2019 (እ.አ.አ)
የገና ታሪክ ስለ አገልግሎት የሚያስተምረን
ታህሳስ 2019 (እ.አ.አ)


የአገልግሎት መርሆች፣ ታህሳስ 2019 (እ.አ.አ.)

የገና ታሪክ ስለአገልግሎት ምን እንደሚያስተምረን

“ይህ የአመቱ ተመራጭ ወቅት ነው፡፡ግጥምን ዘምሩ; የገና ወቅት በቅርቡ ይመጣል፡፡ የጌታን የውልደቱን እውነተኛ ታሪክ ተናገሩ፣ እንደ ህጻን ወደ ምድር የመጣበትን ጊዜ(“የውልደቱ መዝሙር፣”የህጻናት የመዝሙር መጽሃፍ

ministering

ዝርዝሩ ከ Behold the Lamb of God,በዋልተር ሬን፡፡

የገና በዓል በጎች ፣ እረኞች ፣ ግርግሞች እና ኮከቦች በድንገት አዲስ ትርጉም የሚይዙበት ድንቅ ጊዜ ነው። በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በጣም አስፈላጊ ከሆኑት ክስተቶች አንዱን በመዘከር ረገድ ወሳኝ ተጫዋቾች ይሆናሉ ፡፡ ብዙ ቤተሰቦች በቤታቸው ውስጥ የውልደቱን ምስል ያሳያሉ። ሌሎች የእርሱን የልደት ታሪክ ለማንበብ ወይም በአንድ ክፍል ውስጥ ለመሳተፍ ልባዊ ጥረት ያደርጋሉ ፡፡ የልደት ታሪኩ እንደ ሌሎች የክርስቶስ ታሪኮች ሁሉ ስለአገልግሎት በሚያስተምሩን ፤ በእርሱ ብርሃን አለምን ብርሃን ለማድረግ በሚያስችሉ ትምህርቶች የተሞላ ነው፡፡ “የገና ታሪክ የፍቅር ታሪክ ነው“ ብለዋል የቀዳሚ አመራር ሁለተኛ አማካሪ የሆኑት ፕሬዚዳንት ሄነሪ ቢ.አይሪንግ።

“…በክርስቶስ የልደት ታሪክ ውስጥ እርሱ ማን እንደነበረ እና ማን እንደሆነ ለማየት እና ለማወቅ እንችላለን፡፡ ያም በመንገዳችን ላይ ሸክማችንን ያቀልልናል፡፡ እናም እራሳችንን ወደ መርሳት እና የሌሎችን ሸክም ወደ ማቅለል ይመራናል፡፡”1

”በእንግዳ ማረፊያው ለእነርሱ የሚሆን ቦታ አልነበረም”ሉቃስ 2፡7

የእንግዳ ማረፊያው ባለቤቶች ለአዳኙ ቦታ አላገኙለትም እኛ ግን ያንን ስህተት መስራት የለብንም፡፡ ለወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችን በጠረጴዛዎቻችን ላይ በቤታችን ውስጥ እና በባህሎቻችን ውስጥ ቦታ በመስጠት ለአዳኙ በልባችን ቦታ ልንሰጠው እንችላለን፡፡ ብዙዎቹ የቤተሰብ ልማዶች ሌሎችን በማካተት ጣፋጭ እና ይበልጥ የማይረሱ ሊደረጉ ይችላሉ፡፡ ዳያና እና ቤተሰቦቿ ገናን ከእነርሱ ጋር እንዲያሳልፍ ሰው የመጋበዝ ልማድ ነበራቸው፡፡ በያንዳንዱ የታህሳስ ወር ማንን ሊጋብዙ እንደሚችሉ ይማከሩና ይወስናሉ፡፡2 ምናልባት ቤተሰባችሁ እንዲህ ያለ ልማድ ሊጀምር ይችላል፡፡ ምናልባት ከምታገለግሏቸው አንዱ ተወዳጅ የሆኑ የገና መዝሙሮችን ከቤተሰባችሁ ጋር አብሮ ለመዘመር ሊቀላቀል ሊወድ ይችላል፡፡ በአቅራቢያ ቤተሰብ የሌለውን አንድ ሰው በገና እራት ላይ ቦታ ልታገኙለት ትችላላችሁ፡፡

የእርሱን የማካተት ምሳሌ ከመከተል ይልቅ አዳኙን የምናስታውስበት ምን የተሻለ መንገድ አለ? “እርሱም ከቸርነቱ ይካፈሉ ዘንድ ሁሉም ወደ እርሱ እንዲመጡ ይጋብዛል፤ እናም ወደ እርሱ የሚመጡትን ማንንም፣ ጥቁርም ነጭም፣ ባሪያውንና ነፃውን፤ ሴትና ወንድን አይክድም፤ እምነተቢሶችንም ያስታውሳል፤ እናም አይሁድም ሆኑ አህዛብ፣ ሁሉም ለእግዚአብሔር አንድ ናቸው።“( 2ኛ ኔፊ 26፡33 ቦታ ፈልጉ እና ማካተትን ፍጠሩ፡፡

“በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ፡፡“ (ሉቃስ 2፡8)

ለህጻኑ አዳኝ መጀመሪያ ሰላምታ ካቀረቡለት ከመጀመሪያዎቹ መካከል እረኞች ነበሩ ማለት ትክክል ይመስላል፡፡ የጥንት ነቢያት ኢየሱስን “የእስራኤል እረኛ“ መዝሙር 80፡1 እና “በምድር ላይ ሁሉ አንድ እረኛ“ ብለው ይጠሩት ነበር፡፡1ኛ ኔፊ13:41 እናም ክርስቶስ ራሱ “ እኔ መልካም እረኛ ነኝ፣ እናም በጎቼን አውቃለሁ “ ብሏል፡፡ በጎቻችንን ማወቅ እና መጠበቅ እንደ አዳኙ አይነት እረኛ የመሆን እና የማገልግል ቁልፍ ክፍል ነው፡፡

ከአንጸባራቂ መብራቶቹ እና ከማጋጊያጫዎቹ ጋር በገና ወቅት ብዙ የሚታዩ ነገሮች አሉ፡፡ ነገር ግን ምናልባት ትልቁ የወቅቱ ውበት ትኩረታችንን ወደምናገለግላቸው እና መንጋዎቻችንን ወደ መጠበቅ ማዞርን ስናስታውስ ሊገኝ ይችላል፡፡ ጥበቃችን የአንድን ሰው ተወዳጅ መዝናኛ ማስተዋልን ወይም የአንድን ሰው የበአል እቅድ መጠየቅ ሊሆን ይችላል፡፡ የሌሎችን ፍላጎቶች ስንመለከት እና ስናሟላ እየጠበቅን ነው—በግልጽ የሚታወቁትንም የማይታወቁትንም፡፡

ቼሪል በድንገት ባሏን በሞት ስትነጠቅ በከባድ ድንጋጤ ተውጣ ነበር፡፡ ያለ እሱ የምታሳልፈው የመጀመሪያው የገና በአል ሲቃረብ ብቸኝነቷ ጨመረ፡፡ እንደ እድል ሆኖ የምታገለግላት እህት ሻውና ነበረችላት፡፡ ሻውና እና ባሏ ጂም በብዙ የበአል ጉዞዎች ላይ ቼሪልን ጋበዟት፡፡ የቼሪልን ያረጀ ኮት ተመለከቱና አንድ ነገር ማድረግ እንዳለባቸው ወሰኑ፡፡ ከገና በአል ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ሻውና እና ጂም ለቼሪል የገና ስጦታ አመጡላት:ያማረ አዲስ ኮት፡፡ የቼሪልን ሙቀት የሚሰጥ የኮት ቁሳዊ ፍላጎት አውቀው ነበር ይህ ብቻም አይደለም የመጽናናት እና የጓደኛ ስሜታዊ ፍላጎቷንም ጭምር፡፡ እነዚያን ፍላጎቶች ለማሟላት የቻሉትን ሁሉ አደረጉ እንዲሁም እኛም መንጋዎቻችንን እንዴት መጠበቅ እንዳለብን ጥሩ ምሳሌ ተዉልን፡፡3

“እረኞቹ እርስ በርሳቸው እንግዲህ እሰከ ቤተልሄም ድረስ እንሂድ ተባባሉ“ሉቃስ 2፡15

“አሁን እንሂድ ”የሚለው አስደሳች ግብዣ ነው! እረኞቹ ጓደኞቻቸው ጉዞውን ለማድረግ እጅግ ይደክማሉ ብለው ቅድመ ትንበያ አላደረጉም፡፡ ድምጻቸውን አጥፍተውም ለብቻቸው ወደ ቤተልሄም አላቀኑም፡፡ በደስታ ተያይተው “አሁን እንሂድ ”አሉ፡፡

ጓደኞቻችን ህጻኑን አዳኝ መጥተው እንዲያዩ መጋበዝ ባንችልም ከኛ ጋር በማገልገል የገና መንፈስ (የክርስቶስ መንፈስ) እንዲሰማቸው መጋበዝ እንችላለን፡፡ “የገናን መንፈስ የምናሳድግበት መንገድ በዙሪያችን ያሉ ሰዎችን በመርዳት እና እራሳችንን በመስጠት ነው“ ትላለች የቀድሞዋ የወጣት ሴቶች ዋና ፕሬዚደንት የሆነችው ቦኒ ኤል. ኦስካርሰን፡፡4 ሻማ ይዛችኋል ብለን እናስብ፡፡ ሌሎች በእርግጠኝነት ማየት እና ከሻማችሁ በሚወጣው ብርሃን መጠቀም ይችላሉ፤ ነገር ግን ሻማችሁን በመጠቀም ሻማቸውን ብታበሩላቸው እና ብርሃኑን እራሳቸው ለራሳቸው እንዲይዙ ብትፈቅዱላቸው ምን ያህል ሙቀት እንደሚሰማቸው አስቡት፡፡

ክርስቶስ እራሱ የሚከተሉት የህይወት ብርሃን እንደሚሆንላቸው አስተምሯል፡፡ዮሐንስ 8፡12 እንደ እርሱ ማገልገል እርሱን የምንከተልበት እና ቃል በተገባልን ብርሐን የምንደሰትበት አንድ መንገድ ነው፡፡ ስለዚህ ሌሎች ከናንተ ጋር እንዲያገለግሉ በመጋበዝ ብርሃኑን አካፍሉ! እናንተ እና የምታገለግሏቸው እንዴት አብራችሁ ማገልገል ትችላላችሁ? የምትወዱትን ምግብ አብራችሁ ልታዘጋጁ ትችላላችሁ ወይም አንድን ሰው በትንሽ ስጦታ ወይም ማስታወሻ በድንገት ማስደሰት ትችላላችሁ፡፡ የክርስቶስን የአገልግሎት ምሳሌ ከመከተል የሚገኘውን ብርሃን ሁለታችሁም አብራችሁ ማጣጣም ትችላላችሁ፡፡

“አይተውም ስለዚህ ህጻን የተነገረላቸውን ነገር ገለጡ፡፡ሉቃስ 2:17

አስደናቂውን የክርስቶስ መወለድ ዜና የቻሉትን ያህል ከብዙ ሰዎች ጋር በተካፈሉ ጊዜ እረኞቹ የተሰማቸውን ደስታ በቀላሉ መገመት ይቻላል፡፡ በመላእክት የተበሰረው የተተነበየለት መሲህ መጥቶ ነበር፡፡ እዚህ ነበር! በርግጥ የአዳኙን መልካም ዜና ማካፈል የውልደቱ ታሪክ ትልቅ ጭብጥ ነው፡፡ መላእክቱ ዘመሩ፡፡ ኮከቡ መንገዱን መራ፡፡ እናም እረኞቹ ከአገር ውጪ ላሉ አሳወቁ፡፡

መልካሙን ዜና በማካፈል እና ስለአዳኙ በመመስከር በገና ታሪኩ ላይ ድምጻችንን እንጨምራለን፡፡ “በአገልግሎት ጥረታችሁ አዳኙን ለመወከል መብት ስላላችሁ ራሳችሁን “ለዚህ ግለሰብ ወይም ቤተሰብ የወንጌልን ብርሃን ማካፈል የምችለው እንዴት ነው?’” ብላችሁ ጠይቁ ሲሉ አስተምረዋል የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንት የሆኑት እህት ዣን ቢ.ቢንግሃም፡፡ ”መንፈስ ምን እንዳደርግ እያነሳሳኝ ነው?”5

ስለአዳኙ እና ስለወንጌሉ እንዴት ምስክርነታችሁን ልታካፍሉ እንደምትችሉ ለማወቅ ስትፈልጉ ግምት ውስጥ የምታስገቧቸው ጥቂት ጥቆማዎች እነሆ

  • ስለአዳኙ ስሜታችሁን የሚገዛ ወይም ስለሱ ለምን አመስጋኝ እንደሆናችሁ የሚገልጽ ቅዱስ ጽሁፍ አግኙ፡፡ ለምታገለግሏቸው አካፍሉ፡፡

  • ከገና ተንቀሳቃሽ መልእክት ጋር አጭር የጽሁፍ ወይም የማህበራዊ ሚዲያ መልእክት ላኩላቸው፡፡ በ ChurchofJesusChrist.org ላይ የሚያስደንቁ ታገኛላችሁ!

  • ክርስቶስን እንድታስታውሱ ስለሚያደርጋችሁ ልዩ ትዝታ ወይም ልማድ ለጓደኛችሁ ተናገሩ፡፡

መንፈስ ቅዱስ ለስምኦን እና ለሃና ህጻኑ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ እንደመሰከረላቸው የምስክርነታችሁን እውነትነት እንደሚመሰክርላችሁ እምነት ይኑራችሁ፡፡(ሉቃስ 2:26 ፣38ን ይመልከቱ፡፡)

”የኢየሱስ ክርስቶስን ወደአለም መምጣት ክብር ለመስጠት እርሱ እንዳደረገው ማድረግ እና በርህራሄ እና በይቅርባይነት ባልንጀሮቻችንን መርዳት አለብን” ብሏል ከአስራሁለቱ ሃዋርያት አንዱ የሆነው ሽማግሌ ዲይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፡፡ “ይህንን በቃልም በተግባርም በየቀኑ ልናደርገው እንችላለን፡፡ ይህ የገና ልማዳችን ይሁን፤የትም ሆንን የትም—ሻል ያልን ደጎች፤ይበልጥ ይቅር የምንል፣ፈራጅነታችን የቀነሰ፣ይበልጥ አመስጋኝ እና ለሚያስፈልጋቸው ከሃብታችን በማካፈል ረገድ ይበልጥ ለጋስ የሆንን፡፡”6

ማስታወሻዎች

  1. ሄነሪ ቢ.አይሪንግ “ የገና ታሪኮች (የመጀመርያ አመራር የገና ጉባኤ፣ ታህሳስ ፣ 6 ፣ 2009 እ.ኤ.አ)broadcasts.ChurchofJesusChrist.org

  2. የዳያና መሊና ዲያስ፣“Sharing Christmas,”ሊያሆናታህሳስ 2007፣17 ን ይመልከቱ፡፡

  3. የቼሪል ቦይልን “He Would Have Bought It for You,”ኢንዛይን ታህሳስ 2001፣57 ን ይመልከቱ፡፡

  4. የቦኒ ኤል.ስካርሰን “Christmas Is Christlike Love” (የመጀመርያ አመራር የገና ጉባኤ፣ ታህሳስ broadcasts.ChurchofJesusChrist.org 7, 2014),

  5. ዣን ቢ. ቢንግሃም፣ “Ministering as the Savior Does,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 104።

  6. ዲየተር ኤፍ.ኡክዶርፍ , “Scatter Your Crumbs” (የመጀመርያ አመራር የገና ጉባኤ፣ ታህሳስ ፣ 3 ፣ 2019 እ.ኤ.አ)broadcasts.ChurchofJesusChrist.org