2019 (እ.አ.አ)
አገልግሎታችንን የሚቀይረው አላማ
ጥር 2019 (እ.አ.አ)


ministering

የአገልግሎት መሰረታዊ መርሆች፣ ጥር 2019 (እ.አ.አ.)

አገልግሎታችንን የሚቀይረው አላማ

በአገልግሎት ጥረት ብዙ አላማዎች ቢኖሩም፣ ጥረቶቻችን ሌሎች ጥልቅ የሆነ የግል ቅያሬ እንዲኖራቸው እና እንደ አዳኝ ለመሆን ተጨማሪ ፍላጎት እንዲኖራቸው ለመርዳት ባለን ፍላጎት መመራት ይገባቸዋል።

አዳኝ እንደሚያደርገው ሌሎችን ስናፈቅር፣ እርሱ እንደሚያደርገው ልንረዳቸው እንፈልጋለን። እንደ መልካም እረኛው፣ ትርጉም ያለው አገልግሎት ምሳሌ ነው።

የእኛን አገልግሎት እንደእርሱ አይነት በማድረግ፣ እርሱ ለማፍቀር፣ ከፍ ለማድረግ፣ ለማገልገል፣ እና ለመባረክ ያለውን ጥረት ወዲያው የሚያስፈልገውን እርዳታ ከማሟላት በላይ ታላቅ እቅድ እንደነበርው ማስታወሳችን አስፈላጊ ነው። በእርግጥም የቀን ለቀን ፍላጎታቸውን ያውቅ ነበር እናም በጊዜው ለነበራቸው ስቃይም ርህራሄ ተሰምቶታል። ስለዚህ እርሱ ፈወሳቸው፣ መገባቸው፣ ይቅርታ ሰጣቸው፣ እናም አስተማራቸው። ነገር ግን የዚያን ቀን ጥማት ከማርካት በላይ ለማድረግ ፈለገ (ዮሀንስ 4፥13–14 ይመልከቱ)። በክቡ ያሉት እንዲከተሉት (ሉቃስ 18፥22ዮሀንስ 21፥22 ይመልከቱ)፣ እንዲያውቁት (John 10:14; ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥22–24 ይመልከቱ)፣ እና መለኮታዊ ችሎታቸውን እንዲደርሱበት (ማቴዎስ 5፥48 ይመልከቱ) ፈለገ። ዛሬ እንዲሁም እውነት ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 67፥13 ይመልከቱ)።

ሌሎችን ለመባረክ የምንችልባቸው ብዙ መንገዶች አሉ፣ ነገር ግን የአገልግሎታችን መጨረሻ አላማ ሌሎች አዳኝን እንዲያውቁ እና እንደእርሱ እንዲሆኑ ለመርዳት ነው፣ ሁላችንም እርሱን ስለምናውቅ ጎረቤቶቻችንን ጌታን እዲያውቁ ማስተማር ወደማያስፈልገን ቀን እንሄዳለን (ኤርምያስ 31፥34 ይመልከቱ)።

የአዳኝ ትኩረት ወዲያው ከሚያስፈልገው በላይ ነው

  • አንዳንድ ግለሰቦች ሽባ ጓደኛቸው እንዲፈወስ ወደ ኢየሱስ ለማምጣት ታላቅ ጥረት አድርገው ነበር። በመጨረሻም አዳኝ ሰውየውን ፈወሰው፣ ነገር ግን እርሱን ከኃጢያቱ ለመሰረይ ከሁሉም በላይ ፈልጎ ነበር (ሉቃስ 5፥18–26 ይመልከቱ)።

  • ሰዎች ወደ አዳኝ በማመንዝር የተያዘችን ሴት ባመጡለት ጊዜ፣ እርሷን አለመኮነኑ በሰውነት ህይወቷን አዳነላት። “ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ” በማለት ግን በመንፈስ ሊያድናትም ፈልጎ ነበር (ዮሀንስ 8፥2–11 ይመልከቱ)።

  • ማርያም እና ማርታ ኢየሱስ ጓደኛውን አልዓዛርን እንዲፈውስ መልእክት ላኩለት። ሌሎችን በብዙ ጊዜ የፈወሰው ኢየሱስ አልዓዛር እስኪሞት ድረስ መምጣቱን አዘገየ። ኢየሱስ ቤተሰቦች ምን እንደፈለጉ ያውቅ ነበር፣ ነገር ግን አልዓዛርን ከሞት በማስነሳት፣ የመለኮታዊነቱን ምስክርነታቸውን አጠናከረ (ዮሀንስ 11፥21–27 ይመልከቱ)።

በዚህ ዝርዝር ላይ ምን ሌሎች ምሳሌዎች ለመጨመር ትችላላችሁ?

እኛ ምን ማድረግ እንችላለን?

እቅዳችን ሌሎች እንደ አዳኝ እንዲሆኑ ለመርዳት ከሆነ፣ የምናገለግልበትን ይቀይራል። ይህን መረዳት በምናገለግልበት ጥረት ልንመራ የምንችልባቸው አንዳንድ መንገዶች የሚቀጥሉት ናቸው።

ሀሳብ 1፥ አገልግሎትን ከአዳኝ ጋር አገናኙ

መልካም ለማድረግ የምንጥርበት ሁሉ ጠቃሚ ነው፣ ነገር ግን አገልግሎታችንን ከአዳኝ ጋር በማገናኘት ለማጉላት እድሎችን ለመፈለግ እንችላለን። ለምሳሌ፣ የምታገለግሏቸው ቤተሰብ ከታመሙ፣ ምግብ እርዳታ የሚሰጥ ይሆናል፣ ነገር ግን አዳኝ ለእነርሱ ስላለው ፍቅር በመመስከር የእናንተ ቀላል የፍቅር መግለጫን ለማባዛት ትችላላችሁ። በሜዳ ስራ መርዳታችሁ ምስጋና ያለው ነው፣ ነገር ግን የክህነት በረከትን በማቅረብ ይህን ተጨማሪ ትርጉም እንዲኖረው ለማድረግ ይቻላል።

የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ምልዓተ ጉባኤ አባል ሽማግሌ ኒል ኤል. አንደርሰን እንዳስተማሩት፣ “መልካም ልብ ያለው ሰው ጎማን ለመጠገን ለመርዳት፣ አብሮ የሚኖሩትን ወደ ሀኪም ለመውሰድ፣ ከተከፋ ሰው ጋር ወደ ምሳ ለመሄድ፣ ወይም ቀኑን ለማብራት ፈገግ ወይም ሰላም ለማለት ይቻላል።

ነገር ግን የመጀመሪያው ትእዛዝ ተከታይ በእነዚህ አስፈላጊ የአገልግሎት ስራዎች ላይ ተጨማሪ ያደርጋል።”1

ሀሳብ 2፥ በቃል ኪዳን መንገድ ላይ አትኩር

እንደ ቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንት ለአባላት ለመጀመሪያ ጊዜ በተናገሩበት ጊዜ፣ ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዲህ አሉ፣ “በቃል ኪዳን መንገድ ላይ ሁኑ።” ቃል ኪዳኖችን መግባት እና ማክበር “ለእያንዳንዱ መለኮታዊ በረከቶች እና መብቶች በርን ይከፍታል።”2

እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን፣ ተጠምቀናል፣ ተረጋግጠናል፣ እናም የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ተቀብለናል። ብቁ የሆኑ ወንድ አባላትም ክህነትን ተቀብለዋል። ለመንፈሳዊ በረከታችን እና እንደ ቤተሰብ ለዘለአለም ለመተሳሰር ወደ ቤተመቅደስ እንሄዳለን። ከእርሱ ጋር ለመኖር እንድንችል ዘንድ እነዚህ የሚያድኑ ስርዓቶች እና ከእነዚህ ጋር የተያያዙ በረከቶች እንደ እርሱ ለመሆናችን አስፈላጊ ናቸው።

ሌሎች ቃል ኪዳኖቻቸውን እንዲጠብቁ እና የወደፊት ቃል ኪዳኖች ለመግባት እንዲዘጋጁ ስንረዳ፣ እነርሱን በመንገዱ በመርዳት የምናደርጋቸው አስፈላጊ ክፍሎች አሉን።3 የምታገለግሏቸውን ግለሰቦች ወይም ቤተሰቦች የሚቀጥለውን ስራአት እንዲቀበሉ እንዴት ለመርዳት ትችላላችሁ? ይህም አባት ሴት ልጁን እንዲያጠምቅ ለማዘጋቸት መርዳት፣ በሚቀጥለው የሚገቡት ቃል ኪዳን ምን እንደሆነ መግለጽ፣ ወይም ቅዱስ ቁርባንን ስንቀበል ቃል ኪዳኖቻችንን የምናሳድስበት ትርጉም ያለው አጋጣሚዎችን መካፈል ሊሆን ይችላል።

ሀሳብ 3፥ ጋብዙ እናም አበረታቱ

ትክክለኛ በሚሆንበት ጊዜም፣ የምትንከባከቧቸውን ስለመቀየር እና እንደ ክርስቶስ አይነት ስለመሆን ጥረቶች ምከሯቸው። በእነርሱ ስለምታዩት እና ስለምትገረሙበት ጥንካሬ ንገሯቸው። የት ለመሻሻል እደሚችሉ እንደሚሰማቸው ለማወቅ ፈልጉ እናም እናንተ እንዴት ለመርዳት እንደምትችሉም ተነጋገሩበት። (ከምታገለግሏቸው ጋር አብሮ ስለመመካከር ተጨማሪ ለማግኘት፣ “ስለፍላጎቶቻቸው ተመካከሩ፣” Liahona, መስከረም 2018 (እ.አ.አ), 6–9 ይመልከቱ።)

አዳኝን እንዲከተሉ ለመጋበዝ አትፍሩ እናም መለኮታዊ ችሎታቸውን እንዲያገኙም እርዳታ ስጧቸው። በእነርሱ ላይ ያላችሁን እምነት እና በእርሱ ካላችሁ እምነት ጋር ሲጣመር፣ ይህም ግብዣ ህይወት የሚቀይር ሊሆን ይችላል።

ሌሎችን ወደ ክርስቶስ እንዲሄዱ ለመርዳት የምንችልበት ስድስት መንገዶች

የሚቀጥሉት ሌሎች የህይወት መሻሻል የሚያደርጉበትን እና በቃል ኪዳን መንገድ የሚገፉበትን ለመደገፍ በሀሳብ የሚቀርቡ ናቸው። (ለተጨማሪ ሀሳቦች Preach My Gospel, chapter 11 ይመልከቱ።)

  1. ተካፈሉ። ውድቀትም ቢኖር በወንጌል መርሆች በመኖር ወደ እርሱ ለመቅረብ በምትሞክሩበት ጊዜ አዳኝ እንዴት እንደረዳችሁ በምትካፈሉበት እውነተኝ እና ደፋር ሁኑ።

  2. ቃል የተገቡ በረከቶች ሰዎች ላለመቀየር ካለ ምክንያት በላይ የሚገፋፉበት የመቀየር ምክንያት ይፈልጋሉ። ከስራ ጋር የተያያዙትን በረከቶች መግለጽ ሀይለኛ መገፋፊያ ይሰጣል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130፥20-21 ይመልከቱ)።

  3. ግብዣ ይስጡ በወንጌል መርሆች መኖር እውነት እንደሆነ ምስክርን ያመጣል (ዮሀንስ 7፥17) እናም ወደ ጥልቅ ቅያሬ ይመራል።4 እያንዳንዱ ጉብኝቶች ወደ ፊት እንዲገፉ የሚረዳቸው ቀላል ግብዣዎች ሊኖሩባቸው ይችላሉ።

  4. አብራችሁ አቅዱ። ለመቀየር ቃል የገቡበትን በውጤታማነት ለመጠበቅ ምን እንዲደርስላቸው ያስፈልጋቸዋል? እናንተ እንዴት ለመርዳት ትችላላችሁ? ከዚህ ጋር የተያያዘ የጊዜ ግዴታ አል?

  5. ደግፉ። እርዳታ የሚሰጥ ሲሆን፣ ግለሰቡ እንዲገፋፋ እና ውጤታማ እንዲሆን የሚረዳ የድገፋ ቡድን ሰብስቡ። ሁላችንም የሚገፋፉን ያስፈልጉናል።

  6. ተከታተሉ። ወደፊት የሚገፉበትን ተከፋፈሉ። በእቅዱ ላይ ትኩረት አድርጉ ነገር ግን አስፈላጊ ሲሆንም አሻሽሉት። ትእግስተኛ፣ ተከታታይ፣ እና የሚያበረታታ ሁኑ። ለውጥ ጊዜ ይፈጃል።

ለመስራት ግብዣ

ትልቅም ይሁን ትንሽ፣ የማገልገል ጥረታችሁ ሌሎች ጥልቅ የሆነ የግል ቅያሬ እንዲኖራቸው እና እንደ አዳኝ ለመሆን ተጨማሪ ፍላጎት እንዲኖራቸው ለመርዳት የምትችሉበትን መንገዶች አስቡ።

ማስታወሻዎች

  1. Neil L. Andersen, “A Holier Approach to Ministering” (Brigham Young University devotional, Apr. 10, 2018), 3, speeches.byu.edu.

  2. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ወደፊት አብረን ስንገፋ፣” Liahona፣ ሚያዝያ፣ 2018 (እ.አ.አ)፣ 7።

  3. ሔንሪ ቢ. አይሪንግ፣ በቃል ኪዳን ውስጥ ያሉ ሴት ልጆች፣” Liahona፣ ግንቦት 2014 (እ.አ.አ)፣ 125–28።

  4. ዴቪድ ኤ.ቤድናር፣ “Converted unto the Lord፣” Liahona፣ Nov. 2012፣ null109።