የአገልግሎት መሰረታዊ መርሆች፣ ጥቅምት 2018 (እ.አ.አ.)
ሌሎችን ለመርዳት እርዳታን ማግኘት
በአገልግሎት ጥረታችን እርዳታ ሲያስፈልገን እንዴት ሌሎች እንዲሳተፉ እናደርጋለን? በአገልግሎት ቃለ መጠይቅ ላይ እና በመጀመሪያ እሁድ የሸንጎ ስብሰባ ላይ ተሳተፉ።
ካቲ በውስጣዊ ብልቶች መጠንከር ምክንያት ታምማ በጋሪ ብቻ መሄድ እንድትችል ሲያደርጋት፣ ከጋሪዋ ወደ መኝታዋ ለመግባት በየምሽቱ እርዳታ እንደሚያስፈልጋት ተገነዘበች። ይህም ስራ ለአንድ አባል በጣም ትልቅ ነበር። ስለዚህ የሽማግሌዎች ሸንጎ ስለእርሷ ጉዳይ ተመካከሩ እናም በየምሽቱ እርሷን የሚረዱበት መርሀ ግብር አዘጋጁ።1
የምናገለግላቸውን ፍላጎት እና ጥንካሬ ስናውቅ፣ የእነርሱን ፍላጎት ለማሟላት እርዳታ እንደሚያስፈልገን ሆኖ እናገኘዋለን። የአገልግሎት ቃለ መጠይቅ ላይ እና የመጀመሪያ እሁድ ሸንጎ ስብሰባ ሌሎችን እንዴት በትክክል ለማሳተፍ ለመወያየት የሚቻሉበት ሁለት እድሎች ናቸው።
የአገልግሎት ቃለ መጠይቅ
በአገልግሎት እህቶችና በሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር ወይም በአገልግሎት ወንድሞችና በሽማግሌዎች ሸንጎ አመራር መካከል ያሉት እነዚህ በየሶስት ወር የሚሆኑ ቃል ጥያቄዎች ስለምናገለግላቸው በሚመለከት ማስገባት የሚያስፈልጉን መደበኛ የሆኑ ዘገባዎች ብቻ ናቸው። ቃል ጥያቄው በየሶስት ወሩ (1) ስለተመደቡት ቤተሰቦች ወይም ግለሰቦች ጥንካሬዎች፣ ፍላጎቶች፣ እና ፈተናዎች የመመካከር፤ (2) ሸንጎ፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር፣ ወይም የአጥቢያ ሸንጎ ለመርዳት ስለሚችሉበት የእርዳታ ፍላጎቶች ለመወሰን፤ እና (3) ከመሪዎች ለመማርና በአገልግሎት ጥረቶች ለመበረታታት የሚቻልበት እድል ነው።
የሽማግሌዎች ሸንጎ ፕሬዘደንት እና የሴቶች መረዳጃ ማህበት ፕሬዘደንት አስፈላጊ የእርዳታ ፍላጎቶችን በቀጥታ ወደ ኤጲስ ቆጶስ ያመጣሉ እናም ከእርሱም ምክርና መመሪያዎች ያገኛሉ።
ስለአገልግሎት ቃል ጥያቄ በministering.lds.org ውስጥ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ትችላላችሁ።
የአገልግሎት ቃለ መጠይቅን ትርጉም ያለው ማድረግ
ፕሬዘደንት ራስል ኤም.ኔልሰን የአገልግሎት ፕሮግራም ቤተክርስቲያኗ የምትወዛወዝበት ማጠፊያ ነው ያሉትን ለመደገፍ፣ የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ አባል ሽማግሌ ጌሪ ኢ. ስቲቨንሰን እንዳስተማሩት፣ “የዚህ የወደፊት ሀሳብን እውን መሆን … የሚመካው እንዴት የአገልግሎት ወንዶችና እህቶች በአገልግሎት ቃለ መጠይቅ በሚማሩበት እና በሚገናኙበት በኩል ነው።”2
ለአገልግሎት ወንድሞች እና እህቶች አምስት ጠቃሚ ምክሮች፥
-
ወደ ቃለ መጠይቁ ምክርን በመፈለግ ሂዱ። ለመማር የተዘጋጃችሁ ሁኑ።
-
ለማሟላት እርዳታ የሚያስፈልጋችሁን የእርዳታ ፍላጎትን ለመወያዩት ተዘጋጅታችሁ ሂዱ።
-
በግለሰብ የእርዳታ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን፣ በጥንካሪዎችና በችሎታዎች ላይ አተኩሩ።
-
አገልግሎታችሁ ውጤታማ መሆኑን የሚያሳይ ውጤትን ተመካከሩበት።
-
በየሶስት ወር ቃል ጥያቄዎች መካከል በሚያስፈልግበት ጊዜ ለመመካከር ከአመራር ጋር ተገናኙ።
ለመሪዎች አምስት ጠቃሚ ምክሮች፥
-
ቃለ መጠይቆች ረጅም መሆን አያስፈልጋቸውም፣ ነገር ግን ትርጉም ያለው ንግግር ለመደረግ በሚያስችል ቦታ ብቁ ጊዜ እንዲኖራችሁ አድርጉ።
-
የአገልግሎት ወንድም ወይም እህትን ለማገልገል እድል ይኑራችሁ።
-
(“አገልግሎታችሁን ፈጽማችኋል?”) የሚል አይነት ጉብኝትን ለመቁጠር ወይም ግንኙነትን ዝርዝር ለመሙላት እንደሚጣር የሚያስመስሉ ጥያቄዎችን አትጠይቁ? አስፈላጊ የሆነ ጸባይን የሚያጠናክሩ ጥያቄዎችን ጠይቁ (ለቤተሰብ ስትጸልዩ ምን መንፈሳዊ መነሳሻ ተሰምቷችኋል? በእነዚህ መንፈሳዊ መነሳሻዎች ስትሰሩ ምን ተከሰተ?)
-
በልባዊነትም አዳምጡ እናም ማስታወሻን ያዙ።
-
አብራችሁ ተመካከሩ። የአገልግሎት ጓደኞች እንዲያገለግሉ ለተመደቡት ሰዎች ራዕይ ለመቀበል መብት አላቸው።
ስለአገልግሎት ቃለ መጠይቅ ጥያቄዎች እና መልሶች
የአገልግሎት ቃለ መጠይቅ ምንድን ነው?
ይህም በአገልግሎት ወንድሞች እና በሽማግሌዎች ሸንጎ አመራር መካከል ወይም በአገልግሎት እህቶች እና በሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር አባል መካከል በመንፈስ ቅዱስ በኩል መንፈሳዊ መነሳሻ ለመፈለግና ለመቀበል በሚያስችላቸው ቦታ የሚከናወን ውይይት ነው። በዚህም የተነሳ፣ የአገልግሎት ወንድሞች እና እህቶች በአዳኝ መንገድ ለመጠበቅ፣ ለማፍቀር፣ ለማስተማር፣ እና ለማፅናናት በመንፈስ ለመነሳሳት ይችላሉ።
እነዚህ የየሶስት ወር ቃል ጥያቄዎች በአካል መፈጸም ይገባቸዋልን?
በልምድ እነዚህ የሚፈጸሙት በአካል ናቸው፣ ነገር ግን ፊት ለፊት መገናኘት የማይቻል ሲሆን፣ እነዚህ በስልክ ወይም በኢንተርኔት መፈጸም ይችላሉ። በአጠቃላይ፣ አስፈላጊ ሲሆን ሁለቱም የአገልግሎት ጓደኞች በቃል ጥያቄው ይሳተፉ።
የአገልግሎት ቃል ጥያቄ አላማ ምንድን ነው?
የአገልግሎት ቃል ጥያቄዎች የአገልግሎት ወንድሞች እና እህቶች የአሁን ጉዳዮችን የሚገመግሙበት፣ የወደፊት እቅድ የሚሰሩበት፣ እና ለሚያገለግሏቸው ግለሰቦች ወይም ቤተሰቦች የሚያስፈልጋቸውን እርዳታ የሚያገኙበት እድል ነው። ሸንጎ እና የሴቶች መረዳጃ ማህበት ለመስጠት የሚችሉትን ምንጭ የሚነጋገሩበት እድል ነው።
ስለሚስጥራዊ ጉዳዮች ምን አደርጋለሁ?
የአገልግሎት ወንድሞች እና እህቶች ሚስጥራዊ መረጃዎችን ከሽማግሌዎች ቡድን ወይም ከሴቶች መረዳጃ ማህበት ፕሬዘደንት ጋር ብቻ—ወይም በቀጥታ ከኤጲስ ቆጶስ ጋር ብቻ ነው የሚካፈሉት። ሚስጥራዊ መረጃዎች በመጀመሪያ እሁድ የሸንጎ ስብሰባዎች ውስጥ መወያይት አይገባቸውም።
የመጀመሪያ እሁድ ሸንጎ ስብሰባዎች
ከአገልግሎት ቃል ጥያቄዎች በተጨማሪ፣ የመጀመሪያ እሁድ ሸንጎ ስብሰባዎች ሌሎችን በአገልግሎት የምታሳትፉበት ሌሎች መንገዶች ናቸው። በሴቶች መረዳጃ ማህበር እና በሽማግሌዎች ሸንጎ ስብሰባዎች ውስጥ፣ በዚያ ለሚገኙት በመንፈስ በኩል እና በቡድኑ በሚገኙ ሌሎች መንፈሳዊ መነሳሻ ለመምጣት ይችላል።
የሸንጎ ስብሰባ እቅድ የሚቀጥለው ነው፥
-
“ስለክልል ሀላፊነቶች፣ እድሎች፣ እና ፈተናዎች አብሮ ለመመካከር፤
-
“ከእርስ በራስ አስተያየት እና አጋጣሚዎች ለመማር፤ እና
-
“ከመንፈስ በሚመጣው መነሳሻ የመስራት መንገዶችን ለማቀድ።”3
የሸንጎ ስብሰባዎች ከውይይቶች በላይ ናቸው፥ ስብሰባዎች እንደ ግለሰብ እና እንደ ቡድን በመንፈስ በምንነሳሳበት እንድንሰራ ይመሩናል። አባላት በእነዚህ ስብሰባዎች ምክንያት የጌታን ስራ ለመፈጸም ፍላጎት ሊሰማቸው ይችላሉ።
ለመስራት ግብዣ
የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ አባል ሽማግሌ ጄፍሪ አር. ሆላንድ እንዳሉት፣ “ዛሬ ጸሎታችን እያንዳዱ ወንድ እና ሴት ሰው—እና ወጣት ወንዶቻችን እና ሴቶቻችን—በክርስቶስ ንጹህ ፍቅር ብቻ ተነሳስተው ለእርስ በራስ በልብ ስሜት ያለው እንክብካቤ ለማድረግ ጥልቅ ውሳኔ እንዲኖራቸው ነው።4
© 2018 በIntellectual Reserve, Inc. መብቶች ሁሉ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ. ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፥ 6/17 (እ.አ.አ.)። ትርጉም የተፈቀደበት፥ 6/17 (እ.አ.አ.)። Ministering Principles, October 2018 ትርጉም።Amharic. 15053 506