2020 (እ.አ.አ)
በአገልግሎት እስራኤልን መሰብሰብ
ጥር 2020 (እ.አ.አ)


ምስል
ministering

የአገልግሎት መርሆች፣ ጥር 2020 (እ.አ.አ.)

በአገልግሎት እስራኤልን መሰብሰብ

አገልግሎት ነብያቶች ስለእስራኤል መሰባሰብ የሰጡትን መመሪያ ለመከተል ጥሩ እድል ነው፡፡

ፕረዘዳንት ራስል ኤም ኔልሰን እስራኤልን በመሰብሰብ እርዳታ እንድናደርግ ጋብዘውናል፤ “ዛሬ በምድር ላይ እየተካሄዱ ካሉ በጣም አስፈላጊው ነገር፡፡1

ለነዛ በእስራኤል መሰባሰብ ስራ ላይ መሳተፍ ለሚፈልጉ ፣ አገልግሎት ታላቅ እድል ሊሆን ይችላል፡፡ የሰዎችን ሕይወት ለመለወጥ ተነሳሽነት ያለው መንገድ ነው። ወይም ደካማ ተሳትፎ ላላቸው አባላት እያገለገልን አሊያም ከእምነታችን ውጪ የሆኑትን በምናገለግልበት ጊዜ እንዲረዱን ስንጋብዛቸው ፤ አገልግሎት እስራኤልን ለመሰብሰብ እድል ይሰጣል ፡፡

የተመለሱ አባላትን ማዳን

ፍቅር መነሳሻ ሆኖ፣ ተአምራቶች ይደርሳሉ፣ እናም ‘ይገኙ ያልነበሩትን’ እህቶች እና ወንድሞች ሁሉንም ወደሚያቅፍ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የምናመጣበትን መንገዶችን እናገኛለን።”2

እኔና ባለቤቴ ወደ አዲስ ከተማ በመጣን ግዜ ቢያንስ ለስድስት ዓመታት ያህል ንቁ ተሳታፊ አልነበርኩም። አዲሷ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዘዳንቴ ጎብኝታኝ ነበር ፤ አንድ እህት እኔን እንድትጎበኘኝ ልትልክልኝ እንደምትችል ለመጠየቅ። በጥቂት ፍርሃት ስሜት ፤ ተስማማሁ ፡፡ ይህቺ እህት በየወሩ ትጎበኘኛለች ለውሾች አለርጂ ብትሆንም - እና እኔ በጣም አፍቃሪ ውሻ አለኝ! አገልግሎቷ ለሁለት ዓመት ያህል ቀጠለ ፣ እናም በእኔ ላይ ትልቅ ተፅእኖ ነበረው ፡፡

ምንም እንኳን ጉብኝቷ ብዙውን ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ማህበራዊ ቢሆኑም አልፎ አልፎ የምትጠይቀኝ ጥያቄዎች ወደ መንፈሳዊ ውይይቶች ይመራን ነበር ። እነዚህ እኔን ትንሽ ምቾት ነስተውኝ ነበር ፤ነገር ግን በወንጌል ወደፊት መሄድን ወይም ባለሁበት እንድቆይ እንድወስን አነሳስተውኛል፡፡ይህ ውሳኔ ለእኔ ትግል ነበር፤ ነገር ግን እህቶች ሚስዮናውያን እንዲጎበኙኝ መረጥኩ::

በስድስት ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ለመከታተል በሄድኩበት ቀን ወደ ውስጥ ለመግባት ፈራሁ:: ወደ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስገባ የእኔ አገልጋይ እህት እየጠበቀችኝ ነበረች::እሷም ከእኔ ጋር ወደ ጸሎት ቤት አብራኝ ገባች ፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ መኪናዬ ሸኘችኝ ፤ ወደ አዳኝ እየቀረብኩ ስሄድ እኔን በተሻለ ለመርዳት ምን ማድረግ እንደምትችል ጠየቀችኝ።

የአገልጋይ እህቶች ጊዜ እና ፍቅር ወደ እንቅስቃሴ እንድመለስ ረድተውኛል ፤ እናም የእርሷን ጥረቶች ከተሰጡኝ ታላላቅ ስጦታዎች መካከል እንደ አንዱ አድርጌ እቆጥረዋለሁ። እሷ ወደ አዳኝ ቤተክርስቲያን ጉዞዪ ስመለስ ከጎኔ ስለነበረች በጣም አመስጋኝ ነኝ፡፡በብሪትሽ ኮሎምቢያ ካናዳ ስም ፣አልተገለጸም፣

ሊታሰብባቸው የሚገቡ መመሪያዎች

“በየወሩ ትጎብኝኛለች”

ከሌሎች ነገሮች ይልቅ ለምታገለግሏቸው ሰዎች እንደምታስቡ እንዴት ማሳየት ትችላላችሁ?ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 121፤44

“ጥያቄ”

ትክክለኛ ጥያቄዎችን መጠየቅ ራስን መመርመርን ለማነሳሳት ይረዳል ፡፡ አገልግሎታችን ከማኅበራዊ ጉዳዮች በላይ የሆነ ዓላማ እንዳለው አስታውሱ::3

“እኔን መጠበቁ”

ሁሉም ሰው ተቀባይነትን እንዳገኘ ሊሰማው ይገባል:: 3 ኔፊ 18፤32

”በመመለሰስ ጉዞዬ እዛ ከጎኔ ነበሩ ፡፡”

ወደ አዳኙ ለመመለስ እና ለመዳን ለተሰናከሉት የእኛ ድጋፍ ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል::

አገልግሎት እና መሰባሰብ

“በየትኛውም መንገድ ለእናንተ ተፈጥሯዊ እና የተለመዱ ቢመስሉም ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ቤተክርስቲያኑ ለምን ለእናንተ አስፈላጊ እንደሆኑ ለሰዎች አካፈሉ…

የእናንተ ተግባር በልባችሁ ውስጥ ያለውን ማጋራት እና እምነታችሁን በወጥነት መኖር ነው፡፡” ሽማግሌ ዲተር ኤፍ ኡክዶርፍ 4

አገልግሎት እና ወንጌልን ማካፈል እጅ አብረው ይሄዳሉ። በአገልግሎታችን ጓደኞቻችንን እና ጎረቤቶቻችንን መሰብሰብ የምንችልባቸው ወይም ጓደኞቻችንን እና ጎረቤቶቻችንን በምንሰበስብበት ጊዜ የምናገለግልባቸው አንዳንድ መንገዶች እዚህ አሉ፡፡

  • በጋራ አገልግሉ ። ጓደኞቻችሁን ወይም ጎረቤቶቻችሁን ለመጋበዝ አጋጣሚዎችን ፈልጉ ፤ አንድ መረዳት የሚፈለግ ሰውን ለማገልገል ከእናንተ ጋር ውሰዷቸው። ለአዲስ እናት ምግብ ለማዘጋጀት እንዲረዷችሁ ጠይቋቸው ፤ አዛውንት ጎረቤቶቻችሁን ጎብኙ ወይም የታመመ ሰውን ቤት አፅዱ

  • በጋራ አስተምሩ። አዘወትሮ ቤተክርስቲያን የማይካፈል አንድ ጓደኛን ወይም ጎረቤትን ከሚስዮናውያን ጋር ለተገናኘ ሰው የሚስዮናዊ ትምህርትን በቤቱ እንዲያስተናግድ መጋበዝን አስቡበት፡፡

  • እርዳታ ፈላጊ ስታዩ ለሌሎች መድረስ። ወደ ቤተክርስቲያን ማጓጓዣ አቅርቡ። ልጆችን ወደ ወጣቶች ወይም ወደ ህጻናት ክፍል ዝግጀቶች ይጋብዙ። በሌሎች መንገዶች ማገልገል እና መሰብሰብ ይችላሉ?

  • ቤተክርስቲያኗ የሰጠችውን ግብዓቶች ተጠቀሙ ፡፡ ቤተክርስቲያኗ አባላት ወንጌልን ለማካፈል እንዲረዳቸው ለአባላት ብዙ ግብአቶችን ታቀርባለች። እስራኤልን በማህበረሰባችን ውስጥ መሰብሰብ እንደሚቻል ሀሳቦችን ለማግኘት በወንጌል ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ባለው “ሚስዮናዊ” ክፍል ውስጥ ፍለጋ ማካሄድ እና መጎብኘት ትችላላችሁ::ComeUntoChrist.org

ማስታወሻዎች

  1. ራስል ኤም ኔልሰን, “ለእስራኤል ተስፋ” (ታማኝ አለም አቀፍ ወጣቶች ፤ሰኔ 3, 2018), “HopeOfIsrael.ChurchofJesusChrist.org

  2. ጂን ቢ. ቢንገም፣ “አዳኝ እንደሚያደርገው ማገልገል፣” Liahona፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 106።

  3. “የአገልግሎት መርሆች፥ አገልግሎታችንን የሚቀይረው አላማ፣” በጥር 2019 (እ.አ.አ) ውስጥ ይመልከቱ።

  4. ዲየትር ኤፍ. ኡክዶርፍ, “Missionary Work: Sharing What Is in Your Heart፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና, ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 17)።

አትም