2019 (እ.አ.አ)
እንዴት መንፈሱ እንድታገለግሉ ሊረዳችሁ እንደሚችል (እናም እንደሚረዳችሁ)።
መስከረም 2019 (እ.አ.አ.)


የአገልግሎት መርሆች፣ መስከረም 2019 (እ.አ.አ.)

እንዴት መንፈሱ እንድታገለግሉ ሊረዳችሁ እንደሚችል (እናም እንደሚረዳችሁ)።

ለወንዶች እና ለሴቶች ለሁለቱም የተሰጠው የማገልገል የክህነት ስራ ራዕይን የመቀበል መብትን ያካትታል።

ምስል
ministering

ስዕላዊ መግለጫዎች ከ Getty Images

ለማገልገል እንዲሁም አዳኙ እንደወደደውም ለመውደድ የቀረበው ጥሪ አንዳንዴ ፈታኝ ሊመስል ይችላል—በተለይ በደንብ የማናውቃቸውን ሰዎች መርዳትን ሲያካትት። አያሌ የአገልግሎት መንገዶች ከመኖራቸው አንጻር ለተመደብንላቸው ከሁሉም የተሻሉትን ልንረዳቸው የምንችልባቸውን መንገዶች እንዴት ልናውቅ እንችላለን ብለን እናስባለን።

ረጅም ጊዜ ማሰብ አያስፈልገንም ምክንያቱም ከልብ የምናደርገው ጥረት በመንፈስ ቅዱስ ሊመራ ይችላል።

“የተቀደሰ የአገልግሎት ስራችሁ የመነሳሳትን መለኮታዊ መብት ይሰጣችኋል፣” ብላለች የወጣት ሴቶች ዋና ፕሬዚዳንት የሆነችው እህት ቦኒ ኤች. ኮርደን። “ያንን መነሳሳት በእምነት መጠየቅ ትችላላችሁ።”1

አዳኙ እንዳገለገለው ለማገልገል ስንፈልግ፣ እርሱን በመራው በዛው መንፈስ ልንመራ እንችላለን። ይህ በኤጲስ ቆጶሱ የክህነት ስልጣን ቁልፎች አማካኝነት በሚሰጡ እንደ አገልግሎት ባሉ ስራዎች ላይ በተለይ እውነት ነው። በመንፈስ አማካኝነት ለማገልገል የሚያስችሉ አምስት ጥቆማዎች እነሆ

በአገልግሎት ወቅት መንፈሱ ሊኖረኝ የሚችለው እንዴት ነው?

  • መመሪያን ጠይቁ። ሰማያዊ አባታችን ከእርሱ ጋር በጸሎት አማካኝነት ግንኙነት እንድናደርግ ይፈልጋል። ጸሎት ወደ እርሱ እንድንቀርብ ብቻ አይደለም የሚረዳን፣ ነገር ግን “እግዚአብሔር ቀድሞውኑ ሊሰጠን የፈቀዳቸውን ነገር ግን በእኛ የመጠየቅ ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠባቸውን በረከቶችንም” ያስገኝልናል።2 “ስንጸልይ እና ሃሳባቸውን ለማወቅ ስንፈልግ” ትላለች እህት ኮርደን “ሰማያዊ አባት እንደሚመራን እና መንፈሱ ከእኛ ጋር እንደሚሄድ እመሰክራለሁ።”3

  • ተነሳሽነት እሰክታገኙ አትጠብቁ። በራሳችሁ ተነሳሽ እና ምላሽ ሰጪ ሁኑ። “በጉጉት የምታከናውኑ” ሁኑ(ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 58፥27)፣ እናም ጥረቶቻችሁ መመሪያ ሊያገኙ እና ሊጎሉ የሚችሉ ሆነው ታገኙታላችሁ። “በአገልግሎታችን እና በስራችን መቀጠላችን መገለጥን ለማግኘት ብቁ ለመሆን ጠቃሚ መንገድ ነው“ ብሏል በቀዳሚ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ የሆነው ፕሬዚዳንት ዳለን ኤች. ኦክስ። “በቅዱሳን ጽሁፎች ጥናቴ ውስጥ አብዛኞቹ መገለጦች ለእግዚአብሔር ልጆች የሚመጡት በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ እንጂ በቤታቸው ተቀምጠው ጌታ የትኛውን የመጀመሪያ እርምጃ እንደሚወስዱ እንዲነግራቸው ሲጠብቁ እንዳልሆነ አስተውያለሁ።”4

ስለማገልገል የሚመጡ የመንፈስ ምሪቶችን እንዴት ለይቼ ማወቅ እችላለሁ?

  • የሞርሞንን ምክር ተቀበሉ። ሃሳቡ ከመንፈስ ምሪት የመጣ ነበር ወይም አልነበረም ብለን መጨነቅ አያስፈልገንም። የሞርሞን ቀላል ቁልፍ የማወቂያ መንገድ እያለን፥ ጥሩ እንድታደርጉ እናም በክርስቶስ እንድታምኑ ወይም ሰዎች እንዲያምኑ ለማሳመን የሚያነሳሳ ሃሳብ ካላችሁ፣ ይህ ከእግዚአብሔር መሆኑን ማወቅ ትችላላችሁ (ሞሮኒ 7፥16 ይመልከቱ)።

  • ስለሱ አትጨነቁ። “ዝም ብላችሁ ወደ መዋኛው ገንዳ ግቡ እና ዋኙ” ብሏል የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ሸንጎ አባል የሆነው ሽማግሌ ጀፈሪ አር. ሆላንድ። “እርዳታ ወደሚያስፈልጋቸው ሂዱ። የጀርባ ዋና ነው ወይስ የደረት ነው የምዋኘው ብላችሁ በመጨነቅ ሳትንቀሳቀሱ አትቅሩ። የተሰጠውን የመሰረታዊ መርሆዎች ትምህርት ከተከተልን፣ ከክህነት ቁልፎች ጋር ስምም ሆነን ከቀጠልን፣ እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ እንዲመራን ከፈለግን፣ ልንወድቅ አንችልም።”5

የመንፈስ ምሪትን ለመከተል ከሁሉ የተሻለው መንገድ የትኛው ነው?

  • ወዲያውኑ። እህት ሱዛን ቤድናር (የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ሸንጎ አባል የሆነው የሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር ባለቤት) መንፈሳዊ ምሪትን በመከተል ታላቅ ምሳሌ ናት። “መንፈሳዊ አይኖች እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ማየት እንዲችሉ “ ከጸለየች በኋላ፣ የተሰበሰቡትን መልከት መልከት አድርጋ ብዙ ጊዜ “በተለይ አንድን ሰው ለመጎብኘት ወይም ለአንድ ሰው ስልክ ለመደወል መንፈሳዊ ግፊት ይሰማታል“ ሲል አካፍሏል ሽማግሌ ቤድናር ። “እናም እህት ቤድናር ይህን የመሰለ ስሜት ሲሰማት፣ ወዲየውኑ ምላሽ ትሰጣለች እናም ትታዘዛለች። አብዛኛውን ጊዜ እንደሚሆነው ልክ የመዝጊያ ጸሎቱ ተጸልዮ ‘አሜን ‘ እንደተባለ፣ ከአንድ ወጣት ልጅ ጋር ታወራለች ወይም አንድን እህት ታቅፋለች ወይም፣ ወደ ቤት እንደተመለስንም፣ ስልኩን ታነሳና ትደውላለች።”6

  • በድፍረት። ተቀባይነትን አላገኝም የሚል ፍርሃት፣ የአይናፋርነት፣ ብቃት ያለመኖር፣ ወይም ተስማሚ ያለመሆን ስሜቶች ለማገልገል የቀረበልንን መንፈሳዊ መመሪያ እንዳንከተል ወደኋላ ሊጎትቱን ይችላሉ። “በተለያዩ ጊዜያት እና መንገዶች፣ ሁላችንም ብቁ ያለመሆን፣ እርግጠኛ ያለመሆን፣ ምናልባትም ዋጋቢስ የመሆን ስሜት ይሰማናል“ ብሏል የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ሸንጎ አባል የሆነው ሽማግሌ ጌሪት ደብልዩ. ጎንግ። “ግን እግዚአብሔርን ለመውደድ እና ጎረቤቶቻችንን ለማገልገል በምናደርገው ታማኝ ጥረት፣የእግዚያብሄር ፍቅር እና የተፈለገው ተነሳሽነት ለእነሱ እና ለእኛ በአዲስ እና በተቀደሱ መንገዶች ሊሰማን ይችላል።”7

    ራሷን ለማጥፋት የሞከረችን ሴት ባል ለመርዳት እንዴት አመንትቶ እንደነበር አንድ ወንድም አካፍሏል። ነገር ግን በመጨረሻ ባልየውን ለምሳ ጋበዘው። “‘ሚስትህ ራሷን ለመግደል ሞክራ ነበር። ያ ለአንተ ከባድ መሆን አለበት። ስለዚህ ነገር ማውራት ትፈልጋለህ?’ ስለው በግልጽ አለቀሰ” ሲል አካፍሏል። “ርህራሄ የተሞላበት እና ወዳጃዊ ውይይት አደረግን እናም በደቂቃዎች ውስጥ ለየት ያለ ቅርበት እና እምነትን አዳብረን ነበር።8

ማስታወሻዎች

  1. ቦኒ ኤች. ኮርደን , “Becoming a Shepherd፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 76።

  2. የመፅሐፍ ቅዱስ የመዝገበ-ቃላት፣ “ጸሎት”

  3. ቦኒ ኤች. ኮርደን , “Becoming a Shepherd፣” 76።

  4. ዳሊን ኤች. ኦክስ ፣ “In His Own Time, in His Own Way፣” ሊያሆና፣ ነሃሴ 2013 (እ.አ.አ)፣ 24።

  5. ጀፍሪ አር. ሆላንድ፣ “The Ministry of Reconciliation,” ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 77።

  6. ዴቪድ ኤ. ቤድናር “Quick to Observe፣” ሊያሆና፣ ታህሳስ 2006 (እ.አ.አ)፣ 17።

  7. ጌሪት ደብልዩ. ጎንግ፣ “Our Campfire of Faith፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 42።

  8. ቦኒ ኤች. ኮርደን፣ “Becoming a Shepherd፣” 76ን ይመልከቱ።

አትም