2018 (እ.አ.አ)
የሚታወሱ ሶስት ነገሮች
የካቲት 2018 (እ.አ.አ)


ወጣቶች

የሚታወሱ ሶስት ነገሮች

ማስታወስ የሚለው ቃል በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ በብዙ ቁጥር ይገኛሉ። ኔፊ ወንድሞቹ እግዚአብሔር ቅድመ አያቶቻቸውን እንዴት እንዳዳነ እንዲያስታውሱ አበረታታቸው። ንጉስ ቢንያም ህዝቡ የእግዚአብሔርን ታላቅነት እንዲያስታውሱ ጠየቃቸው። እናም ሞሮኒ መሪዎቹ ጌታ እንዴት ምህረተኛ እንደነበር እንዲያስታውሱ መመሪያ ሰጣቸው።

አዳኝን ማስታወስ አስፈላጊ ነው—ቅዱስ ቁርባንን በምንወስድበት ጊዜ ሁሉ እንድናስታውሰው ቃል ኪዳን ገብተናል። ፕሬዘደንት አይሪንግ እነዚህን ሶስት ነገሮች በቅዱስ ቁርባን ጊዜ እንድናስታውስ ጋብዘውናል፥

  1. ኢየሱስ ክርስቶስን አስታውሱ፥ አዳኝ እንዴት እንዳገለገለ እና ለሌሎች ያለውን ፍቅር እንደሚያሳይ በቅዱስ መጻህፍት ውስጥ አንብቡ። ፍቅሩ እንዴት ይሰማችኋል? አዳኝ እንደሚያደርገው ለማገልገል እና ወደሌሎች ፍቅር ማሳየት እንዴት ትችላላችሁ?

  2. ምን የተሻለ ማድረግ እንደሚያስፈልጋችሁ አስታውሱ፥ ስላለፈው ሳምንት ንስሀ በሚገባ ልብ አስተዋሉ። ለመቀየር የምትችሉትን አንድ ነገር ምረጡ፣ እናም ያን ማሻሻያ እንዴት እንደምታደርጉት ጻፉ። እቅዳችሁን ሁልጊዜ ለማየት በምትችሉበት ቦታ አስቀምጡት።

  3. እድገታችሁን አስታውሱ፥ እግዚአብሔር የምታደርጉትን መልካም እድገት ለማየት እንዲረዳችሁ ጠይቁት። ስሜታችሁን መዝግቡ።

ፍጹም አይደለንም፣ ነገር ግን አዳኝ ያን ያውቃል። ለዚህነው እንድናስታውሰው የሚጠይቀን። እርሱን ማስታወስ ተስፋ ይሰጠናል እናም ለመሻሻል እንድንፈልግ ይረዳናል። እርሱን በማናስታውስበት ጊዜም፣ ፕሬዘደንት አይሪንግ እንዲህ ብለዋል፣ “እርሱ ሁልጊዜም ያስታውሳችኋል።”

አትም