግዚአብሔርን እንዲያምኑ አስተማሯቸው።
ሄልማን መሪያቸው እንዲሆን መረጡ። ደፋር ነበሩ እናም እግዚአብሔር ረዳቸው። ሁሉም ተጎድተው ነበር፣ ነገር ግን እርስ በእርስ ተጋገዙ። እግዚአብሔር እምነታቸውን አከበረ እና ሁሉም በህይወት ኖሩ።
የሚቀባ ገፅ
ቅዱሳት መጻህፍት በየቀኑ ሊረዱኝ ይችላሉ
ሥዕል በአደም ኮፎርድ
የትኛውን የቅዱሳት መጻህፍት ታሪክ በጣም ትወዳላችሁ?
© 2024 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Friend Message, July 2024 (እ.አ.አ) ትርጉም። Amharic. 19290 506