2018 (እ.አ.አ)
የእግዚአብሔር ቃል ለልጆቹ
ሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ)


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ መጋቢት 2018 (እ.አ.አ)

የእግዚአብሔር ቃል ለልጆቹ

ቅዱሳት መጻህፍት እንደሚነግሩን እግዚአብሔር ወንድና ሴትን ከፈጠረ በኋላ በመጀመሪያ ያደረገው ነገር እነሱን ማነጋገር ነበር።1 ለእነሱ የሚሰጣቸው አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችና ውድ የሆኑ መመሪያዎች ነበረው። ዓላማው ወደ ደስታ እና ዘለአለማዊ ክብር ለመምራት እንጂ ሸክም ወይም ጭንቀትን ለመስጠት አልነበረም።

እናም ይህ መነሻ ነበር። ከዚያ ቀን ጀምሮ እስካሁን ድረስ እግዚአብሔር ከልጆቹ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል። የእርሱ ቃላት በየዘመናቱ ደቀ-መዛሙርቶች ተጠብቀዋል፣ እንደ ትልቅ ሃብት ተይዘዋል እናም ተጠንተውታል። የእግዚ አብሔርን ፈቃድ ለማወቅ በሚፈልጉ ሰዎች የተከበሩ ናቸው እናም “ጌታ እግዚአብሄር ምስጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም እንደማያደርግ” ያለውን እውነታ ይመሰክራሉ።2

ይህም ከዘመናት መጀመሪያ ጀምሮ ንድፍ መንገድ ሆኖ ቆይቷል፣ እናም በዚህም ዘመን ይቀጥላል። ጥሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ብቻ አይደለም፤ ወሳኝ የሆኑ መልዕክቶችን ለልጆቹ ለማስተላለፍ የተቋቋመ የእግዚአብሔር መንገድ ነው። መካከላችን ግለሰቦችን ያስነሳል፣ ነብያቶችን ይጠራቸዋል፣ እና ከእሱ ከራሱ አፍ እንደተቀበልን አድርገን እንድንወስድ የተጋበዝንባቸውን ቃላት ይሰጣቸዋል።3 በእኔም ድምፅ ሆነ ወይም በአገልጋዮቼ ድምፅ፣ አንድ ነው ብሎ አውጇል።4

ይህ በዳግም ከተመለሰው ወንጌል መልእክት ውስጥ እጅግ የከበረው፣ የሚያበረታታው፣ እና ተስፋ ሰጪ መልዕክቶች አንዱ ነው፤ እግዚአብሔር ጸጥ አላለም! ልጆቹን ይወዳል። በጭለማ ውስጥ እንድንጠፋ በብቻችንን አልተወንም።

በየአመቱ ሁለት ጊዜ፣ በሚያዚያ እና በጥቅምት፣ በአስገራሚ አጠቃላይ ጉባኤዎቻችን አማካይነት የጌታን ድምፅ ለመስማት እድል አለን።

ተናጋሪው በአጠቃላይ ጉባኤ ላይ ረጅም ጉዞን ወደ መድረኩ ከማድረጉ በፊት፣ እሱ ወይም እርሷ ንግግር ለማድረግ በተሰጣቸው ሃላፊነት ምክንያት ከፍተኛ ጥረት፣ ጸሎት፣ እና ጥናት እንደሚያደርጉ የግል ምስክሬን እሰጣችኋለሁ። እያንዳንዱ የጉባዬ መልእክቶች ጌታ የእርሱ ቅዱሳን መስማት እንዲችሉ የሚፈልጓቸውን ነገሮች ለመጨመር የማይቆጠሩ የዝግጅት ሰዓቶችን እና ከልብ የመነጩ ስሜቶችን ይወክላል።

እኛ አድማጮች ከተናጋሪው ጋር የሚስተካከል ዝግጅት ብናደርግ ምን ሊከሰት ይችላል? ጉባኤን ከጌታ ከራሱ መልክት የመቀበያ እድል አድርገን ከተመለከትን ለጠቅላይ ጉባኤ ያለን አቀራረብ እንዴት ሊለይ ይችላል? በአጠቃላይ ጉባኤ ውስጥ ባሉ ቃላት እና ሙዚቃ በኩል፣ ለሚኖሩን ማንኛውም ጥያቄዎች ወይም ችግሮች ለግል የተበጁ ምላሾች እንቀበላለን ብለን መጠበቅ እንችላለን።

የሰማይ አባት በእውነት ለእናንተ እንደሚናገር ጥያቄ ካደረባችሁ፣ የህጻናት ክፍል ልጆች የሚዘምሩትን [እናንተ] የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ፣ እናም እዚህ [እናንተን] ልኳችኋል የሚለውን ቀላል እና ጥልቅ ቃላት አስታውሳችኋለሁ። የእሱ ዓላማ ከእርሱ ጋር አንድ ቀን እንድትኖሩ ለመርዳት ነው።

የሰማይ አባትን እንደእርሱ ልጅ የምትቀርቡት ከሆናችሁ፣ ምራኝ፣ ከአጠገቤ ተራመድ፣ መንገዱን እንዳገኝ እርዳኝ ብለን ከልብ በሆነ ስሜት ልትጠይቁት ትችላላችሁ። እኔ ማድረግ ያለብኝን ሁሉ አስተምረኝ። እሱ በመንፈስ ቅዱስ በኩል ያነጋግራችሁ፣ እና “የእርሱን ፈቃድ ለማድረግ” የእናንተ ፋንታ ይሆናል። እንዲህ ካደረጋችሁ የተትረፈረፉ በረከቶችም በጎተራው እንዳሉ ቃል እገባላችኋለሁ።5

የጌታ አመራር በአለም ታሪክ ሁሉ አስፈላጊ እንደሆነ ሁሉ ዛሬም እንዲሁ በጣም አስፈላጊ ነው። የጌታን ቃል ለማዳመጥ በምንዘጋጅበት ወቅት፣ ጌታ በአገልጋዮቹ በሚናገርበት ጊዜ መረዳት እንድንችል፣ እንድንታነጽ፣ እና አብረን መደሰት እንድንችል የእውነት መንፈስን በትጋት እንሻ።6

እነዚህን ነገሮች በማድረግ የገሃነምን ደጃፍ [አያሸንፈንም]፤ አዎ፣ እግዚአብሔር አምላክም ከፊታችን የጭለማ ኃይላትን ይበትናል፣ ሰማያትም [ለእኛ] መልካምነት ምክንያት እና ለራሱም ስም ክብር ሲል እንዲንቀጠቀጡ [እንደሚያደርግ] እመሰክራለሁ።7

አትም