የአገልግሎት መሰረታዊ መርሆች፣ ሐምሌ 2018 (እ.አ.አ)
በርህራሄ እርዳታ ስጡ
የአዳኝን የርህራሄ ምሳሌ ስትከተሉ፣ በሌሎች ህይወቶች ውስጥ ለውጥ ለማምጣት እንደምትችሉ ታውቃላችሁ።
ርኅራኄ የሌሎችን ችግር መገንዘብ ሲሆን ለማስታገስ ወይም ለማቃለል ካለ ፍላጎት ጋር የተጣመረ ነው። አዳኝን ለመከተል የሚገባ ቃል ኪዳን “አንዳችሁ የአንዳችሁን ሸክም ለመሸከም” የሚገባ የርህራሄ ቃል ኪዳን ነው (ሞዛያ 18፥8)። ሌሎችን ለመንከባከብ የሚሰጥ ሃላፊነት፣ “በርህራሄ፣ ልዩነትን በማምጣት” (ይሁዳ 1፥22) ጌታ እንደሚያደርገው የማገልገል እድል ነው። ጌታ እንደሚያዘው፣ “ቸርነትንና ምሕረትን ሁላችሁ ለወንድሞቻችሁ አድርጉ” (ዘካርያስ 7፥9)።
የአዳኝ ርህራሄ
ርህራሄ በአዳኝ አገልግሎት ውስጥ የሚገፋፋው ሀይል ነበር (sidebar: “A Compassionate Savior” ይመልከቱ)። ለሰዎች ያለው ርህራሄ በበርካታ ጊዜያት በአካባቢው ያሉትን እንዲረዳ አደረገው። የሰዎችን ፍላጎት እና መሻት በመለየት፣ እነርሱን ለመባረክ እና ለእነርሱ ከሁሉም በላይ ለውጥ በሚያመጣ መንገድ ለማስተማር ችሏል። አዳኝ ከስቃያችን በላይ ከፍ ለማድረግ ያለው ፍላጎት ለመጨረሻው የርህራሄ ስራ መራው፥ ለሰው ዘር ኃጢያቶችና ስቃይ ያደረገው የኃጢያት ክፍያው ነው።
ለሰዎች ፍላጎቶች መልስ ለመስጠት ያለውን ችሎታ እኛው ስናገለግል ለመሆን ለመጣር የምንችልበት ነገር ነው። በጽድቅ ስንኖር እና በመንፈስ መነሳሳትን ስናዳምጥ፣ ትርጉም ባለው መንገር ለመርዳት ለመጣር እንነሳሳለን።
የርህራሄ ቃል ኪዳናችን
የሰማይ አባት ልጆቹ ርህራሄ ያላቸው እንዲሆኑ ይፈልጋል (1 ቆሮንጦስ 12፥25–27 ይመልከቱ)። እውነተኛ ደቀመዛሙርት ለመሆን፣ለሌሎች፣ በልዩም እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው፣ርህራሄ ማግኘት እና ማሳየት ያስፈልገናል (ት. እና ቃ. 52፥40)።
በጥምቀት ቃል ኪዳናችን በኩል የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በራሳችን ላይ በመውሰድ፣ ርህራሄን ለመጠቀም ፈቃደኞች እንደሆንን እንመሰክራለን። ፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ. አይሪንግ፣ የቀዳሚ አመራር ሁለተኛ አማካሪ፣ እንዳስተማሩት፣ መንፈስ ቅዱስ ይህን ለማድረግ ይረዳናል፥ “እናንተ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን የቃል ኪዳን አባላት ናችሁ። …
“የሀዘን ሸክም እና አስቸጋሪ ነገርን ተሸክሞ ወደ ፊት ለመሄድ እየተቸገረ ያለ ሰውን የመርዳት ፍላጎት ስሜት ያላችሁ ለዛ ነው። ሸክማቸው ቀላል ለማድረግ እና እንዲፅናኑ አመቺ በማድረጉ ላይ ጌታን ለመርዳት ቃል ገብታችኋል። የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ስትቀበሉ እነኛን ሸክሞች ለማቅለል የመርዳትን ሀይል ተሰጥቷችሁ ነበር።”1
ለምሳሌ፣ አንድ የራሺያ እህት ከአንድ አመት በላይ በቤተክርስቲያን ተሳታፊ እንዳትሆን ያደረጋት አስቸጋሪ የቤተሰብ ጉዳይ ነበራት። የቅርንጫፍ ውስጥ የነበረች ሌላ እህት በየእሁዱ በመደወል ስለንግግሮች፣ የሚስዮን ጥሪዎች፣ ስለተወለዱ ህጻናት፣ እና ሌሎች የቅርንጫፍ ዜናዎች በመንገር በርህራሄ ታገለግላት ነበር። በቤት የምትቆየው እህት የቤተሰብ ጉዳይ መፍትሄ ሲያገኝ፣ በጓደኛዋ የየሳምንት የስልክ ንግግር ምክንያት በቅርንጫፉ ውስጥ ክፍል እንዳላት ይሰማት ነበር።
© 2018 በIntellectual Reserve, Inc. መብቶች ሁሉ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ. ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፥ 6/17 (እ.አ.አ)። ትርጉም የተፈቀደበት፥ 6/17 (እ.አ.አ)። Ministering Principles, July 2018 ትርጉም። Amharic. 15050 506