2018 (እ.አ.አ)
እርሷን እና ቤተሰቧን እወቁ
የካቲት 2018 (እ.አ.አ)


የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ማስተማሪያ መሰረታዊ መርሆዎች፣ ጥር 2018 (እ.አ.አ)

እርሷን እና ቤተሰቧን እወቁ

የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ትምህርት እምነቷን ለማጠናከር እና አገልግሎት ለመስጠት እንረዳት ዘንድ እያንዳንዷን እህት ስለማወቅ እና ስለማፍቀር ነው።

እምነት፣ ቤተሰብ፣ እርዳታ

ሪታ ጀፕሰን እና የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት አስተማሪዋ እርስ በራስ ሲጎበኙና የወንጌል መርሆችን ሲካፈሉ መልካም ጓደኛዎች ሆኑ። ነገር ግን የእነርሱ ጉብኝት ደግሞም የቃል ጨዋታዎችን አብሮ መጫወትን ያካትታል። ይህም ሪታ ስለሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት አስተማሪዋ የምትወደው ነገር ነበር ምክንያቱም ጓደኞች እንደሆኑ ስለምታውቅ እና የምትጎበኛት “ዝርዝሩን ለመቁጠር” ብቻ እንዳልሆነ ስለምታውቅ ነበር። እህቶች አብረው ለመንሸራሸር ወይም ልጆቹ ሲጫወቱ ሳሉ የአትክልት ስፍራዎችን ለማረም አይነት በጉብኝት ለማድረግ የሚችሉት ብዙ ነገሮች አሉ።

የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ሸንጎ አባል ሽማግሌ ጀፍሪ አር. ሆላንድ እንዳሉት፣ “ራሳችሁን ለልጆቹ እንደ ጌታ መልእክተኞች ተመልከቱ። በምትኩ ቀና የሆነ፣ በወንጌል ላይ ባተኮረ መልኩ ለአባላት በማሰብ፣ በርህራሄ መንገዶች አንዱ እንዱን በመጠበቅ እና በመንከባከብ፣ በተቻለው መንገድ ሁሉ የመንፈሳዊውን እና ጊዜአዊ ፍላጎቶች የሚሟሉበትን ወቅት እንደምትመሰርቱ ተስፋ እናደርጋለን።”1

የእስራኤል ህዝብ ስለዚህ ርዕስ ቀጥተኛ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል፥ “እናንተ በግብፅ ምድር እንግዶች ነበራችሁና ከእናንተ ጋር የሚቀመጥ እንግዳ እንደ አገር ልጅ ይሁንላችሁ፥ [እርሷንም] እንደ [ራስሽ ውደጂ]”(ዘሌዋውያን 19፥34)። በጉብኝት የምናስተምራቸው እህቶች አገልግሎትን ስንጀምር እንደ “እንግዶች” ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን እርሷን እና ቤተሰቧን ስናውቅ፣ የእርስ በራስ “ሸክም ቀላል እንዲሆኑ ዘንድ ለመሸከም ፈቃደኞች በመሆን” እና “ልባቸው በአንድ ላይ በአንድነትና፣ አንዱ ሌላኛውን ባለው ፍቅር እንዲጣበቁ” (ሞዛያ 18፥8፣ 21) የማድረግ ፍላጎታችን ይጨምራል።

የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት ሬይናል ኤል. አቡርቶ በቅርብ የተፋታች አዲስ የቤተክርስቲያኗ አባል የነበረችበትን ጊዜ ታስታውሳለች። እንዲህም አለች፣ “የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት አስተማሪ ወደ ቤቴ መጡ፣ እናም ክፍል የመሆን የሚያሞቅ ስሜትን እና ፍቅርን በልቤ አመጡልኝ።”2

ይህን አስቡበት

በጉብኝት ከምታስተምሯቸው የእህቶች ቤተሰቦች ውስጥ፣ ለማወቅ እና ለማስታወስ የሚገባችሁ ምን በቅርብ የሚመጡ ድርጊቶች አሉ?

ማስታወሻዎች

  1. ጀፍሪ አር. ሆላንድ፣ “Emissaries to the Church፣” Liahona፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 62።

  2. ሬይናል ኤል. አቡርቶ፣ “What Has Relief Society Been for Me?” Brigham Young University Women’s Conference፣ ግንቦት 5፣ 2017 (እ.አ.አ)፣ LDS.org{86}።

አትም