2019 (እ.አ.አ)
በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሳታፊነትን ባህል እንዴት መፍጠር እንችላለን?
ሐምሌ 2019 (እ.አ.አ)


ministering

የአገልግሎት መርሆች፣ ሐምሌ 2019 (እ.ኤ.አ)

በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሳታፊነትን ባህል እንዴት መፍጠር እንችላለን?

አ ጥቢያዎቻችንን እና በቅርንጫፎቻችንን ስንመለከት በቀላሉ የሚላመዱ የሚመስሉ ሰዎችን እንመለከታለን፡፡ የማንገነዘበው ነገር በቀላሉ የሚላመዱ በሚመስሉን ሰዎች መካከል እንኳን ብችኝነት የሚሰማቸው ብዙዎች እንዳሉ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ በቅርቡ የተደረገ ጥናት እንዳገኘው በአሜሪካ የሚኖሩ ግማሽ ያህሉ ጎልማሶች የብችኝነት ፣ የመተዉ እና የመገለል ስሜት እንደሚሰማቸው ዘግቧል፡፡1

የተካተቱ የመሆን ስሜት መሰማት በጣም ጠቃሚ ነዉ፡፡ ይህ የሰው ልጆች መሠረታዊ ፍላጎት ነው ፤ የተገለልን መስሎ ሲሰማን እንጎዳለን፡፡ መገለል የሃዘን እና የቁጣ ስሜትን ያስከትላል፡፡2 የተካተትን እንደሆንን ሳይሰማን ሲቀር ለኛ ይበልጥ አመቺ የሆኑ ስፍራዎችን ወደመመልከት እናዘነብላለን፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሁሉም ሰው ተሳታፊ እንደሆነ እንዲሰማው መርዳት ያስፈልገናል፡፡

እንደ አዳኙ አካታች መሆን

አዳኙ ዋጋ በመስጠትና በማካተት ፍጹም የሆነ ተምሳሌታችን ነበር፡፡ ሃዋርያቶቹን በመረጠበት ወቅት ለዝና፣ ለሃብት፣ ወይም ለከበረ የስራ መደብ ትኩረት አልሰጠም፡፡ ምንም እንኳን አይሁዶች ሳምራውያንን ዝቅ አድርገው ይመለከቱ የነበረ ቢሆንም በውሃ ጉድጓዱ አጠገብ ስለአምላክነቱ ምስክርነቱን በመስጠት ለሳምራዊቷ ሴት ዋጋ ሰጥቷታል፡፡(ዮሃንስ 4ን ይመልከቱ). የልብን ይመለከታል፤ሰዎችንም አያበላልጥም:: 1ኛ ሳሚኤል 16:7; ትምህርትና ቃልኪዳኖች 38:16, 26ን ይመልከቱ).

አዳኝ እንዲህ ብሏል፡

“እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በእርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።

“እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ ደቀመዛሙርቴ እንደሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ” (ዮሃንስ 13:34–35).

እኛ ምን ማድረግ እንችላለን?

አንዳንድ ጊዜ ሰዎች የተካተቱ እንዳልሆኑ እንደሚሰማቸው ለማወቅ ይከብዳል፡፡ አንዳንዶች አውጥተው አይናገሩትም —ቢያንስ ግልጽ አድርገው አያወጡትም፡፡ ነገር ግን አፍቃሪ በሆነ ልብ፣ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት እና ለመገንዘብ በምናደርገው ጥረት አንድ ሰው በቤተክርስቲያን ስብሰባዎችና እየተሰማው እንደሆነ ላይ ያለመካተት ስሜት እየተሰማው እንደሆነ ለማወቅ እንችላለን፡፡

አንድ ሰው ያለመካተት ስሜት እየተሰማውእንደሆነ ለማወቅ የሚረዱ ምልክቶች

  • እጅን አጥብቆ እንደ ማጣመርና አቀርቅሮ እንደ መመልከት የመሳሰሉ ዝግ የሰውነት ቋንቋዎች፡፡

  • በክፍሉ ውስጥ በመጨረሻ ረድፍ መቀመጥ ወይም ለብቻ መቀመጥ፡፡

  • ቤተክርስቲያን አለመካፈል ወይም አልፎ አልፎ መምጣት፡፡

  • ስብሰባዎችን ወይም አክቲቪቲዎችን አቋርጦ መውጣት፡፡

  • በውይይቶች ላይ ወይም በትምህርት ጊዜ አለመሳተፍ፡፡ እነዚህ ምልክቶች ምናልባት አይናፋር እንደ መሆን ፤ እንደ ጭንቀት እና ምቾት እንዳለመሰማት የመሳሰሉ የሌሎች ስሜቶችም መገለጫ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

አባላት የአንድ ቤተክርስቲያን አዲስ አባል ሲሆኑ፣ ከሌላ ሃገር ወይም ባህል የመጡ ሲሆኑ ፣ ወይም በህይወታቸው በቅርብ ጠባሳን ጥሎ ያለፈ እንደ ፍቺ፣ የቤተሰብ አባል ሞት ወይም ከሚስዮን አገልግሎት አቋርጦ እንደ መመለስ ያሉ ለውጦች አጋጥመዋቸው ከነበረ “ለየት ያሉ የመሆን”’ ስሜት ሊሰማቸው ይችላል፡፡

ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን በፍቅር ለመቅረብ ማመንታት የለብንም፡፡ የምንናገረው እና የምናደርገው ነገር ሁሉም ቅቡል እና ተፈላጊ እንደሆኑ እንዲሰማቸው የሚያደርግ ስሜት ሊፈጥር ይችላል፡፡

ተቀባይ እና አካታች የምንሆንባቸው አንዳንድ መንገዶች፡

  • ሁልጊዜም ቤተክርስቲያን ውስጥ ከተመሳሳይ ሰዎች ጋር አለመቀመጥ፡፡

  • እውነተኛ ማንነታቸውን ለመመልከት የሰዎችን ውጫዊ መገለጫዎች ወደጎን ማለት፡፡ (በዚህ ርዕስ ዙሪያ ይበልጥ ለማወቅ, “Ministering Is Seeing Others as the Savior Does” ሊያሆና, ሰኔ 2019 እኤአ, 8–11.)

  • ሌሎችን በውይይቶች ላይ ማሳተፍ፡፡

  • ሌሎች የህይወታችሁ አካል እንዲሆኑ መጋበዝ፡፡ እያቀዳችኋቸው ባሉ አክቲቪቲዎች ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ፡፡

  • ተመሳሳይ ፍላጎቶችን ማወቅና መገንባት፡፡

  • የኛን መስፈርት አያሟሉም ከሚል ስሜት በመነጨ ብቻ ከሌሎች ጋር ጓደኝነትን ከመፍጠር አለመቆጠብ፡፡

  • አንድ ሰው ላይ ልዩ ነገርን ስንመለከት ችላ ብለን ከማለፍና እንዳላየ ከመሆን ይልቅ አትኩሮትን መስጠት፡፡

  • ፍቅራችንን መግለጽና እውነተኛ የሆነ አድናቆትን ማሳየት፡፡

  • ምንም እንኳን ልዩነቶች ቢኖሩም ቤተክርስቲያኒቷ ለሁሉም ነች ማለት በእርግጥ ምን ማለት እንደሆነ ግዜን ወስዳችሁ አስቡ፡፡ እንዴት አድርገን ይሄንን እውን ማድረግ እንችላለን?

ከኛ ጋር ልዩነት ካላቸው ሰዎች ዙሪያ ሆነን ምቾት መሰማት ሁልጊዜ ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ነገር ግን በልምድ በልዩነቶቻችን ውስጥ ዋጋ ያለው ነገር ለማግኘትና እያንዳንዱ ሰው ይዞት የሚመጣውን ለየት ያለ አስተዋጽኦ ልናደንቅ እንችላለን፡፡ የአስራ ሁለቱ ሃዋሪያት ሽንጎ አባል የሆነው ሽማግሌ ዲተር ኤፍ ኡክዶርፍ እንዳስተማረው ልዩነቶቻችን የተሻልንና ደስተኛ ሰዎች እንድንሆን ያደርጉናል:: “ኑ! የመፈወስን፣ የደግነትን፣ እና የመሃሪነትን ባህል በሁሉም የእግዚአብሄር ልጆች ዘንድ እንገንባ እና እናጠንክር፡፡”3

በማካተት መባረክ

ክሪስትል ፌችተር ሃገሯ በጦርነት ምክንያኛት ከፈራረሰ በኋላ ወደ ሌላ አገር ተጓዘች፡፡ በአዲሱ መኖሪያዋ ማንንም አታውቅም ነበር ፤ ቋንቋውንም አትችልም ነበር፡፡ በዚህም መጀመሪያ የመገለል እና የብቸኝነት ስሜት ተሰማት፡፡

እንደ ቤተክርስቲያን አባልነትዋ ድፍረቷን አሰባስባ በአዲሱ ቅርንጫፏ መካፈል ጀመረች፡፡ የአነጋገር ዘይቤዋ ለየት ማለት ሰዎች እኔን ለማናገር እንዳይፈልጉ ሊያደርጋቸው ይችላል ወይም ያላገባች መሆንዋ በሌሎች ዘንድ እንድትገመት ሊያደርጋት ይችል ይሆን ብላ ተጨነቀች፡፡

ነገር ግን ያላቸውን ልዩነት ወደኋላ ብለው ፤ እንኳን ደህና መጣሽ የሚሏትን እና ወደ ጓደኝነታቸው ህብረት የሚቀላቅሏትን ሰዎች አገኘች :: በፍቅር ቀረቧት፣ እናም በአጭር ጊዜ እራሷን በህጻናት ክፍል አስተማሪነት እየረዳች አገኘችው፡፡ ህጻናቱ የተቀባይነት ታላቅ ተምሳሌቶች ነበሩ፤ የመፈቀርና የመፈለግ ስሜትዋ እምነትዋን አጠናክሮ በውስጧ የነበረውን ለጌታ ያላትን ጽናት አቀጣጠለው፡፡

ማስታወሻዎች

  1. አሌክሳ ላርዴሪ “ጥናት: ብዙ አሜሪካውያን የብቸኝነትን ስሜት ዘግበዋል፣ በተለይም ወጣቱ ትውልድ,” U.S. News, ግንቦት 1, 2018 እኤአ, usnews.com. ይመልከቱ

  2. ካርሊ ኬ ፒተርሰን፣ ላውራ ሲ ግሬቨንስ እና ኤዲ ሃርመን ጆንስ “Asymmetric Frontal Cortical Activity and Negative Affective Responses to Ostracism,” Social Cognitive and Affective Neuroscience, vol. 6, no. 3 (June 2011), 277–85. ይመልከቱ

  3. ዲየትር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “እመን ፣ አፍቅር፣ ተግብር” ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 48።