2019 (እ.አ.አ)
አንድን ሰው እንዲለወጥ መርዳት እችላለሁ ?
ነሐሴ 2019 (እ.ኤ.አ)


ምስል
ministering

የአገልግሎት መርሆች፣ ነሐሴ 2019 (እ.አ.አ)

አንድን ሰው እዲለወጥ መርዳት እችላለሁ ?

አዎን ነገር ግን ሚናችሁ ካሰባችሁት የተለየ ሊሆን ይችላል፡፡

የተፈጠርነው ከመለወጥ አቅም ጋር ነው፡፡ ወደ መለኮታዊ ሀይላችን ማደግ የስጋዊ ልምምዳችን አላማ ነው፡፡ በአገልግሎት ውስጥ ከትልቁ ግባችን አንዱ ሌሎችን ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ መርዳት እና እሱ ወዳለበት ለመመለስ አስፈላጊውን ለውጦች ማድረግ ነው፡፡ ነገር ግን በመምረጥ ነጻነታቸው ምክንያት ፤ እነሱን ይበልጥ ክርስቶስን መሰል እንዲሆኑ በመርዳት ውስጥ ያለን ሚና የተገደበ ነው፡፡

ሌሎችን ለመለወጥ እና ይበልጥ እሱን ለመምሰል በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ እንዴት መርዳት እንደምንችል ከአዳኙ የተወሰዱ ሰባት አይነተኛ ትምህርቶች ውሰጥ እነሆ፡

  1. ለውጥን ለመጋበዝ አትፍሩ

    አዳኙ ሌሎችን የድሮ መንገዳቸውን ወደኋላ እንዲተዉና የሱን ትምህርት እንዲቀበሉ ከመጋበዝ አልተቆጠበም ነበር፡፡ ጴጥሮስ እና ያዕቆብ ስራቸውን ትተው “ሰዎችን አጥማጆች እንዲሆኑ” ጋብዟቸዋል (ማርቆስ 1፡17)፡፡ በዝሙት የተያዘችዋን ሴት “ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትስሪ” ብሎ ጋብዟታል፡፡(ዮሀንስ 8:11 )። ወጣቱን ሀብታም ልጅ ከአለማዊ ነገሮች ጋር ያለውን ቁርኝት እንዲተው እና እንዲከተለው ጋብዞታል፡፡(ማርቆስ 10፡17-22 ን ይመልከቱ)፡፡ እኛም ሌሎችን ለውጦች እንዲያደርጉ እና አዳኙን እንዲከተሉ ስንጋብዝ ደፋር እና አፍቃሪ መሆን እንችላለን፡፡

  2. መለወጥ የነሱ ምርጫ እንደሆነ አስታውሱ

    አዳኙ የሚጋብዘው የለውጥ አይነት በግፊት ሊሆን አይችልም፡፡ አዳኙ አስተምሯል እንዲሁም ጋብዟል ፤ ነገር ግን አላስገደደም፡፡ሃበታሙ ወጣት ልጅ “እያዘነ ሄደ”(ማቲዎስ ወንጌል 19፡22)፡፡በቅፍርናሆም ፤ ከደቀ-መዛሙርቱ ብዙዎቹ “ወደ ኋላ ተመለሱ” እናም አስራ ሁለቱንም ለመመለስ ይወዱ እንደሆነ ጠየቃቸው(ዮሀንስ 6፡66-67)፡፡ አንዳንድ የመጥምቁ ዮሀንስ ተከታዮች አዳኙን ለመከተል መረጡ ፤ ሌሎች አልመረጡም፡፡(ዮሀንስ 1፡35-3710፡40-42)፡፡ እሱን ይበልጥ እንዲመስሉ ሌሎችን መጋበዝ እንችላለን ፤ ነገር ግን የመለወጥ ውሳኔውን እኛ ለእነሱ ልንወስንላቸው አንችልም፡፡እናም እስካሁን ለመለወጥ ካልወሰኑ ፤ ተስፋ ልንቆርጥም ሆነ እንደወደቅን ሊሰማን አይገባን፡፡

  3. ለሌሎች የመለወጥ ችሎታ ጸልዩ

    እየሱስ በምልጃ ጸሎቱ ጊዜ ፤ ደቀ-መዛሙርቱ ከክፉ እንዲጠበቁ ፣ የበለጠ እሱን እና አባቱን እንዲመስሉ፣ እናም በእግዚአብሔር ፍቅር እንዲሞሉ እግዚአብሔርን ጠየቀ፡፡(ዮሀንስ 17፡11፣ 21-23፣ 26 ይመልከቱ)፡፡ እናም ጴጥሮስ ወደ ሚናው ለማደግ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ ጥንካሬ እንደሚያስፈልገው አውቆ አዳኙ ጸለየለት(ሉቃስ 22፡32 ይመልከቱ)፡፡ ለሌሎች የምናደርጋቸው ጸሎቶች ልዩነት ማምጣት ይችላሉ(ያእቆብ 5፡16)፡፡

  4. በሱ ሀይል ላይ እንዲደገፉ አስተምሩዋቸው

    በአዳኙ አማካኝነት ብቻ ነው የእውነት መለወጥ የምንችለው እናም ሁላችንም ወዳለን መለኮታዊ አቅም የምናድገው፡፡ እሱ “መንገድና እውነት ህይወትም [ነው]፤ [በእሱ] በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” (ዮሀንስ 14፥6)። የሱ ሀይል ነው “ደካማ የሆኑትን ለእነርሱ ጠንካራ እንዲሆኑ” የሚያደርገው (ኤተር 12፡27)፡፡ አልማ ትንሹን እንዲለወጥ የረዳው የሱ የቤዛነት ሀይል ላይ የነበረው እምነት ነበር(አልማ 36፡16-23 ይመልከቱ)፡፡ ሌሎችም በህይወታቸው የሱ አንጣሪ ሀይል እንዲኖራቸው በአዳኙ ላይ እንዲደገፉ ልናስተምራቸው እንችላለን፡፡

  5. ወደፊት መሆን ወደሚችሉት ሰው እንደተለወጡ አድርጋችሁ ያዟቸው

    ፍቅር እና አቀባበል የለውጥ ሀይለኛ መሳሪያ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በውሃ ጉድጓዱ አጠገብ የነበረችው ሴት ባሏ ካልሆነ ወንድ ጋር ነበር የምትኖረው፡፡የእየሱስ ደቀ-መዛሙርት “ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተደነቁ” (ዮሀንስ 4፡27) ግን እየሱስ ወደፊት ምን ልትሆን እንደምትችል ነበር ይበልጥ የተጠነቀቀው፡፡ አስተማራት እንዲሁም ለመለወጥ እድል ሰጣት፤ እሷም ተለወጠች፡፡ (ዮሐንስ 4፥4-42ተመልከቱ)።

    ሌሎችን ወደፊት በሚሆኑት ሳይሆን አሁን በሚኖሩበት ስንይዛቸው ወደ ኋላ ልንጎትታቸው እንችላለን፡፡ በዛ ፋንታ ይቅር ማለት እና ያለፉ ስህተቶችን መርሳት እንችላለን፡፡ ሌሎች እንደሚለወጡ ማመን እንችላለን፡፡ ድክመትን ችላ ማለት እና ምናልባት በራሳቸው ውሰጥ ሊያዩት የማይችሉትን አወንታዊ ባህሪ መጠቆም እንችላለን፡፡“ግለሰቦችን አሁን እንዳሉት ሳይሆን መሆን ስለሚችሉት የማየት ግዴታ አለብን”፡፡1

  6. በራሳቸው ፍጥነት እንዲሄዱ ፍቀዱላቸው

    ለውጥ ጊዜ ይወስዳል፡፡ “ፍጹማን እስከምንደረግ ድረስ በትእግስት መቀጠል” አለብን (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 67፡13)፡፡ እየሱስ ለሌሎች ትግስት ነበረው እናም የሚቃወሙትን እንኳን በአባቱ የተሰጠውን ሀላፊነት አየመሰከረ እና ጥያቄዎቻቸውን እየመለሰ ማሰተማሩን ቀጥሏል (ማቲዎስ 12፡1-13ዮሀንስ 7፡28-29 ይመልከቱ)፡፡ ለሌሎች ትግስት ሊኖረን እና ለራሳቸውም ትግስት እንዲኖራቸው ማበረታታት እንችላለን፡፡

  7. ወደ ድሮ መንገዳቸው ከተመለሱ ተስፋ አትቁረጡ

    ክርስቶስ ከሞተ በኋላ ጴጥሮስ እና ሌሎቹ አንዳንድ ሀዋርያቶች እንኳን ወደ ለመዱት ህይወት ተመልሰው ነበር(ዮሀንስ 21፡3 ይመልከቱ)፡፡ ክርስቶስ ጴጥሮስን “በጎቹን መመገብ” እንደሚያስፈልገዉ አስታወሰው (ዮሀንስ 21፡15-17 ይመልከቱ)፤ እናም ጴጥሮስ ወደ አገልግሎቱ ተመለሰ፡፡ ወደ በፊት መንገዶች መመለስ እጅግ ቀላል ሊሆን ይችላል፡፡ አዳኙን መከተላቸውን እና ይበልጥ እሱን ለመምሰል መጣራቸውን እንዲቀጥሉ ፤ ድጋፋችንን በጨዋ ማበረታቻ እና በመንፈስ በተመሩ ግባዣዎች መቀጠል እንችላለን፡፡

ሌሎች እንዲያድጉ ፍቀዱላቸው

የአስራ-ሁለቱ ሀዋሪያት ሸንጎ አባል ሽማግሌ ጄፍሪ አር.ሆላንድ ሌሎችን እንዲያድጉ ስለመፍቀድ ይህን ታሪክ ይናገራል፡፡አንድ ጊዜ በትምህርት ቤቱ ይብዛም ይነስም ለብዙ አመታት የሁሉም ቀልድ መነሻ ስለነበር ወጣት ልጅ ተነግሮኝ ነበር፡፡ አንዳንድ ጉድለቶች ነበሩት ፤ እናም በሱ ላይ ማሾፍ ለአቻዎቹ ቀላል ነበር፡፡ ከጊዜ በኋላም ወደ ሌላ ቦታ ለቆ ሄደ፡፡ በስተመጨረሻም ሰራዊቱን ተቀላቀለ እናም ትምህርት በማግኘት እና በአጠቃላይ ከበፊት ህይወቱ በመውጣት ላይ አንዳንድ ስኬታማ ልምዶችን አገኘ፡፡ ከሁሉም በላይ በውትድርና ውስጥ ያሉ አብዘኛዎቹ እንደሚያደርጉት የቤተክርስቲያኑን ውበት እና ግርማ አገኘ እናም ንቁ ተሳታፊ ሆነ እናም ተደሰተበት፡፡

ከዛም ከተወሰኑ አመታት በኋላ ፤ ወደ ወጣትነቱ ከተማ ተመለሰ፡፡ሁሉም ባይሆኑም አብዛኞቹ የሱ ትውልዶች ግን ቦታ ቀይረው ነበር ፡፡ በደንብ ስኬታማ ሆኖ እና እንደ አዲስ ንቁ ሆኖ ሲመጣ ግን ፤ እዛ በነበረበት ጊዜ የነበረው የድሮው አስተሳሰብ እራሱ ፤ የሱን መመለስ እየጠበቀ ነበር፡፡ በትውልዱ ቦታ ለነበሩ ሰዎች እሱ አሁንም ያው ያረጀ ተመሳሳይ ሰው ነበር፡፡

በወጣትነት ጊዜ ይኖር የነበረውን አይነት ሕይወት አየኖረ እስኪሞት ድረስ ፤ ትንሽ በትንሽ ያለፈውን ነገር ለመተው እና እግዚአብሔር በፊቱ ያስቀመጠውን ሽልማት ለመያዝ ያለው የዚህ ሰው የጳውሎስ መሰል ጥረት፤ ቀስበቀስ ቀነሰ፡፡ ያለፈው ህይወቱ ከወደፊት ህይወቱ ይበልጥ አጓጊ ነው ብለው በሚያስቡ ሰዎች ድጋሚ ሊከበብ መሆኑ በጣም መጥፎ እና በጣም አሳዘኝ ነበር፡፡ ክርስቶስ ያስጨበጠውን ከጭብጡ ለማውጣት ችለዋል፡፡ በራሱ ትንሽ ስህተት ቢሆንም … አዝኖ ሞተ፡፡

ሰዎች ንስሀ እንዲገቡ ፍቀዱ፡፡ ሰዎች እንዲያድጉ ፍቀዱ፡፡ ሰዎች መለወጥ እና መሻሻል እንደሚችሉ እመኑ፡፡2

ማስታወሻዎች

  1. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “ሌሎችን መሆን አንደሚችሉት እዩዋቸው፣” Liahona፣ ህዳር 2012 (እ.ኤ.አ)፣ 70።

  2. ጄፍሪ አር. ሆላንድ፣ “The Best Is Yet to Be፣” Liahona፣ ጥር 2010፣ 1920፤

አትም