“የማያቋርጥ ራዕይ፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ መጋቢት 2021 (እ.አ.አ)፣ 16
ወርኃዊ ለወጣቶች ጥንካሬ መልእክት፣ መጋቢት 2021 (እ.አ.አ)
የማያቋርጥ ራዕይ
ከሚያዝያ 2020 (እ.አ.አ) የአጠቃላይ ጉባዔ ንግግር።
ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በተከታታይ ራዕይ ተቀበለ። ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተቀበላቸው ብዙ ራእዮች በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ ተጠብቀዋል።
በተጨማሪም፣ የጌታ “ወኪል አገልጋዮች በሆኑ፣ ስለ እርሱ እንዲናገሩ ሥልጣን ከተሰጣቸው ሕያው ነቢያት የማያቋርጥ ራዕይን በማግኘት ተባርከናል።”1
የግል መገለጥ በተጨማሪ በትህትና ከጌታ መመሪያን ለማግኘት ለሚሹ ሁሉ የሚገኝ ይሆናል። የትንቢታዊ መገለጥን ያህል አስፈላጊ ነው።
የግል መገለጥ የተመሠረተው ከመንፈስ ቅዱስ በሚመጡ መንፈሳዊ እውነቶች ነው። መንፈስ ቅዱስ የእውነቶች ሁሉ ገላጭ እና መስካሪ ነው፤ በተለይ የአዳኛችን የኢየሱስ። ያለመንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ መሆኑን በትክክል ልናውቅ አንችልም ነበር። የእሱ ወሳኝ ሚና ስለ አባት እና ስለልጁ እንዲሁም ስለማእረጋቸው እና ክብራቸው መመስከር ነው።
በጌታ የወይን እርሻ በትህትና ስንሠራ እያንዳንዳችን ገላጭ ምሪትን ልንቀበል እንደምንችል አረጋግጥላችኋለሁ።
የእኔ ትሁት ልመና እያንዳንዳችን ህይወታችንን ለመምራት የማያቋርጥ ራዕይን እንድንፈልግ እንዲሁም እግዚአብሔርን እና አዳኛችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ስናመልክ መንፈሱን እንድንከተል ነው።
© 2021 በ Intellectual Reserve, Inc. መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው። በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly For the Strength of Youth Message, March 2021 ትርጉም። Amharic. 17466 506