“ለእግሮቻችን መብራት፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ነሐሴ 2022 (እ.አ.አ)።
ወርሀዊ የ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ነሐሴ 2022(እ.አ.አ)
ለእግሮቻችን መብራት
በጥንት እስራኤላዊያን የተለመደ ቁስ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚመራን ሊያስተምረን ይችላል።
እውነታዎች
በብሉይ ኪዳን ጊዜያት፣ ሰዎች በጨለማ ውስጥ ሲሆኑ ብርሃን ለማግኘት የዘይት መብራትን ይጠቀሙ ነበር። አብዛኞቹ እነዚህ መብራቶች 3 መሰረታዊ ገጽታዎች ነበሯቸው፤
-
በአብዛኛው፣ ትንሽ ከሰው እጅ መዳፍ የማይበልጥ የወይራ ዘይት ለመያዝ የሚያገለግል የሸክላ ጎድጓዳ ሰሃን
-
ዘይቱን ከመጠጠ በኋላ የሚለኮስ የተልባ እግር
-
የተልባ እግሩን ቀና አድርጎ ለመያዝ የሚያገለግል አፈሙዝ ወይም አፍንጫ
አንድ ብቻ የተልባ እግር ያላቸው ቀላል የዘይት መብራቶች በዙሪያቸው ለጥቂት ጫማ ያህል ብቻ ብርሃን ይሰጣሉ። በእግር ስትጓዙ ከተጠቀማችሁባቸው፣ በጨለማ ውስጥ በጥንቃቄ ለመሄድ እንድትችሉ ከፊታችሁ አንድ እርምጃ ያህል ብቻ ለማየት በቂ ብርሃን ይሰጣሉ።
መማር የምንችለው ነገር
የጌታ ቃል በአለም ላይ በዙሪያችን ባለው ጨለማ እና ግራ መጋባት መንገዳችንን ሊያበራልን ይችላል።
ጌታ ብርሃናችንን እንዳንሸፍን ነገር ግን ሌሎች እንዲያዩት የወንጌልን ብርሃን እንድንይዝ ጠይቆናል ( ማቴዎስ 5፤14–16 ተመልከቱ)።
መብራቶቻችን በዘይት መሞላታቸውን ማረጋገጥ የእኛ ሃላፊነት ነው (ማቴዎስ 25:1-13 ተመልከቱ)። ይህን የምናደርገው በመጸለይ፣ ቅዱሳን መጻህፍትን በማጥናት፣ አገልግሎት በመስጠት፣ ነብዩን በመከተል፣ እና ሌሎች የእምነት እና የአምልኮ ተግባራትን በመፈጸም ነው (ስፔንሰር ደብሊው. ኪምቦል፣ እምነት ተአምሩን ይቀድማል [1972 (እ.አ.አ.)]፣ 256)።
እምነትን ከተለማመድን፣ ጌታ አንዳንዴ አንድ ተጨማሪ እርምጃ ወደፊት ለመራመድ በሚበቃ ብርሃን መንገዳችንን ያበራልናል (ቦይድ ኬ. ፓከር፣ “የጌታ ሻማ፣” ኤንዛይን፣ ጥር 1983 እ.አ.አ፣ 54)።
© 2022 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly For the Strength of Youth Message, August 2022 (እ.አ.አ)ትርጉም። Amharic። 18316 506