2019 (እ.አ.አ)
ምስክርነትን በቀላሉ ለማካፈል እንዴት እንደሚቻል
መጋቢት 2019 (እ.አ.አ)


ምስል
ministering

የአገልግሎት መሰረታዊ መርሆች፣ መጋቢት 2019 (እ.አ.አ.)

ምስክርነትን በቀላሉ ለማካፈል እንዴት እንደሚቻል

አገልግሎት መመስከር ነው። የአገልግሎት ተለዋዋጭነት መደበኛ በሆኑ ወይም ባልሆኑ መንገዶች ምስክርነታችንን ለማካፈል ያሉንን እድሎች ለማሳደግ ይችላሉ።

“በሁሉም ጊዜ በሁሉም ነገርና፣ የእግዚአብሔር ምስክር በመሆን [ለመቆም]” (ሞዛያ 18፥9) ቃል ኪዳን ገብተናል። ምስክርነቶቻችንን ማካፈልም እንደ ምስክር የመቆም ክፍል እናም መንፈስ ቅዱስ የአንድ ሰውን ልብ እዲነካ እና ህይወታቸውን እንዲቀይር የሚጋበዝበት ሀይለኛ መንገድ ነው።

የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ጉባኤ ጊዜአዊ ፕሬዘዳንት ኤም. ራስል ባለርድ እንዳሉት፣ “ምስክርነት—በመንፈስ የተሰጠ እና በመንፈስ ቅዱስ የተረጋገጠ እውነተኛ ምስክርነት—ህይወቶችን ይቀይራል።” 1

ነገር ግን ምስክረነታችንን ማካፈል ለአንዳንዳችን ምቾት የሌለው ወይም የሚያስፈራ ሊሆን ይችላል። የዚህም ምክንያት ምስክርነትን የምንሰጠው በጾም እና ምስክርነት ጊዜ ወይም ትምህርትን በምናስተምርበት ጊዜ ብቻ ነው ብለን ስለምናስብ ነው። በእነዚህ መደበኛ በሆኑ ሁኔታዎች በአብዛኛው ጊዜ በየቀኑ ንግግሮች ለመጠቀም የማይመች የሆኑ አንዳንድ ቃላቶችን እና ሀረጎችን እንጠቀማለን።

በየቀኑ ሁኔታዎች ይህን ለማካፈል እንዴት ቀላል እንደሆነ ስንረዳ፣ ምስክርነቶቻችንን ማካፈል በህይወታችንና በሌሎች ህይወቶች ውስጥ ሁልጊዜ የሚገኙ በረከቶች ለመሆን ይችላሉ። እንዲያስጀምራችሁ የሚረዱ ጥቂት ሀሳቦች እነዚህ ናቸው።

ቀላል አድርጉት

ምስክርነት “እኔ ምስክሬን ለመስጠት እፈልጋለው” በሚለው ሀረግ መጀመር አያስፈልገውም፣ እናም “በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን” በሚለው መፈጸው አያስፈልገውም። ምስክርነት የምናምንበት እና እውነት እንደሆነ የምናውቀው የሚገለፅበት ነው። ስለዚህ ችግር ካላት ጎረቤታችሁ ጋር በመንገድ መገናኘት እና “እግዚአብሔር ጸሎቶችን እንደሚመልስ አውቃለህ” ማለት፣ በቤተክርስቲያን መስበኪያ ላይ እንደሚደረገው አይነት ሀይለኛ ምስከርነት ለመሆን ይችላል። ይህም ሀይል የሚመጣው አበባዊ በሆኑ ንግግሮች አይደለም፤ ይህም የሚመጣው መንፈስ ቅዱስ በሚያረጋግጠው እውነት ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 100፥7–8 ይመልከቱ)።

የየቀኑን ንግግር አካሄድ ጋር አስማሙት

ለማካፈል ፈቃደኛ ከሆንን፣ በየቀኑ ንግግራችን ውስጥ ምስክርነትን ለማስማማት በአካባቢያችን ሁሉ እድሎች አሉ። ለምሳሌ፥

  • አንድ ሰው ስለሳምንት መጨረሻችሁ ይጠይቋችኋል። “መልካም ነበር፣” ብላችሁ ትመልሳላችሁ። “ቤተክርስቲያን ልክ የሚያስፈልገኝ ነበር።”

  • አንድ ሰው በህይወታችሁ ስላለው ፈተና በሚያውቁ ጊዜ ሀዘናቸውን በመግለጽ “ይቅርታ” ይላሉ። እናንተም እንዲህ ትመልሳላችሁ፥ “ለሀሳብህ አመሰግናለሁ። እግዚአብሔር እንደሚረዳኝ አውቃለሁ። ከዚህ በፊት ለእኔ እርዳታ ሰጥቶኛልና።”

  • አንደ ሰው እንዲህ ይላል፥ “ይህ መጥፎ የአየር ሁኔታ በቅርብ እንደሚለወጥ ተስፋ አለኝ፣” ወይም “ይህን የመኪና መጨናነቅ ተመልከት።” እናንተም እንዲህ ትመልሱ ይሆናል፥ “እግዚአብሔር ሁሉም እንዲስተካከል እንደሚያደርግ እርግጠኛ ነኝ።”

ተሞክራችሁን አካፍሉ

በአብዛኛው ጊዜ ስለፈተናዎቻችን እርስ በራስ እንነጋገራለን። ሰው ምን እንደሚያጋጥማቸው በሚነግሯችሁ ጊዜ፣ እናንተን በፈተናችሁ ግዜ እንዴት እግዚአብሔር እንደረዳችሁ ለማካፈል እና እነርሱን ለመርዳት እንደሚችል እንደምታውቁ ለመመስከር ትችላላችሁ። ጌታ እንዳለው፣ በፈተናችን የሚያጠናክረን “ከዚህ በኋላ ለእኔ በምስክርነት እንድትቆሙ ነው፤ እናም እኔ ጌታ እግዚአብሔር በእውነት በመከራቸው ጊዜ ህዝቤን እንደምጎበኝ ታውቁ ዘንድ ነው።” (ሞዛያ 24፥14)። በፈተናችን እንዴት እንደረዳን ስንመሰክር ለእርሱ ምስክሮች በመሆን ለመቆም እንችላለን።

ተዘጋጁ

ለአንዳንዳችን፣ ምስክርን በማንኛውም ጊዜ ማካፈል የሚያስፈራ ይሆናል። ወደፊት ለማቀድ የምንችልባቸው መንገዶች አሉ እናም “[በእኛ] ስላለ ተስፋ ምክንያትን [ለሚጠይቁን] ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር [የተዘጋጀን እንሁን]” (1 ጴጥሮስ 3፥15)።

መጀመሪያ፣ መዘጋጀት ማለት እንዴት እንደምንኖር መመልከት ሊሆን ይችላል። መንፈስ ቅዱስን ወደ ህይወታችን ውስጥ እየጋበዝን እና በጽድቅ ህይወት በኩል የራሳችንን ምስክርነቶች በየቀኑ እያጥናከርን ነን? መንፈስ እንዲያነጋግረን እና በጸሎት እና በቅዱስ መጻህፍት ጥናት በኩል የሚያስፈልገንን ቃላት እንዲሰጠን እድል እየሰጠነው ነን? ጌታ ሀይረም ስሚዝን እንደመከረ፣ “ቃሌን ለማወጅ አትፈልግ፣ ነገር ግን አስቀድመህ ቃሌን ለማግኘት ፈልግ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11፥21)።

ሁለተኛ፣ መዘጋጀት ማለት አስቀድሞ መመልከት እና በዚያ ቀን ወይም በዚያ ሳምንት ምስክራችሁን ለማካፈል ስለነበራችሁ እድሎች ስለማሰብም ለመሆን ይችላል። ለእነዚያ እድሎችም ስለምታምኗቸው ለማካፈል እድል ሲኖራችሁ ምን እንደምትካፈሉ በማሰብ ለመዘጋጀትም ትችላላችሁ።

በአዳኝ እና በትምህርቱ ላይ ያተኮራችሁ ሁኑ

ፕሬዘደንት ባለርድ እንዳስተማሩት፣ “እንደቤተክርስቲያኑ አባላት ስለብዙ ነገሮች ብዙ ምስክርነቶች ቢኖሩንም፣ ሁልጊዜም እርስ በራስ ለማስተማር እና ለማካፈል የሚያስፈልጉን ዋና እውነቶች አሉ።” እንደ ምሳሌም፣ እነዚህን ዘረዘሩ፥ “እግዚአብሔር አባታችን እና ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የደህንነት እቅድ የአዳኝ የኃጢያት ክፍያ ዋና ክፍል ነው። ጆሴፍ ስሚዝ የኢየሱስ ክርስቶስ የዘለአለም ወንጌልን ሙሉነት በዳግም መልሷል፣ እናም መፅሐፈ ሞርሞን ምስክራችን እውነት እንደሆነ መረጃ ነው። እነዚህን ከልብ ከመነጩ እወነቶች ስንገልፅ፣ ያልነው እውነት እንደሆኑ እንዲመሰክር መንፈስን እንጋብዛለን። ፕሬዘደንት ባለርድ እንዲህ በማለት ትኩረት ሰጥተዋል “የክርስቶስ ንጹህ ምስክርነት ሲሰጥ መንፈስን ለመገደብ አይቻልም።” 2

የአዳኝ ምሳሌ

በሰማርያ ውስጥ ከጉዞው ደክሞ፣ ኢየሱስ በውሀ ጉድጓድ አጠገብ አረፈ እና አንድ ሴትን በዚያ አገኘ። ውሀን ከጉድጓዱ ውስጥ ስለማውጣት ንግግር ጀመረ። በየቀኑ ሴቷ የምታደርገው ስራ በእርሱ በኩል ለሚያምኑት ሁሉ ስለሚገኘው ህያው ውሀ እና ዘለአለም ህይወት ምስክርን ለመስጠት ለኢየሱስ እድል አቀረበለት (ይኦሀንስ 4፥13–15፣ 25–26 ይመልከቱ)።

ቀላል ምስክርነት ህይወቶችን ለመቀየር ይችላሉ

ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን አንድ ነርስ ዶክተር ኔልሰንን ስለ አስቸጋሪ የቀዶ ጥገና ሂደት ስለጠየቀቻቸው ጥያቄ ተናግረው ነበር። “እንደ ሌሎቹ ቀዶ ጠጋኞች ለምን አንተ አይደለህም?” የምታውቃቸው አንዳንድ ቀዶ ጠጋኞች ከባድ ተጽዕኖ ባለቸው ሂደቶች ላይ ሲሰሩ ቁጠኛ እና የሚሳደቡ ነበሩ።

ዶክተር ኔልሰን በተለያዩ መንገዶች ለመመለስ ይችሉ ነበር። ግን እንዲህ በማለት በቀላል መለሱ፣ “መፅሐፈ ሞርሞን እውነት መሆኑን ስለማውቅ ነው።”

ይህ መልስ ነርሷ እና ባለቤቷ መፅሀፈ ሞርሞንን እንዲያጠኑ ገፋፋቸው። ፕሬዘዳንት ኔልሰን በኋላም ነርሷን አጠመቋት። ከብዙ አመታት በኋላ፣ በተነሲ፣ ዩ.ኤስ. ኤ. ውስጥ የካስማ ጉባኤን ሲያካሂዱ፣ እንደ አዲስ ሐዋርያ የተሾሙት ፕሬዘደንት ኔልሰን ከዚያች ነርስ ጋር ይጠብቁት ባልነበረ ግንኙነትን ተደሰቱ በእርሳቸው ቀላል ምስክርነት የተገፋፋው ቅያሬዋን ታሪክ እና የመፅሐፈ ሞርሞን ተፅዕኖ ሌላ 80 ሰዎች እንዲቀየሩ እንደረዳም ተናገረች።3

ለመስራት ግብዣ

ምስክርነታችሁን ለማካፈል አትፍሩ። የምታገለግሏቸውን ለመባረክ ይችላል። እነዚህን ወይም የራሳችሁን ሀሳቦች ዛሬ ምስክርነታችሁን ለመካፈል እንዴት ትጠቀሙበታላችሁ?

ማስታወሻዎች

  1. M. Russell Ballard, “Pure Testimony,” Liahona, Nov. 2004, 40.

  2. M. Russell Ballard, “Pure Testimony,” 41.

  3. In Jason Swensen, “Be Ready to Explain Your Testimony Using the Book of Mormon, President Nelson Says,” Church News section of LDS.org, Feb. 6, 2018, news.lds.org.

አትም