2018 (እ.አ.አ)
የእግዚአብሔርን ድምጽ ለመስማት መዘጋጀት
ሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ)


ወጣቶች

የእግዚአብሔርን ድምጽ ለመስማት መዘጋጀት

ቅዱሳት መጻህፍት እንደሚነግሩን እግዚአብሔር ወንድና ሴትን ከፈጠረ በኋላ በመጀመሪያ ያደረገው ነገር እነሱን ማነጋገር እናም በጣም ጠቃሚ መረጃዎችን እና መመሪያዎችን መስጠት ነበር። በሚያዝያ እና በጥቅምት ወር በአጠቃላይ ጉባኤ ውስጥ የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ሲናገሩን እና ጌታ እኛ እንድናዳምጥ የሚፈልገውን ምክር ሲሰጡ ተመሳሳይ በረከት እናገኛለን።

በአጠቃላይ ጉባኤ በአገልጋዮቹ በኩል የእግዚአብሔርን ድምጽ ሰምታችሁ ታውቃላችሁን? የምትፈልጉትን መልስ አንድ የተወሰነ መልእክት እንደሰጣችሁ ተሰምቷችሁ ያውቃልን? በማስታወሻ ውስጥ፣ ያንን ተሞክሮ እና እንዴት እንደረዳችሁ መጻፍ ትችላላችሁ። ከዚያም በቅዱስ መጻህፍት ጥናታችሁ ወቅት ጥያቄዎችን በመፃፍ እና በማጥናት ይህንን የጌታን ድምጽ በመጪው ጉባኤ ለማዳመጥ ተዘጋጁ። በስብሰባው ወቅት መልሶች እና ግንዛቤዎችን ለመቀበል ወደ ሰማይ አባት ይጸልዩ። የጌታን አገልጋዮች ስታዳምጡ፣ በግል የመንፈስ ማነሳሻ ላይ አተኩሩ። ምን ተማራችሁ? እንዴት ለለውጥ የመነሳሻ መንፈስ ተሰማችሁ? እነዚያን መነሳሳቶች ጻፉ ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ እያናገራችሁ ነውና!

የሰማይ አባት እንደሚወዳችሁ እና በትክክለኛው አቅጣጫ እንደሚመራችሁ አስታውሱ። በባሪያዎቹ በኩል ድምፁን ለመስማት ስትሞክሩ ትባረካላችሁ እና ትታነጻላችሁ።

አትም