የአገልግሎት መሰረታዊ መርሆች፣ ነሐሴ 2018 (እ.አ.አ)
ትርጉም ያለው ግንኙነቶችን መገንባት
ከእነርሱ ጋር ትርጉም ያለው ግንኙነት ሲኖረን ሌሎችን ለመንከባከብ ያለን ችሎታ ይጨምራል።
ሌሎችን ለማገልገል ያለው ግብዣ ከእነርሱ ጋር ለመንከባከብ የሚያስችል ግንኙነትን የመገንባት እድል ነው—ይህም እነርሱ ለእርዳታ ለመጠየቅ ወይም ለመቀበል ምቾት እንዲኖራቸው የሚያደርግ አይነት ግንኙነትም ነው። እንደዚያ አይነት ግንኙነት ለመገንባት ጥረት ስናደርግ፣ በግንኙነቱ በሁለቱም በኩል ህይወቶችን ለመቀየር እግዚአብሔር ይችላል።
የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ፣ ሼረን ዩባንክስ እንዳሉት፣ “ትርጉም ካለው ግንኙነት ውጪ ምንም ትርጉም ያለው ለውጥ እንደማይኖር እውነተኛ እምነት አለኝ።” እናም፣ እርሳቸው እንዳሉት፣ የአገልግሎት ስራችን በሌሎች ህይወቶች ውስጥ ለውጥ የሚያመጣ እንዲሆን፣ እነዚህ “ለመፈወስ እና ለማዳመጥ እናም ለመተባበርና ለማክበር ባለ ልባዊ ፍላጎት የተተከሉ”1 መሆን ይገባቸዋል።
ትርጉም ያለው ግንኙነቶች ዘዴዎች አይደሉም። በርህራሄ፣ በልባዊ ጥረቶች፣ እና “ግብዝነት በሌለው ፍቅር” (ት. እና ቃ. 121፥41) ላይ የተገነቡ ናቸው።2
ግኑኝነቶችን መገንቢያ እና ማጠናከሪያ መንገዶች
“እኛ [ግንኙነቶችን] በአንድ ጊዜ አንድ ሰውን የምንገነባቸው ናቸው፥” ብለዋል የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ አባል ሽማግሌ ዲየትር ኤፍ. ኡክዶርፍ።3 ከምናገለግላቸው ጋር ትርጉም ያለው ግንኙነቶችን ለመገባት ስንጥር፣ መንፈስ ቅዱስ ሊመራን ይችላል። የሚቀጥሉት ሀሳቦች ሽማግሌ ኡክዶርፍ ባቀረቧቸው ንድፎች ላይ የተመሰረቱ ናቸው።4
-
ስለእነርሱ ተማሩ
ፕሬዘደንት ኤዝራ ታፍት ቤንሰን [1899-1994 (እ.አ.አ)] እንዳስተማሩት፣ “በደንብ የማታውቋቸውን በደንብ ለማገልገል አትችሉም።” የእያንዳንዱን የቤተሰብ አባል ስም ማወቅን እና እንደ ልደት፣ በረከቶች፣ ጥምቀቶች፣ እና ጋብቻዎች አይነት አስፈላጊ ድርጊቶችን ማወቅን በሀሳብ አቅርበዋል። ይህም ለቤተሰብ አባል ልዩ ስኬት ወይም ፍጻሜ መልካም ምኞትን ለመስጠት ማስታወሻ ለመጻፍ ወይም ስልክ ለመደወል እድል ይሰጣል።5
-
አብሮ ጊዜ ማሳለፍ።
ግንኙነትን ለመገንባት ጊዜ ይፈጃል። ከእነርሱ ጋር በተደጋጋሚ ለመገናኘት እድሎችን ፈልጉ። ሰዎችን እንደምታስቡላቸው ማሳወቅ ለጤናማ ግንኙነት አስፈላጊ እንደሆነ ጥናቶች አሳይተዋል።6 እንድታገለግሉ የተጠራችሁባቸውን በተደጋጋሚ ለመጎብኘት ሂዱ። በቤተክርስቲያን ውስጥም አነጋግሯቸው። እንደ ኢሜል፣ ፌስ ቡክ፣ ኢንስተግራም፣ ትዊተር፣ ስካይፕ፣ የስልክ ጥሪ፣ ወይም ፖስታ የመላክ አይነት፣ መልካም እንደሆነ የሚሰማችሁን ማንኛውንም ተጨማሪ መንገዶችንም ተጠቀሙ። የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ አባል ሪቻርድ ጂ. ስኮት [1928–2015 (እ.አ.አ)] ስለቀላል እና የፈጠራ ችሎታ ያለው የፍቅር እና የድጋፍ መግለጫ ሀይል ተናግረዋል፥ “በብዛት ቅዱሳት መጻህፍቴን እከፍታለሁ፣ … እናም [ባለቤቴ] ጅኒን በገጾቹ ውስጥ በሚስጥር ያስገባችውን የፍቅር እና የድጋፍ ማስታወሻን አገኛለሁ። … እነዚያ ውድ ማስታወሻዎች … ታላቅ ዋጋ ያላቸው የምቾት እና የማነሳሻ ሀብቶች በመሆን ይቀጥላሉ።”7
ደግሞም፣ ግንኙነት ሁለት እንደሚያስፈልገው አስታውሱ። ፍቅር እና ጓደኝነት ለማቅረብ ትችላላችሁ፣ ነገር ግን የሚቀርበው ተቀባይነት እና የጋራ ካልሆነ ግንኙነት ለማደግ አይችልም። ሌላው ግለሰብ ተቀባይ የማይሆን ከሆነ፣ ግንኙነትን በግድ አታድርጉት። እርሱ ወይም እርሷ ልባዊ ጥረታችሁን እንዲመለከት ወይም እንድትመለከት ጊዜ ስጡት ወይም ስጧት፣ እናም አስፈላጊ ከሆነም፣ ትርጉም ያለው ግንኙነት የሚቻል እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ከመሪዎቻችሁ ጋር ተማከሩ።
-
እንደምታስቡላቸው መረጃ ስጧቸው።
ትርጉም ያለው ግንኙነት ከማስመሰል በላይ ማድረግን ያስፈልገዋል። ጥልቀት የሌለው ግንኙነት ስለቀጠሮ፣ ስለአየር ሁኔታ፣ እና ሌሎች ትትንሽ ጉዳዮች መነጋገር የተሞላበት ነው፣ ነገር ግን ይህም ትርጉም ያለው ግንኙነቶችን ለመስራት አስፈላጊ የሆኑትን ስሜት፣ እምነት፣ አላማዎች፣ እና የሚያስጨንቁ ሀሳቦች ማካፈል የሚጨምር አይደለም። የሰማይ አባት ይህም ተጨማሪ ትርጉን ያለው ግንኙነትን የእርሱን ስሜቶች እና እቅዶች ከልጁ ጋር (ዮሀንስ 5፥20 ይመልከቱ) እና ከእኛም ጋር በነቢያት በኩል (see አሞፅ 3፥7) በማካፈል ምሳሌ ሰጥቶናል። የቀን በቀን ድርጊቶችን እና የህይወት ለውጦችን መንፈስ በሚመራበት በኩል እርስ በራስ በመካፈል፣ በጋራ ያለንን ፍላጎት እና የጋራ የሆኑ ልምምዶችን በማግኘት ለእርስ በራስ አድናቆት እንዲኖረን እንሆናለን።
ማድመጥም እናንተ እንደምታስቡላቸው መረጃ የመስጠታችሁ ዋና ክፍል ነው።8 በጥንቃቄ ስታዳምጡ፣ እናም ስለ ፍላጎታቸውን ስትረዱ መረጃ ስታገኙ እናም እነርሱ እንደሚፈቀሩ፣ እንደሚግባቡ፣ እና ደህንነት ሲሰማቸው፣ ሌሎችን ወደ ክርስቶስ ለማምጣት ያላችሁ እድል ይጨምራል።
-
ልዩነትን እና አንድነትን አድንቁ።
ሽማግሌ ኡክዶርፍ እንዳሉት፣ “አንዳንዶች … ቤተክርስቲያኗ አባላትን ከአንድ ንድፍ ለመፍጠር የምትፈልግ እንደሆነች—ይህም ማለት እያንዳንዱ ከሌላው ጋር በምስላቸው፣ በስሜታቸው፣ እና ጸባያቸው አንድ መሆነ እንደሚገባቸው ያምናሉ።” “ይህም የሰውን ከወንድሙ ልዩ አድርጎ የፈጠረውን የእግዚአብሔርን ልዩ የአዕምሮ ችሎታን ይቃረናል። …
“በዚህ ልዩነት ላይ ጥቅም ስናደርግ እና እርስ በራስ ለማደግና ችሎታችንን ሌሎች ደቀ መዛሙርቶችን ከፍ ለማድረግና ለማጠናከር ስንጠቀምበት፣ ቤተክርስቲያኗ ታድጋለች።”9
ሌሎችን እግዚአብሔር እንደሚያፈቅረን ለማፍቀር እግዚአብሔር ሌሎችን እንደሚያየው እንድንመለከታቸው ይጠብቅብናል። ፕሬዘደንት ቶማሴስ. ሞንሰን [1927–2018 (እ.አ.አ)] እንዳስተማሩት፥ “[ሌሎችን አሁን በሚታዩበት ሳይሆን ግን ወደፊት በሚሆኑበት የመመልከት ችሎታ መገንባት አለብን።”10 እግዚአብሔር እንደሚያያቸው ሌሎችን ለመመልከት ለመጸለይ እንችላለን። ሌሎችን ወደፊት በሚኖራቸው እድገት ላይ በመመስረት ስንመለከታቸው፣ ወደዚያ ከፍ ለማለት ያላቸው እድል ከፍተኛ ነው።11
-
አገልግሏቸው።
ለምታገለግሏቸው ሰዎች ፍላጎቶች ስሜት ያላችሁ ሁኑ እናም እርዳታ በሚያስፈልግበት ጊዜም ይሁን ወይም እናንተ በማሰባችሁ ምክንያት ጊዜአችሁን እና ችሎታችሁን ለመስጠት ፈቃደኛ ሁኑ። አደጋ በሚደርስበት፣ በበሽታ፣ ወይም በአስቸኳይ ግዜ መፅናኛ፣ ድጋፍ፣ እና የሚያስፈልገውን እርዳታ ለመስጠት ለማገኘት ትችላላችሁ። ነገር ግን ብዙዎቹ ግንኙነቶች በሁኔታው የሚለወጡ ናቸው። እግዚአብሔር ለመስራት እንጂ እንዲሰራበን አይደለም ነጻ ምርጫ የሰጠን (2 ኔፊ 2፥14 ይመልከቱ)። ሐዋርያው ዮሀንስ እግዚአብሔርን የምናፈቅረው እርሱ በመጀመሪያ ስላፈቀረን ነው እንዳለው (1 ዮሀንስ 4፥19 ይመልከቱ)፣ ሌሎች እውነተኛ ፍቅራችን በአገልግሎታችን ሲሰማቸው፣ ልቦችን ያሰላስላል እናም ፍቅርን እና ታማኝነትን ይጨምራል።12 ይህም ግንኙነትን ለመገንባት የሚያስችል ወደላይ የሚያድግ የደግነት ስራን ይፈጥራል።
አዳኝ እንዳደረገው ማገልገል
ኢየሱስ ክርስቶስ ትርጉም ያለው ግንኙነቶች ከደቀመዛሙርቱ ጋር ገነባ (ዮሀንስ 11፥5 ይመልከቱ)። እነርሱን ያውቅ ነበር (ዮሀንስ 1፥47–48 ይመልከቱ)። ከእነርሱ ጋር ጊዜ አሳለፎ ነበር (ሉቃስ 24፥13–31 ይመልከቱ)። ንግግሩ ጥልቀት ከሌለው በላይ ነበር (ዮሀንስ 15፥15 ይመልከቱ)። የእነርሱን ልዩነት አደነቀ (ማቴዎስ 9፥10 ይመልከቱ) እናም የእነርሱን የእድገት ችሎታ ተመልክቶ ነበር (ዮሀንስ 17፥23 ይመልከቱ)። ምንም እንኳን የሁሉም ጌታ ቢሆንም፣ የመጣው ሊያገለግል እንጂ እንዲገለግሉት አይደለም በማለት ሁሉንም አገለገለ (ማርቆስ 10፥42–45 ይመልከቱ)።
ለማገለገል ከተጠራቹት ጋር ጠንካራ ግንኙነቶችን ለመገንባት ምን ታደርጋላችሁ።
© 2018 በIntellectual Reserve, Inc. መብቶች ሁሉ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ. ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፥ 6/17 (እ.አ.አ)። ትርጉም የተፈቀደበት፥ 6/17 (እ.አ.አ)። Ministering Principles, August 2018. ትርጉም። Amharic. 15051 506