የአገልግሎት መሰረታዊ መርሆች፣ መስከረም 2018 (እ.አ.አ.)
ስለሚያስፈልጋቸው ነገሮች ተመካከሩ
ይህን በብቻችሁ ማድረግ አያስፈልጋችሁም። መመካከር ሌሎችን ለመርዳት የሚያስፈልጋችሁን እርዳታ ሊሰጣችሁ ይችላል።
እግዚአብሔር በዎርዳችሁ ወይም በቅርንጫፋችሁ ውስጥ የሚገኘውን ግለሰብ ወይም ቤተሰብ እንደሚያስፈልጋቸው እርዳታ መሰረት እንድታገለግሉ ጋብዟኋል። እነዚያ የሚያስፈልጓቸው ምን እንደሆኑ እንዴት ለማወቅ ትችላላችሁ? በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ዋና ትኩረት የነበረው፣ የመመካከር መሰረታዊ መርሆ ቁልፍ ነው።
ስለምን እንደምንመካከር ከተወያየን በኋላ፣ እነዚህን እንፈትሻለን፥
-
ከሰማይ አባት ጋር መመካከር።
-
ከተመደቡት ግለሰብ ወይም ቤተሰብ ጋር መመካከር።
-
ከጓደኞቻችን ጋር መመካከር።
-
እናም ለዚያ አንድ ግለሰብ ወይም ቤተሰብ ከተመደቡት ሌሎች ጋር መመካከር።
ከመሪዎቻችን ጋር መመካከር ደግሞም አስፈላጊ ነው። ከመሪዎች ጋር መመካከርን እና በዚያ ድርጊት ውስጥ የአገልግሎት ቃል ጥያቄ ስላለው ክፍል በLiahona ውስጥ የሚገኝ የወደፊት የአገልግሎት መሰረታዊ መርሆች ህትመት ይፈትሻል።
ምን እኛ የምንመካከርባቸው
የሚያስፈልገውን ነገሮች መረዳት እርስ በራስ ለማገልገል አስፈላጊ ነው። ነገር ግን እነዚያ ፍላጎቶች ምን አይነት ቅርጽ አላቸው፣ እናም ከፍላጎት በላይ የሆነ ማወቅ የሚያስፈልጉን ነገሮች አሉን?
ፍላጎቶች በብዙ ቅርጾች ለመምጣት ይችላሉ። የምናገለግላቸው የስሜት፣ የገንዘብ፣ የሰውነት፣ የትምህርት፣ እናም ተጨማሪ አይነት ፈተናዎች ሊያጋጥሟቸው ይችላሉ። አንዳንድ ፍላጎቶች ከሌሎች በላይ ቀዳሚነት አላቸው ለአንዳንዶች እርዳታ ለመስጠት ችሎታዎች ይኖሩናል፤ ሌሎች የሌሎችን እንርዳታ እንድንፈልግ ያደርጉን ይሆናል። በጊዜአዊ የእርዳታ ፍላጎቶች ለመረዳት ስንጥር፣ ለማገልገል የተጠራንበት ሌሎችን በቃል ኪዳን መንገድ እንዲገፉ፣ ለከፍተኛነት አስፈላጊ ለሆኑት ለክህነት ስርዓቶች ለመዘጋጀት እና ለመቀበል መርዳትን እንደሚጨምርም አትርሱ።
ስለግለሰብ ወይም ቤተሰብ ፍላጎቶች ከመመካከር በተጨማሪም፣ የእነርሱን ጥንካሬ ለመማር መፈለግ ይገባናል። እርዳታ የማያስፈልጋቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? ሌሎችን ለመባረክ የሚችሉ ምን ችሎታዎች እና ስጦታዎች አሏቸው? የእግዚአብሔርን መንግስት ለመገንባት ለመርዳት ምን ልዩ ችሎታ አላቸው? የግለሰብ ጥንካሬን መረዳት እንደ እርሱ ወይም እርሷ ፍላጎት ለመረዳት አስፈላጊ ነው።
ከሰማይ አባት ጋር መመካከር
የእምንነታችን አንዱ መካከለኛ መሰረታዊ መመሪያ ቢኖር የሰማይ አባት ከልጆቹ ጋር እንደሚነጋገር ነው (የእምነት አንቀጾች 1፥9 ይመልከቱ)። አንድን ሰው እንድናገለግል አዲስ ሀላፊነት ስንቀበል፣ ስለፍላጎታቸው እና ጥንካሬአቸው አስተያየት እና መረጃ ለማግኘት ከሰማይ አባት ጋር በጸሎት መመካከር ይገባናል። ያም በጸሎት የመመካከር ሂደት ለማገልገል በተመደብንበት ጊዜ በሙሉ መቀጠል ይገባናል።
ከግለሰቦች እና ከቤተሰቦች ጋር መመካከር
ለማገልገል የተጠራናቸውን ግለሰቦችን እና ቤተሰቦችን እንዴት እና መቼ ልናነጋግራቸው የምንወስንበት በጉዳዮች ላይ የተመካ ነው፣ ነገር ግን ግንኙነቶችን ለመገንባትና ፍላጎታቸውን፣ እንዲሁም እንዴት ለመረዳት እንደሚፈልጉ፣ ለመረዳት ከግለሰብ ወይም ከቤተሰብ ጋር በቀጥታ መመካከር አስፈላጊ ነው። አንዳንድ ጥያቄዎች ትርጉም ያለው ግንኙነቶች እስከሚገነቡ ድረስ ለመቆየት ያስፈልጋቸው ይሆናል። ይህን ለማድረግ ምንም እንኳን አንድ መንገድ ባይኖርም፥ የሚቀጥሉትን አስቡበት፥
-
ስንት ጊዜ እና መቼ ከእነርሱ ጋር ግንኙነት እንዲደረግ እንደሚፈልጉ እወቁ።
-
እነርሱ ስለሚወዷቸው እና ስለእነርሱ ቀዳሚ ታሪክ ተማሩ።
-
እናንተ እነርሱን እንዴት እንደምትረዱ ሀሳቦችን አቅርቡ፣ እናም ስለእነርሱ ሀሳቦች ጠይቁ።
ታማኝነትን ስንገነባ፣ የግለሰብ ወይም የቤተሰብ ፍላጎቶችን ለመወያየት አስቡበት። በመንፈስ ቅዱስ የተነሳሱ ጥያቄዎችን ጠይቁ።1 ለምሳሌ፥
-
የሚያጋጥሟቸው ፈተናዎች ምን ናቸው?
-
የቤተሰብ ወይም የግለሰብ አላማዎች ምን ናቸው? ለምሳሌ፣ ደንበኛ የቤተሰብ የቤት ምሽት ለማድረግ፣ ወይም ራስን ቻይ በመሆን ለመሻሻል ይፈልጋሉ?
-
በአላማቸው እና በፈተናቸው እንዴት ልንረዳቸው እንችላለን?
-
ምን የወንጌል ስርዓቶች በህይወታቸው እየመጡ ናቸው? እነርሱን እንዴት ለመዘጋጀት ለመርዳት እንችላለን?
“በዚህ ሳምንት ውስጥ በየትኛው ምሽት ምግብ ልናመጣላችሁ እንችላለን?” እንደሚሉ አይነት እርዳታዎችን ለማቅረብ አስታውሱ። “ለማድረግ የምንችላቸው ማንኛዎች ነገሮች ካሉ ንገሩን?” የሚሉ አይነት የተለየ ያልሆኑ ጥያቄዎችን አታቅርቡ።
ከአገልግሎት ጓደኞቻችን ጋር መመካከር
እናንተ እና የአገልግሎት ጓደኛችሁ ከግለሰብ ወይም ከቤተሰብ ጋር በምትገናኙበት ጊዜ ሁልጊዜ አብራችሁ የማትገናኙ ስለምትሆኑ፣ እንደ አገልግሎት ጓደኞች መንፈሳዊ መነሳሻት ስትሹ አብራችሁ ማቀናበራችሁና መመካከራችሁ አስፈላጊ ነው። የሚቀጥሉት የምታስቡባቸው አንዳንድ ጥያቄዎች ናቸው፥
-
እንደ አገልግሎት ጓደኞች እንዴት እና ምን ያህል ጊዜ ትነጋገራላችሁ?
-
የግለሰብ ጥንካሬአችሁን የቤተሰብ ወይም የግለሰቦች ፍላጎቶች ለማገልገል ለመጠቀም እንዴት ትችላላችሁ?
-
ምን ነገሮች ተምራችኋል፣ ምን አጋጣሚዎች አላችሁ፣ እናም ስለግለሰብ ወይም ስለቤተሰብ በመጨረሻ ጊዜ በተነጋገራችሁበት ጊኤ ምን መንፈሳዊ መነሳሻዎች ተቀብላችኋል?
ከተመደቡ ሌሎች ጋር መመካከር
ከጊዜ ወደጊዜ እናንተ የምታገለግሏቸውን ግለሰብ ወይም ቤተሰብ ለማገልገል ከተመደቡት ጋር መነጋገራችሁ መልካም ነው።
ለፈተናዎች መፍትሄ ለማግኘት ተነጋገሩ
የሰባዎች አባል ሽማግሌ ጂ ሆንግ (ሳም) ዎንግ በጋራ መመካከር አራት ሰዎች በሽተኛ ሰውን በክርስቶስ ፊት ለማድረግ መንገድን እንዳገኙ በማሳየት የማርቆስ 2 ታሪክን ለአሁን ጊዜአቸን እንደምሳሌ ተተቀሙበት።
“እንደዚህ ሊሆን እችላል፣” አሉ ሽማግሌ ዋንግ። “አራት ሰዎች ከኤጲስ ቆጶሳቸው ሸባ የሆነውን አንድ ሰው በቤቱ እንዲጎበኙት ሃላፊነትን አገኙ። … በቅርብ በነበረ የአጥቢያ ሸንጎ ላይ፣ በአጥቢያ ውስጥ በእርዳታ ስለሚያስፈልጉት አብረው ከተመካከሩ በኋላ፣ ኤጲስ ቆጶስ ‘የማዳን’ መደቦችን ሰጠ። እነዚህ አራትም ይህን ሰው እንዲረዱ ተመደቡ። …
“[ኢየሱስ ባለበት ህንጻ አጠገብ ሲደርሱ፣] ስፍራም እስኪጠባቸው ድረስ ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ። በበር በኩል ለመግባት አልቻሉም። ለማሰብ የሚችሉትን ነገሮች ሁሉ እንደሞከሩ እርግጠኛ ነኝ፣ ነገር ግን ለመግባት አልቻሉም። … በሚቀጥለው ምን ማድረግ እንደሚገባቸው—ሰውየውን ወደ ክርስቶስ እንዲፈወስ እንዴት ለማምጣት እንደሚችሉ—ተመካከሩበት። … እቅድ ሰሩ—ቀላል አልነበረም፣ ነገር ግን በዚህ ሰሩ።
“… ‘እርሱ ያለበትን የቤቱን ጣራ አነሡ፣ ቀጥለውም ነድለውም ሽባው የተኛበትን አልጋ አወረዱ’ (ማርቆስ 2፥4)። …
“… ‘ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፣ አንተ ልጅ፥ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ አለው’ (ማርቆስ 2፥5)።”2
ለመስራት ግብዣ
የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ አባል ሽማግሌ ዲየተር ኤፍ. ኡክዶርፍ እንዳበረታቱት፣ “በጋራ መማከር፣ የተገኘውን ግብአት በሙሉ ተጠቀሙ፣ የመንፈስ ቅዱስን አመራር እሹ፣ ጌታን ለእርሱ ማረጋገጫ ጠይቁ እና ከዛ ሸሚዛችሁን ወደ ላይ ሰብስባችሁ ወደ ስራ ሂዱ።
“ቃል እገባላችኋለው፥ ይህን መንገድ ከተከተላችሁ በጌታ መንገድ ማንን፣ ምን፣ መቼ፣ እና የት እደምትለግሱ የተለየ አመራር ትቀበላላችሁ።”3
© 2018 በIntellectual Reserve, Inc. መብቶች ሁሉ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ. ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፥ 6/17 (እ.አ.አ)። ትርጉም የተፈቀደበት፥ 6/17 (እ.አ.አ)። Ministering Principles, September 2018 ትርጉም።አማርኛ። 15052 506