2019 (እ.አ.አ)
አገልግሎትን አስደሳች ማድረግ
ሚያዝያ 2019 (እ.አ.አ)


ምስል
ministering

የአገልግሎት መሰረታዊ መርሆች፣ ሚያዝያ 2019 (እ.አ.አ.)

አገልግሎትን አስደሳች ማድረግ

በፍቅር ማገልገል ለሚሰጠው እናም ለሚቀበለው ደስታን ያመጣል።

አንዳንድ ጊዜ በዚህ ህይወት የምንፈልግው ደስታ በአስለቺ የእለት ተእለት ተግባር እንደመሯሯጥ ነው። እንሯሯጣለን እናም የትም እንደማንደርስ ያህል ይሰማናል። ለአንዳንድ ሰዎች፣ ሌሎችን ማገልገል ሌላ የሚያደርጉት እንደሚጨመርባቸው ይሰማቸዋል።

ነገር ግን የሰማይ አባታችን ደስታ እንድንለማመድ ይፈልገናል እናም “ሰዎች የሚኖሩትም ደስታም እንዲኖራቸው ዘንድ ነው” (2 ኔፊ 2፥25) ብሎ ነግሮናል። አዳኝም ሌሎችን ማገልገል ለህይወታችን እና ለሌሎች ህይወት ደስታ የምናመጣበት ዋና ክፍል እንደሆነ አስተምሮናል።

ደስታ ምንድን ነው?

ደስታ “ታላቅ የእርካታ እና የሃሴት ስሜት” 1 የሚል ትርጉም አለው። የኋለኛው ቀን ነቢያት ደስታ ከየት እንደሚመጣ እና እንዴት እንደሚገኝ መግለጫ ሰጥተውናል። ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “የሚሰማን ደስታ በህይወታችን ካለንበት ጉዳይ ትንሽ ግንኙነት አለው እናም በህይወታችን ትኩረት ላይ ሁሉም ትኩረት አለው” ብለዋል። “… ደስታ [በኢየሱስ ክርስቶስ] ምክንያት ይመጣል። እሱ የደስታ ሁሉ ምንጭ ነው።”2

አገግሎት ደስታን ያመጣል

ሌሂ የህይወት ዛፍ ፍሬ ሲበላ፣ ነፍሱ “በታላቅ ደስታ” (1 ኔፊ 8፥12) ተሞላ። የመጀመሪያው ፍላጎቱ ይን ፍሬ ከሚያፈቅራቸው ጋር ለመካፈል ነበር።

ሌሎችን ለማገልገል ያለን ፍላጎት እንዲህ አይነት ደስታ ለእኛና ለእነርሱም ለማምጣት ይችላል። ከእርሱ ጋር የተገናኘን ስንሆን የምናመጣው ፍሬ የደስታ ሙላት ለማምጣት እንደሚረዳን አዳኝ ደቀመዛሙርቱን አስተምሯል (ዮሀንስ 15፥1–11 ይመልከቱ)። በማገልገል እና ሌሎችን ወደ እርሱ ለማምጣት በመፈለግ የእርሱን ስራ ማከናወን የደስታ ልምምድ የሚሰጥ ሊሆን ይችላል (ሉቃስ 15፥7አልማ 29፥9ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥1650፥22 ይመልከቱ)። ይህን ደስታ በቅዋሜ እና በስቃይ መካከልም ሊሰማን እንችላለን (2 ቆሮንጦስ 7፥4ቄላስዮስ 1፥11 ይመልከቱ)።

አዳኝ በዚህች ጊዜአዊ ህይወት ውስጥ ታላቅ የእውነት ደስታ ምንጭ የሚገኘው በአገልግሎት በኩል እንደሆነ አሳይቶናል። አዳኝ እንዳደረገው እኛም በልባችን ውስጥ ልግስና እና ፍቅር በመሞላት ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ስናገለግል፣ ከቀላል ከደስታ በላይ የሆነ ሃሴት ሊሰማን እንችላለን።

“[አገልግሎትን] በፈቃደኛ ልብ ስንቀበል፣ የፅዮን ሰዎች ለመሆን እየቀረብን እንመጣለን እናም የሚደንቅ ደስታ ከእነኛ በደቀመሙርትነት መንገዳቸው ላይ ከረዳናቸው ጋር ይሰማናል” ብለው የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት እህት ጂን ቢ. ቢንገም አስተምረዋል።3

አገልግሎትን እንዴት በተጨማሪ አስደሳች ለማድረግ እንችላለን?

ወደ አገልግሎታችን ታላቅ ደስታን የማምጣት ብዙ መንገዶች አሉ። እነዚህም ጥቂት ሀሳቦች ናቸው፥

  1. የአገልገሎት አላማችሁን ይረዱ። ለማገልገል ብዙ ምክንያቶች አሉ። በመጨረሻም፣ ጥረቶቻችን “የሰውን ህያውነት እና ዘለአመማዊነት ማምጣት” (ሙሴ 1፥39) ከሆኑት የእግዚአብሔር አላማዎች ጋር መስማማት ያስፈልገናል። ሌሎችን በወንጌል መንገድ እንድንረዳ ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን ያቀረቡልንን ግብዣ ስንቀበል፣ በእግዚአብሔር ስራ በመሳተፍ ደስታ ለማግኘት እንችላለን።4 (ለተጨማሪ የአገልጎት አላማዎች፣ “የአገልግሎት መሰረታዊ መርሆች፥ አገልግሎታችንን የሚቀይረው አላማ፣” በጥር 2018 (እ.አ.አ) ሊያሆና ውስጥ ይመልከቱ።)

  2. አገልልግሎትን ስለስራው ሳይሆን ስለሰዎች አድርጉት። ፕሬዘዳንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንዲህ እንድናስታውስ እንዳደረጉት፣ “የሚፈታው ችግር ከሚወደደው ሰው እንዲበልጥ በፍፁም አታድርጉ።”5 አገልግሎት ሰዎችን ስለመውደድ ነው፣ ስለሚደረጉ ነገሮች ሳይሆን። አዳኝ እንዳደረገው በማፍቀር ስናድግ፣ ሌሎችን በማገልገል ለሚመጣው ደስታ በተጨማሪም ዝግጁ እንሆናለን።

  3. አገልግሎትን ቀላል አድርጉ። የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ጉባኤ ጊዜአዊ ፕሬዘዳንት ኤም. ራሰል ባላርድ እንደነገሩን፥ “ታላቅ ነገሮች በቀላል እና በትንሽ ነገሮች መጥተዋል።… የእኛ ቀላል እና ትንሽ ደግነት እና አገልግሎት ወደ ሰማይ አባት ፍቅር ወደተሞላ ህይወት፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስራ በልባዊነት ወደመስራት፣ እና ለእርስ በራስ በምንረዳዳበት ጊዜ በሚሰማው ሰላም እና ደስታ ይጨማመራል።”6

  4. ከአገልግሎት ውስጥ ጭንቀትን አስወጡ። የሰውን ደህንነት ማከናወን የእናንተ ሀላፊነት አይደለም። ያም በግለሰቡ እና በጌታ መካከል ነው። የእኛ ሀላፊነት እነርሱን ማፍቀር እና አዳኛቸው ወደሆነው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲመለሱ መርዳት ነው።

የአገልግሎትን ደስታ ችላ አትበሉ።

አንዳንድ ጊዜ ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን እርዳታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ አይደሉም፣ ስለዚህ አገልግሎታችንን ማቅረባችን በትክክል የሚያስፈልጋቸው ነገር ሊሆን ይችላል። ነገር ግን እራሳችንን ሰዎች እንዲቀበሉን ማስገደድም መልሱ አይደለም። ከማገልገል በፊት ፈቃድ መጠየቅ መልካም ሀሳብ ነው።

የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ምልዓተ ጉባኤ አባል፣ ሽማግሌ ዲየተር ኤፍ. ኡክዶርፍ የኩፍኝ በሽታ ስለያዛት—እናም ልጆቿም ስለታመሙባት—ባለቤት የሌላት እናት ነግረውን ነበር። በጣም ንጹህ የነበረው ቤት ቆሻሻ እና የተበታተነ ሆነ። ሳህኖች እና ቆሻሻ ልብሶች ተኮለሉ።

ከአቅሟ በላይ እንደሆነ በተሰማት ጊዜ፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶች በሯን አንኳኩ። “ለመርዳት የምንችለውን ንገሪን” አላሉም። ጉዳዩን ሲመለከቱ፣ ወዲያው መስራት ጀመሩ።

“የፈራረሰውን አፀዱ፣ ብርሃንን እና ግልፅነትን ወደ ቤት አመጡ። አናም ግዋደኛቸውን በጣም አስፈላጊ ሸቀጣ ሸቀጦችን እንዲያመጡ ጠሩ። በስተመጨረሻ ስራቸውን ጨርሰው ሲሰናበቱ፣ ያቺን ወጣት አናት በእምባ ጥለዋት ነበር የሄዱት— የምስጋና እና የፍቅር እምባ።”7

ሰጪዎቹ እና ተቀባይም የደስታ ሙቀት ተሰማቸው።

በህይወታችሁ ደስታን አዳብሩ

ተጨማሪ ደስታ፣ ሰላም፣ እና እርካታ በህይወታችን ካዳበርን፣ ስናገለግልም ከሌሎች ጋር በተጨማሪ ለመካፈል እንችላለን። ደስታ በመንፈስ ቅዱስ በኩል ይመጣል (ገላትያ 5፥22 እና ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 11፥13 ይመልከቱ)። ይህም ለመጸለይ (ትምህርት እና ቃልኪዳን 136፥29 ይመልከቱ) እና ወደ ህይወታችን ለመጋበዝ የምንችልበት ነው። እነዚህ በራሳችን ህይወት ውስጥ ደስታን ለማዳበር የምንችልባቸው አንዳንድ ሀሳቦች ናቸው፥

  1. በረከታችሁን ቁጠሩ። ህይወታችሁን ስትመረምሩ፣ በማስታወሻችሁ ውስጥ እግዚአብሔር የባረካችሁን ነገሮች ጻፉ።8 በአካባቢያችሁ የሚገኙትን መልካም ነገሮች ተመልከቱ።9 ደስታ ከመሰማት የሚገድባችሁን ነገሮች ላይ ትኩረት ስጡ፣ እናም ለእነዚህ መፍትሄ ለማግኘት ወይም ለመረዳት የምትችሉበትን መንገዶች ጻፉ። በዚህ የትንሳኤ ዘመን፣ ከአዳኝ ጋር ታላቅ ግንኙነት ለማግኘት ጊዜ ውሰዱ(ትምህርት እና ቃልኪዳን 101፥36 ይመልከቱ)።

  2. መንከባከብን ተለማመዱ። ደስታን በጸጥተኛ ጥልቅ ሀሳብ በቀላል ለማግኘት ትችላላችሁ። 10 ደስታ ምን እንደሚያመጣላችሁ በቅርብ አድምጡ (1 ዜና መዋዕል 16፥15 ይመልከቱ)። ከማህደረ መረጃዎች የመለይየት ጊዜ አንዳንዴ መንከባከብን ለመለማመድ አስፈላጊ ለመሆን ይችላል።11

  3. እራሳችሁን ከሌሎች ጋር ማመዛዘንን አስወግዱ። ማመዛዘን የደስታ ሌባ ነው ተብሏል። ጳውሎስ እንዳስጠነቀቀው “እነርሱ ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር ሲያመዛዝኑ፥ ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር ሲያስተያዩ፥ አያስተውሉም” 1 ቆሮንጦስ 10፥12)።

  4. የግል ራዕይን ፈልጉ። አዳኝ እንዳስተማረው፥ “ብትጠየቁ፣ ደስታንና የሚያመጡትን፣ ዘለአለማዊ ህይወትን የሚያመጡትን—ሰላማዊ የሆኑ ነገሮችንና ሚስጥራትንም ታውቁ ዘንድ በራዕይ ላይ ራዕይን፣ በእውቀት ላይ እውቀትን ትቀበላላችሁ”ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥61)።

ለመስራት ግብዣ

በህይወታችሁ ውስጥ የምታገኙትን ደስታ በአገልገሎት እንዴት ለመጨመር ትችላላችሁ?

ማስታወሻዎች

  1. “Joy,” en.oxforddictionaries.com

  2. ራስል ኤ. ኔልሰን፣ “ደስታ እና መንፈሳዊ ደህንነት፣” Liahona፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 82።

  3. ጂን ቢ. ቢንገም፣ “አዳኝ እንደሚያደርገው ማገልገል፣” Liahona፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 107።

  4. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ወደፊት አብረን ስንገፋ፣” Liahona፣ ሚያዝያ፣ 2018 (እ.አ.አ)፣ 4–7።

  5. ቶማስ ኤስ ሞንሰን፣ “በጉዞው ደስታን ማግኘት፣” Liahona, ህዳር 2008 (እ.አ.አ.)፣ 86።

  6. ኤም. ራሰል ባላርድ “በሚያፈቅር አገልግሎት በኩል ደስታን ማግኘት፣” Liahona, ግንቦት 2011 (እ.አ.አ)፣ 49።

  7. ዲየተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “በወንጌል በደስታ መኖር፣” Liahona፣ ህዳር 2014፣ 120–123።

  8. ሔንሪ ቢ. አይሪንግ፣ “ለልጅ ልጆቼ፣” Liahona፣ ህዳር. 2007 (እ.አ.አ)፣ 67።

  9. ጂን ቢ. ቢንግሃም፣ “ደስታቹ ሙሉ ይሆን ዘንድ” Liahona፣ ህዳር 2017፣ 87።

  10. ዲየትር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “ከሁሉም በላይ አስፈላጊ ስለሆኑት ነገሮች፣” Liahona፣ ህዳር 2010 (እ.አ.አ)፣ 21።

  11. ጌሪ ኢ. ስቲቨሰን፣ “መንፈሳዊ ጭለማ፣” Liahona፣ ህዳር. 2017, 46

አትም