2019 (እ.አ.አ)
ይህን በጣም አስፈላጊ የአገልግሎት ክፍል እያጣችሁ ነውን ?
ጥቅምት 2019 (እ.ኤ.አ)


የአገልግሎት መርሆች፣ ጥቅምት 2019 (እ.ኤ.አ.)

ይህን በጣም አስፈላጊ የአገልግሎት ክፍል እያጣችሁ ነውን?

“ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ እንደዚሁም ሁሉ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ” ይህ ነው አገልግሎት (ሮሜ 12፡15)፡፡

ministering

ምስል በአጉስቶ ዛምቦናቶ

ስለአገልግሎት ስናስብ የተቸገሩትን ስለመርዳት ማሰብ ቀላል ነው፡፡ ባሏ ለሞተባት ሴት የአትክልት ቦታዋን ስለማስተካከል፣ ለታመመ ሰው እራት ስለመውሰድ፣ ወይም ለተቸገሩ ስለመስጠት እናወራለን፡፡ ‘’ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ’’ የሚለውን የጳውሎስን ምክር እናስታውሳለን ፤ ነገርግን ‘’ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ’’ የሚለውን የዚህን ጥቅስ የመጀመሪያ ክፍል ላይ በቂ ትኩረት እንሰጣለን? (ሮሜ 12:15 )፡፡ ከምናገለግላቸው ሰዎች ጋር መደሰት--- ትርጉሙ ላገኙት መልካም ውጤት አንድ ላይ ማክበር ወይም በከባድ ጊዜያት ውስጥ ደስታን እንዲያገኙ መርዳት ቢሆን---እንደአዳኙ ለማገልገል ትልቁ ክፍል ነው፡፡

እግዚአብሄር በህይወታችን ውስጥ ያስቀመጠው መልካም ነገር ላይ ለማተኮር ስንመለከት ሊረዱን የሚችሉ (አንዱ ደሞ መሸሽ ያለብን) ሶስት ሃሳቦች እነኚህ ናቸው፡፡

1.እወቁ

የወጣት ሴቶች አጠቃላይ ፕሬዘዳንት ቦኒ ኤች. ኮርዶን የምናገለግላቸውን ሰዎች ሸክማቸውን እና ችግራቸውን ብቻ ሳይሆን ጥንካሬያቸውን ፣ተሰጦአቸውን፣ እና ስኬታቸውንም ማየት እንዳለብን እንድንረዳ ረድታናለች፡፡ ‘’ሁኔታቸውን የምናውቅ እናም በተስፋቸውና በህልማቸው ላይ የምንደግፋቸው - ደጋፊ እና ሚስጥረኛ’ መሆን እንዳለብን ተናግራለች፡፡1

በበጉ እና በፍየሎቹ ምሳሌ ውስጥ አዳኙ እነዛ ከእርሱ በስተቀኝ በኩል የሚገኙት እንዲህ ብለው ይጠይቁኛል ብሏል ‘’ጌታ ሆይ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?

እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ ?’’ የማቴዎስ ወንጌል25፥37–38)፡፡

እህት ኮርደን “ወንድሞች እና እህቶች፣ ቁልፍ ቃሉ ማየት ነው” ብላለች፡፡ ‘’ጻድቃኖቹ የተቸገሩትን ያዩት እየተመለከቱ እና እያስተዋሉ ስለነበር ነው፡፡ እኛም ለመርዳት እና ለማጽናናት ፣ ለማክበር እና እንዲያዉም ለማለም ንቁ ተመልካች መሆን እንችላለን፡፡’’2

2.ለማክበር ምክንያቶችን ፈልጉ

ትልቅም ሆነ ትንሽም ስኬትን አክብሩ፡፡ ካንሰር በሽታን ማሸነፍ ሊሆን ይችላል ወይም ከፍቅረኛ ጋር መለያየትን ማለፍ፣ አዲስ ስራ ማግኘት ወይም የጠፋ ጫማን ማግኘት፣ የምንወደውን ሰው ካጣን በኋላ አንድ ወርን ተቋቁሞ ማለፍ ወይም ያለስኳር አንድ ሳምንትን ተቋቁሞ ማለፍ ሊሆን ይችላል፡፡

እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት ደውሉ፣ካርድ ላኩላቸው፣ ወይም ለምሳ አንድ ላይ ውጡ፡፡ በረከቶቻችንን አንድ ላይ ስንጋራ፣ በምስጋና ስንኖር፣ እናም የሌሎችን በረከቶች እና ስኬቶች ስናከብር፣ እኛ ‘’በወንድሞቻችን ደስታ ሀሴት” እያደረግን ነው (አልማ 30፡34 )፡፡

3.የእግዚአብሄርን እጅ ተመልከቱ

አንዳንድ ጊዜ ከሌሎች ጋር መደሰት ማለት፤ በህይወታችን ምንም አይነት ችግር ወይም ደስታ ቢገባ ለመደሰት ያሉአቸውን ምክንያቶች እንዲያዩ መርዳት ነው፡፡ የሰማይ አባታችን እንደሚያውቀን እና እኛን ለማንሳት ዝግጁ የመሆኑ ቀላል እውነታ ለደስታ አስገራሚ ምንጭ ነው፡፡

እናንተ የጌታን እጅ እንዴት በህይወታችሁ እንዳያችሁት በማካፈል ሌሎች በህይወታቸው የጌታን እጅ እንዲያዩ መርዳት ትችላላችሁ፡፡ በችግራችሁ ውስጥ የሰማይ አባት እንዴት እንደረዳችሁ ለማካፈል ራሳችሁን ትሁት አድርጉ፡፡ ይህ ምስክርነት እሱ እንዴት እንደረዳቸው እንዲያዩ እና እንዲገነዘቡ ይረዳቸዋል(ሞዛያ 24፡14ን ይመልከቱ)፡፡

4.ለመደሰት ያላችሁን አቅም አትገድቡት

በሚያሳዝን ሁኔታ ልናበረክተው ስለምንችለው ነገር ወይም በህይወት ስላለንበት ቦታ አለመረጋጋት ሲሰማን ፤ ከሌሎች ጋር ለመደሰት ያለንን አቅም ልንገድብ እንችላለን፡፡ በሌሎች ሰዎች ደስታ ውስጥ ሀሴትን ከመፈለግ ይልቅ በንጽጽር ወጥመድ ውስጥ እንወድቃለን፡፡ የአስራ ሁለቱ ሀዋርያት ሸንጎ አባል የሆኑት ሽማግሌ ክዊንተን ኤል ኩክ እንዳስተማሩት ‘’በረከቶችን ማነጻጸር በእርግጥ ደስታን ያባርራል፡፡ በተመሳሳይ ሰአት አመስጋኞች እና ቅናተኞች መሆን አንችልም፡፡’’3

‘’ሁሉም ሰው ውስጥ በሚባል መልኩ የተለመደን ይህን አይነት ዝንባሌ እንዴት ልናሸንፍ እንችላለን?’’ ብለው የአስራ ሁለቱ ሀዋርያት ሸንጎ አባል የሆኑት ሽማግሌ ጀፍሪ አር ሆላንድ ጠይቀዋል፡፡‘’…ብዛት ያላቸውን በረከቶቻችንን መቁጠር እንችላለን እናም ለሌሎች ስኬት ማጨብጨብ እንችላለን፡፡ ከሁሉም የተሻለው ደሞ ፤ለልብ የሚታዘዝ ምርጡ እንቅስቃሴ፤ ሌሎችን ማገልገል ነው፡፡’’4 ከማነጻጸር ይልቅ የምናገለግላቸውን ሰዎች ማመስገን እንችላለን፡፡ በነጻነት ስለነሱ ወይም ስለቤተሰባቸው አባል የምታደንቁትን ነገር አካፍሏቸው፡፡

ጳውሎስ እንደሚያስታውሰን እኛ ሁላችንም የክርስቶስ አካል አባል ነን እናም ‘’አንድ ብልትም ቢከበር ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል’’ (1ኛ ቆሮንጦስ 12፤26)፡፡ በሌሎች በረከቶች፣ ተሰጥኦዎች፣ እናም ደስታ የእውነት እንድንደሰት ፤ በሰማይ አባት እርዳታ የሌሎችን ልምዶች ለመገንዘብ ፣ትልቅም ሆነ ትንሽም ስኬትን ለማክበር፣ የእግዚአብሄርን እጅ እንዲያዩ መርዳት ፣እናም ቅናትን ማስወገድ እንችላለን፡፡

ማስታወሻዎች

  1. ቦኒ ኤች. ኮርደን , “Becoming a Shepherd፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.ኤ.አ)፣ 75።

  2. ቦኒ ኤች. ኮርደን , “Becoming a Shepherd፣” 75።

  3. ክዉንተን ኤል. ኩክ፣ “ተደሰቱ!” Ensign፣ ህዳር 1996 (እ.ኤ.አ)፣ 30።

  4. ጀፍሪ አር. ሆላንድ፣ “The Other Prodigal,” ሊያሆና፣ ህዳር 2002 (እ.ኤ.አ)፣ 64።