2022 (እ.አ.አ)
እርሱን እንዴት ነው የምትሰሙት?
መጋቢት 2022 (እ.አ.አ)


“እርሱን እንዴት ነው የምትሰሙት?፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ መጋቢት 2022 (እ.አ.አ)

ወርኃዊ ለወጣቶች ጥንካሬ መልእክት፣ መጋቢት 2022 (እ.አ.አ)

እርሱን እንዴት ነው የምትሰሙት?

የሚያዝያ 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ ንግግር

የእንቆቅልሽ ቁርጥራጮች
ህዝቦች የጎደለ የእንቆቅልሽ ቁራጭ ቅርፆችን ይዘው

ማብራሪያ በኦክሳና ግሪቪና

ከመንፈስ ቅዱስ ከምንቀበለው ሰላማዊ አቅጣጫ ጎን ለጎን፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እግዚአብሔር በኃይል እና በጣም ግላዊ በሆነ መልኩ እያንዳንዳችንን እንደሚያውቀን እና እንደሚወደን ያረጋግጥልናል። ከዛ በከባድ ጊዜያችን ውስጥ አዳኙ እነዚህን ልምዶች ወደ አእምሮአችን ያመጣል።

ስለ እራሳችሁ ህይወት አስቡ። እነዚህ ልምዶች በሕይወታችን ውስጥ ጠቃሚ በሆኑ ጊዜያት ወይም በመጀመሪያ ባዶ በሚመስሉ ክስተቶች ላይ ሊመጡ ይችላሉ። እነዚህ መንፈሳዊ ትርጉም የሚሰጡ ሰዓቶች በተለያዩ ጊዜያት እና በተለያዩ መንገዶች ግላዊ በሆነ መልኩ ለእያንዳንዳችን ይመጣሉ።

አንዳንድ ጊዜ “ድንገተኛ ሃሳብን” እና አልፎ አልፎ ንፅሁ የጥበብ ፍሰትን እንደምንቀበል ጆሴፍ ስሚዝ ገለፀ።1

ፕሬዝዳንት ዳለን ኤች ኦክስ እንደዚህ አይነት ልምድ መቼም አጋጥሞት እንደማያውቅ ለገለፀ ለአንድ ትሁት ሰው ምላሽ ሲሰጡ እንዲህ መከሩ፣ “ምናልባት የአንተ ፀሎቶች በተደጋጋሚ ተመልሰው ይሆናል ነገር ግን ግምትህን በታላቅ ምልክት ወይም በከፍተኛ ድምፅ ላይ በማድረግህ ምክንያት ያልተመለሰልህ ሊመስልህ ይችላል።”2

በቅርቡ ፕሬዝዳንት ረስል ኤም ኔልሰን እንዲህ ሲሉ ሰማን፦ “በጥልቅ እና አዘውትራችሁ ስለዚህ ጥያቄ እንድታስቡ እጋብዛችኋለሁ፦ እንዴት ነው እናንተ እርሱን መስማት የምትችሉት? እንዲሁም በተሻለ ሁኔታ እና በተደጋጋሚ እርሱን ለመስማት ደረጃዎችን እንድትወስዱ እኔ እጋብዛችኋለሁ።”3

ማስታወሻዎች

  1. የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንቶች ትምህርቶች፦ ጆሴፍ ስሚዝ (2007) (እ.አ.አ)፣ 132።

  2. ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “Life’s Lessons Learned: Personal Reflections [የተማሩት የህይወት ትምህርቶች፦ ግላዊ ነጸብራቆች]፣” 2011 (እ.አ.አ)፣ 116።

  3. ረስል ኤም ኔልሰን፣ “‘እርሱን እንዴት ነው የምትሰሙት?’ ልዩ ግብዣ፣” የካቲት 26፣ 2020 (እ.አ.አ)፣ blog.ChurchofJesusChrist.org.