2018 (እ.አ.አ)
ሁሌም እርሱን አስታውሱት
የካቲት 2018 (እ.አ.አ)


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ የካቲት 2018 (እ.አ.አ)

ሁሌም እርሱን አስታውሱት

ነቢዩ ሞሮኒ የመፅሐፈ ሞርሞንን የመጨረሻ ቃላት በወርቃማ ሰሌዳዎች ላይ ሲቀርፅ ከእኔ ጋር በአዕምሮዋችሁ ለማየት ትችላላችሁን? ብቻውን ነበር። ሀገሩ፣ ህዝቡ፣ እና ቤተሰቡ ሲወድቁ አይቷል። ምድሩም “በሙሉ የማያቋርጥ” ጦርነት ላይ ነበር (ሞርሞን 8፥8)። ግን ተስፋ ነበረው፣ ቀናችንን አይቷልና! ለመጻፍ ከሚችላቸው ነገሮች ሁሉ፣ እኛ እንድናስታውስ ጋበዘን (መሮኒ 10፥3)።

ፕሬዘደንት ስፔንሰር ደብሊው. ኪምባል [1895–1985 (እ.አ.አ)] ማስታወስ በመዝገብ ቃላት ውስጥ ከሚገኙት ውስጥ በጣም አስፈላጊቃል ነው ብለው ማስተማር ይወዱ ነበር። ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ስለገባን፣ እንዲህ አሉ፣ “ከሁሉም በላይ የሚያስፈልገን ማስታወስ ነው።”1

በቅዱስ መጻህፍት ውስጥ በሙሉ አስታውሱ የሚለውን ቃል ለማግኘት ትችላላችሁ። ኔፊ ወንድሞቹን ሲገስፅ፣ በብዛት የጌታን ቃል እንዲያስታውሱ እና እግዚአብሔር ቅድመ አባቶቻቸው እንዴት እንዳዳነ እንዲያስታውሱ ይጋብዛቸዋል ( 1 ኔፊ 15፥11፣ 25 17፥40)።

ከሁሉም ታላቅ ከነበረው ስብከት ውስጥ፣ ንጉስ ቢንያም አስታውሱ የሚለውን ቃል ለሰባት ጊዜ ተጠቀመበት። ህዝቡ “የእግዚአብሔርን ታላቅነት እናም [ለእነርሱ ያለውን] የእርሱን ጥሩነትና ትዕግስት” ያስታውሱ ዘንድ ተስፋ ነበረውሞዛያ 4፥11ደግሞም 2፥414፥28፣ 305፥11–12 ተመልከቱ)

ጌታ ቅዱስ ቁርባንን ሲመሰርት፣ደቀ መዛሙርቱ የእርሱን መስዋዕት “በማስታወስ” ምልክቱን እንዲወስዱ ጋበዛቸው (ሉቃስ 22፥19)። እኔ እና እናንተ በምናዳምጣቸው እያንዳንዱ የቅዱስ ቁርባን ጸሎቶች ውስጥ፣ሁልጊዜ የሚለው ቃል አስታውሱ ከሚለው ቃል በፊት ይመጣል ( ት. እና ቃ. 20፥77፣ 79)።

መልእክቴም እንድናስታውስ ግብዣ፣ እንዲሁም ልመና ነው። የቅዱስ ቁርባን የተቀደሰ ምልክትን ስትቀበሉ ለማስታውስ የምትችሏቸው ሶስት ሀሳቦች የሚቀጥሉት ናቸው። ለእኔ እንደነበሩ፣ ለእናንተም የሚረዷችሁ እንዲሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ።

ኢየሱስ ክርስቶስን አስታውሱ።

መጀምሪያ፣ አዳኝን አስታውሱ። እርሱ በምድር ላይ እያለ ማን እንደነበረ፣ ከሌሎች ጋር እንዴት እንደተነጋገረ፣ እና በስራው እንዴት ደግነት እንዳሳየ አስታውሱ። ከማን ጋር ጊዜውን እንዳሳለፈ እና ምን እንዳስተማረ አስታውሱ። አዳኝ “መልካም እያደረገ ዞረ” (የሐዋሪያት ስራ 10፥38)። ህሙማንን ጎበኘ። የአባቱን ፍላጎት ለመፈጸም የወሰነ ነበረ።

ከሁሉም በላይ፣ ለእኛ ባለው ታላቅ ፍቅር፣ የእኛን ኃጢያት እድፍ ለማውጣት ታላቅ ዋጋ እንደከፈለ ለማስታወስ እንችላለን። እርሱን ስናስታውስም፣ እርሱን ለመከተል ያለን ፍላጎት ያድጋል። በተጨማሪም ደግ፣ ምህረት ሰጪ፣ እና የእግዚአብሔርን መሻት ለመፈለግ እናም ለማከናወን በተጨማሪ ፈቃደኞች ለመሆን እንፈልጋለን።

ምን የተሻለ ለማድረግ እንደሚያስፈልጋችሁ አስታውሱ።

አዳኝን—የእርሱን ንጹነት እና ፍጹምነት—የእኛን እንከንነት እና ፍጹም አለመሆን ጋር ካለማነጻጸር ለማሰብ አስቸጋሪ ነው። ትእዛዛቱን ለማክበር ቃል ኪዳኖች ገብተናል፣ ነገር ግን ከዚህ ከፍተኛ መሰረት በብዛት የወደቅን ነን። ነግር ግን አዳኝ ይህ እንደሚሆን አውቋል፣ ለዚህም ነው የቅዱስ ቁርባን ስርዓት የሰጠን።

ቅዱስ ቁርባን የብሉይ ኪዳን መስዋዕት ከማቅረብ ድርጊት ጋር መጀመሪያ አለው፣ ይህም ኃጢያትን መናዘዝ ይጨምራል ( ዘሌዋውያን 5፥5 ተመልከቱ)። እንስሳትን የምንሰዋ አይደለንም፣ ነገር ግን ኃጢያቶቻችንን ለማስወገድ እንችላለን። ቅዱሳት መጻህፍት ይህን መስዋዕት “የተሰበረ ልብ እና የተዋረደ መንፈስ” (3 ኔፊ 9) ብለው ይጠሩታል። ወደ ቅዱስ ቁርባን ንስሀ በሚገባ ልብ ኑ (ት. እና ቃ. 59፥1242 ሞሮኒ 6፥2) ተመልከቱ ይህን ስታደርጉ፣ ለኃጢያቶቻችሁ ምህረትን ታገኛላችሁ እናም ወደ እግዚአብሔር ከሚመራው መንገድ አትወጡም።

እድገታችሁን አስታውሱ

በቅዱስ ቁርባን ስርዓት ጊዜ ህይወታችሁን ስተፈትሹ፣ ሀሳባችሁ ስህተት ባደረጋችሁት ነገሮች ብቻ ላይ ሳይሆን ደግሞም በትክክል ስላደረጋችሁትም፣ እንዲሁም የሰማይ አባት እና አዳኝ በእናንተ የተደሰቱበት የተሰማችሁ ጊዜዎች ላይ ሀሳቦቻችሁ እንዲያተኩሩ አድርጉ። በቅዱስ ቁርባን ጊዜ እግዚአብሔር እነዚህ ነገሮች እንዲታያችሁ ለመጠየቅ ጊዜ ውሰዱ። ይህን ካደረጋችሁ፣ ስሜት እንደሚኖራችሁ ቃል እገባለሁ። ተስፋ ይሰማችኋል።

ይህን ሳደርግ፣ እኔ ከፍጹምነት የራቅሁኝ ብሆንም፣ ዛሬ ትላንትና ከነበርኩት የተሻልኩኝ እንደሆንኩ መንፈስ ማረጋገጫ ይሰፍጥኛል። እና ይህም፣ በአዳኝ ምክንያት ነገ እንደሚሻለኝም ልበ ሙሉ ነኝ።

ሁልጊዜ ረጅም ጊዜ ነው፣ እናም የትኩረት ጥረት ያስፈልገዋል። ከተሞክሮ በአንድ ነገር ላይ በህሊና ለማተኮር እንዴት ከባድ እንደሆነ ታውቃላችሁ። ነገር ግን እርሱን ለማስታወስ የገባችሁትን ቃል ኪዳን ለመጠበቅ በደንብ ብትችሉም፣ እርሱ ሁልጊዜም ያስታውሳችኋል።

አዳኝ ፈተናዎቻችሁን ያውቃል። የህይወት ችግር በእናንተ ላይ እንደ ሸከም ሲሆን ምን እንደሚሰማችሁ ያውቃል። “[እናንተም] ሁልጊዜ መንፈሱ [ከእናንተ] ጋር ይሆን ዘንድ፣” (ት. እና ቃ. 20፥77፤ ትኩረት ተጨምሮበታል) እርሱን ሁል ጊዜ በማስታወስ እና እርሱን በመታዘዝ የሚመጡት በረከቶችን እንዴት በፍጥነት እንደምትፈልጉም ያውቃል።

ስለዚህ፣ ወደ ቅዱስ ቁርባን ጠረጴዛ በየሳምንቱ፣ እንደገና በእርሱ ፊት ሁልጊዜ እንደምታስታውሱት ለመመስከር እድል እየሰጣችሁ፣ እንኳን ደህና መጣችሁ ይላችኋል።

ማስታወሻ

  1. ስፔንሰር ደብሊው. ኪምባል፣ “Circles of Exaltation” [ለቤተክርስቲያኗ የሀይማኖት አስተማሪዎች የተሰጠ ንግግር፣ ሰኔ 28፣ 1968 (እ.አ.አ)]፣ 5።

አትም