2018 (እ.አ.አ)
የንስሀ ስጦታ
ጥር 2018 (እ.አ.አ)


የቀዳሚ አመራር መልዕክት፣ ጥር 2018 (እ.አ.አ)

የንስሀ ስጦታ

“ሀላፊነታችን በመለስተኛ አቋም ላይ ያሉትን ወደ ብቁነት፣ ከውድቀት ወደ ውጤተኛነት ከፍ ለማድረግ ነው፣” ብለው ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን አስተምረዋል። “ስራችንም እኛ ከምንችለው በላይ የተሻልን ለመሆን ነው። እግዚአብሔር ከሰጠን ስጦታዎች ሁሉ ታላቅ ከሆኑት አንዱ እንደገና በመጣር መደሰት ነው፣ ምንም ውድቀት የመጨረሻ መሆን የለበትምና።”1

የአዲስ አመት ምፅዓትን ከውሳኔ እና ከአላማዎች እናገናኛለን። ለመሻሻል፣ ለመቀየር፣ እና እንደገና ለመጣርም እንወስናለን። ምናልባት እንደገና ለመጣር የምንችልበት አስፈላጊ መንገድም ፕሬዘደንት ሞንሰን “የንስሀ ስጦታ” ብለው የሚጠሩትን በማቀፍ ነው።2

የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንት ከሆኑ በኋላ ካሏቸው በተመረጡት በሚቀጥሉት ምንባብ ውስጥ፣ ፕሬዘደንት ሞንሰን “ለኃጢያቶቻችን ስርየት ለማግኘት፣ እና ልባችን ይነጹ ዘንድ፣ የክርስቶስን የኃጢያት ክፍያ ደም እንድንጠቀም” መክረውናል።3

የምህረት ታዕምራት

“ህላችንም ትክክል ያልሆኑ ምርጫዎችን አድርገናል፡ እንደዚህ አይነት ምርጫዎችን ያላስተካከልን ከሆንን፣ ይህን ለማድረግ የሚቻልበት መንገድ እንዳለ አረጋግጥላችኋለሁ። ሂደቱ ንስሃ ይባላል። ስህተታችሁን እንድታስተካክሉ እለምናችኋለሁ። አዳኛችን ለእናንተ እና ለእኔ ያንን የተባረከ ስጦታ ሊሰጠን ሞተ። መንገዱ ቀላል ባይሆንም፣ የተስፋ ቃሉ እውነት ነው፥ ‘ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች’ [ኢሳይያስ 1፥18]። ‘እናም እኔ፣ ጌታ፣ በምንም አላስታውሳቸውም’ [ት. እና ቃ. 58፥42]። የዘለአለም ህይወታችሁን በአደጋ ላይ አትጣሉ። ኃጢያት ከሰራችሁ፣ የምትመለሱበትን ወዲያው ከጀመራችሁ፣ ጣፋጯን ሰላም እና ከምህረት ታዕምራት ጋር የምትመጣውን ደስታ ወዲያው ታገኛላችሁና።”4

ወደ መንገዱ ተመለሱ

“ምንም እንኳን በብልኃት መምረጣችን አስፈላጊ ቢሆንም፣ የሞኝ ምርጫዎችን የምናደርግበት ጊዜዎች አሉ። በአዳኙ የተሰጠ የንስሃ ስጦታ ወደምንሻው የሰለስቲያል የክብር ደረጃ ወደሚያመራው መንገድ መመልስ እንድንችል የመንገድ ድባባችንን ለማስተካከል ያስችለናል።”5

የመመለሻው መንገድ

“ማናችሁም በመንገዳችሁ የተደናቀፋችሁ ብትሆኑም፣ መመለሻ መንገድ እንዳለ አረጋግጥላችኋለሁ። ሂደቱ ንስሃ ይባላል። ምንም እንኳን መንገዱ ከባድ ቢሆንም፣ የዘላለም መዳናችሁ በእሱ ላይ የተመረኮዘ ነው። ከዚህ በላይ ለጥረታችሁ ብቁ ለመሆን የሚችል ምን አለ? በሙሉ ንስሃ ለመግባት የሚያስፈልጉትን ደረጃዎች ለመውሰድ እዚህና አሁን እንድትወስኑ እማጸናችኋለሁ። ይህንን ቶሎ ባደረጋችሁ ጊዜ ኢሳይያስ የተናገረውን ሰላም፣ ጸጥታና መታመን ቶሎ ትለማመዳላችሁ [ ኢሳይያስ 1፥18ተመልከቱ]።”6

ሰዎች ለመለወጥ ይችላሉ

“ሰዎች መለወጥ እንደሚችሉ በአእምሮአችን ማሰብ ይኖርብናል። መጥፎ ልምዶችን መተው ይችላሉ። ከመተላለፎች ንሰሀ መግባት ይችላሉ። የክህነት ስልጣንን በብቁነት መሸከም ይችላሉ። እናም ጌታን በትጋት ማገልገል ይችላሉ።”7

እንደገና ንጹህ መሆን

“በህይወታችሁ የተሳሳተ ምንም ነገር ቢኖር፣ እናንተ የምትወጡበት የተከፈተ መንገድ አላችሁ። ምንም ጻድቅ ያለሆነውን አቁሙ። ከኤጲስ ቆጶሳችሁ ጋር ተነጋገሩ። ችግሩ ምንም ቢሆን፣ በትክክለኛ ንስሀ በኩል ለመስተካከል ይችላል። እንደገና ንጹህ ለመሆን ትችላላችሁ፡”8

የአዳኝ አስፈላጊ ሚና

“ለ[ደህንነት] እቅድ ወሳኝ ክፍል የሆነው አዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ያለ እርሱ የኃጢያት ክፍያ፣ ሁሉም ነገር ጠፊ ነበር። በእርሱ እና በተልእኮው ማመን ብቻ ግን በቂ አይደለም። መስራት እና መማር፣ መሻት እና መፀለይ፣ ንሰሀ መግባት እና መሻሻል አለብን። የእግዚአብሔርን ህግጋት ማወቅ እና መኖር አለብን። የእርሱን አዳኝ ስርአቶች መቀበል አለብን። ይህንን በማድረግ ብቻ እውነተኛ፣ ዘለአለማዊ ደስታን እናገኛለን።”9

ማስታወሻዎች

  1. “The Will Within፣” Ensign፣ ግንቦት 1987 (እ.አ.አ)፣ 68።

  2. “ምርጫዎች” Liahona፣ ሚያዝያ 2016 (እ.አ.አ.)፣ 86።

  3. ሞዛያ 4፥2{32}።

  4. “The Three Rs of Choice፣” Liahona፣ ህዳር 2010 (እ.አ.አ)፣ 69።

  5. “ምርጫዎች፣” 86።

  6. “ትዕዛዛቱን ጠብቁ፣” Liahona፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 85፡፡

  7. “ሌሎችን መሆን አንደሚችሉት እዩዋቸው፣” Liahona፣ ህዳር 2012 (እ.አ.አ)፣ 68።

  8. “የክህነት ሀይል፣” Liahona፣ ግንቦት 2011 (እ.አ.አ)፣ 67።

  9. “ወደ ደስታ የሚያመራው ፍፁሙ መንገድ፣” Liahona፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 80–81።

አትም