የአገልግሎት መሰረታዊ መርሆች፣ ሰኔ 2018 (እ.አ.አ)
ጥሩ አዳማጮች የሚያደርጓቸው አምስት ነገሮች
በእውነት ማዳመጥ የሌሎችን መንፈሳዊ እና ምድራዊ ፍላጎቶች አዳኝ እንደሚያደርገው ለማድረግ እንዴት ለመርዳት እንደምትችሉ ለማወቅ ይረዳችኋል።
የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ምልዓተ ጉባኤ አባል ሽማግሌ ጀፍሪ አር. ሆላንድ እንዳሉት፥ “ምናልባት ከመናገር በላይ በጣም አስፈላጊ የሆነው ማዳመጥ ነው።. … በፍቅር ካዳመጥን፣ ምን ማለት እንደሚያስፈልገን ማሰብ አያስፈልገንም። ይህም ይሰጠናል—በመንፈስም”1
ማዳመጥ ለመማር የምንችለው ስጦታ ነው። ማዳመጥ ለሌሎች ያለንን ፍቅር ያሳያል፣ ጠንካራ ግንኙነት ለመገንባት ይረዳል፣ እናም የሌሎችን ፍላጎቶች ለመረዳት የሚረዳን ስጦታ በመስጠት የሚባርከንን መንፈስ ይጋብዛል።2 ለማዳመጥ የምንችልበትን ለማሻሻል የምንችልበት አምስት መንገዶች እነዚህ ናቸው።
1.ጊዜ ስጧቸው
ብዙ ሰዎች ከመናገራቸው በፊት ሀሳባቸውን የማሰባሰቢያ ጊዜ ያስፈልጋቸዋል። አንድ ነገር ከማለታቸው በፊት እና ካሉ በኋላ ለማሰብ ጊዜ ስጧቸው ( ያዕቆብ 1፥19ይመልከቱ)። መናገር በመፈጸማቸው ምክንያት ለማለት የሚፈልጓቸውን ሁሉ ብለዋል ማለት አይደለም። ጸጥ ለማለት አትፍሩ ( ኢዮብ 2፥11–3፥1 እና አልማ 18፥14–16 ይመልከቱ)።
2. ትኩረት ስጡ
ሌሎች ከሚናገሩ በላይ በፍጥነት እናስባለን። መደምደሚያው ላይ ለመድረስ ለመፍጠን ወይም እነርሱ ሲጨርሱ ምን እንደምትሉ ወደፊት ለማሰብ የሚኖራችሁን አስተሳሰብ ተቋቋሙ ( ምሳሌ 18፥13ይመልከቱ)። በዚህ ምትክ፣ ለመረዳት ባለ ፍላጎት አድምጡ። መልሳችሁ የተሻለ ይሆናል ምክንያቱም ይህም በታላቅ መረዳት ላይ የተመሰረተ ነውና።
3. ግልፅና
ለመረዳት ያልቻላችሁትን ግልፅ ለማድረግ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ አትፍሩ ( ማርቆስ 9፥32)። ግልፅ ማድረግ አለመግባባትን ይቀንሳል እናም ንግግሩም ስሜታችሁን እንደሚስብ ያሳያል።
4. ማሰላሰል
የምትሰሙትን እና ሌሎች ምን እንደሚሰማቸው የተረዳችሁትን በራሳችሁ ቃላት መልሳችሁ በሏቸው። ይህም እነርሱን እንደተረዷቸው እንዲያውቁ ይረዳቸዋል እና ግልፅ ለማድረግም እድል ይሰጣቸዋል።
5. የምትስማሙበትን አግኙ
በሚባለው ሁሉ የማትስማሙ ይሆናል፣ ነገር ግን የራሳችሁን ስሜት በስህተት ባለማቅረብ ለመስማማት የምትችሉትን ተስማሙበት። ተስማሚ መሆን ታላቅ ጭንቀትን እና ተከላካይ መሆንን ይቀንሳል (ማቴዎስ 5፥25)።
ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዳስተማሩት፣ እኛም “ለማዳመጥ መማር፣ እና ከእርስ በራስ ለመማር ማዳመጥ”3 ይገባናል። ስለሌሎች ለመማር ባለ አላማ ስታዳምጡ፣ የእነርሱን ፍላጎት በተሻለ ለመረዳት እና በአካባቢያችሁ ያሉትን አዳኝ እንደሚያደርገው ለመርዳት እንድትችሉ መነሳሻን ለመስማት በተሻለ ቦታ ላይ ትሆናላችሁ።
ማዳመጥ ማፍቀር ነው።
የሽማግሌ ሆላንድ ታሪክ የማዳመጥን ሀይል በምሳሌ ያሳያል፥
“ጓደኛዬ ትሮይ ራስል መኪናውን ከጋራዡ በቀስታ አስወጣ። … የኋለኛው ጎማ ጉብታ ላይ እንደወጣ ተሰማው። … ሲወጣ ያገኘው የዘጠኝ አመት ልጁ ኦስትን የድንጋይ ንጣፉ መንገድ ላይ ፊቱ ተዘቅዝቆ ወድቆ ነበር። … ኦስትን ህይወቱ አልፏል።
መተኛት ወይም ሰላም ማግኘት ሳይችል፣ ትሮይ ከልቡ አዝኖ ነበር። … ነገር ግን በዛ መሪር ጊዜ … ጆን ማኒንግ መጡ። …
“ጆን እና የአገልግሎት ወጣት ጓደኛው የራስልን ቤት ለመጎብኘት በምን እቅድ እንደተጠቀሙ አላውቅም። … የማውቀው ነገር ባለፈው ፀደይ ልክ ትሮይ ሩሴል ትንሹን ኦስትንን እንዳነሳው፣ እርሱን ደግሞ ወንድም ማኒንግ ከመንገዱ አደጋ ደርሶ ከፍ እንዳደረገው ነው። … በወንጌል ውስጥ ወንድምነት፣ ጆን በቀላሉ የክህነት ድርሻውን ወሰደ እና ትሮይ ሩሴልን ጠበቀው። እንዲህም ማለት ጀመረ፣ ‘ትሮይ፣ ኦስተን በእግርህ እንድትነሳ ይፈልግሀል—እንዲሁም በቅርጫት ኳስ መጫወቻ ላይ—ስለዚህ በየጠዋቱ በ5፥13 በዚህ እገኛልሁ። ተዘጋጅ። …’
በኋላም ትሮይ እንደነገረኝ፣ “‘መሄድ አልፈልግም ነበር፣ ምክንያቱም ኦስትን ሁልጊዜም ከእኔ ጋር ነበርና። … ነገር ግን ጆን ወተወተኝ፣ ስለዚህ ሄድኩ። ከዛ የመጀመሪያ ቀን በኋላ፣ አወራን—ወይም እኔ አወራሁ—እናም ጆን አዳመጠኝ። መጀመሪያ ላይ ከባድ ነበር፣ ነገር ግን ከጊዜ በኋላ በህይወቴ ዳግም ፀሀይ እስክትወጣ ድረስ እኔን በወደደኝ እና ባዳመጠኝ፣ [በጆን ማኒንግ] አማካኝነት ጥንካሬዬን እንዳገኘው አስተዋልኩ።’”4
© 2018 በ Intellectual Reserve, Inc. መብቶች ሁሉ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ. ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፥ 6/17 (እ.አ.አ)። ትርጉም የተፈቀደበት፥ 6/17 (እ.አ.አ)። Ministering Principles, June 2018. ትርጉም። Amharic. 15055 506