2020 (እ.አ.አ)
ራስን በመቻል በኩል ማገልገል
ነሐሴ 2020 (እ.አ.አ)


“ራስን በመቻል በኩል ማገልገል፣” ሊያሆና ፣ ነሐሴ 2020 (እ.አ.አ)

ምስል
አገልግሎት

የአገልግሎት መርሆች፣ ነሐሴ 2020 (እ.አ.አ)

ራስን በመቻል በኩል ማገልገል

ሌሎች ራሳቸውን እንዲችሉ በማድረግ መርዳት በጌታ መንገድ ማቅረብ እና ማገልገል ነው።

ብዙ የቤተሰባችን አባላት፣ ጓደኞቻችን እና ጎረቤቶቻችን የበለጠ ራሳቸውን የሚችሉ ለመሆን ፍላጎት አላቸው። የቤተክርስቲያኗን ራስን-የመቻል መነሳሳትን በመጠቀም፣ የቤተክርስቲያኗ አባላት “ታላቅ ተስፋ፣ ሰላም እናም እድገት” በሚያመጡት መርሆዎች ሌሎችን ሲባርኩ፣ ለመንከባከብ እና ለማገልገል እድሎችን እያገኙ ናቸው።1

“ቤት ነበርኩ”

በክሪሲ ኬፕለር፣ አሪዞና፣ ዩ.ኤስ.ኤ

ፍቺዬን ተከትሎ፣ ለስምንት ዓመታት በቤት ውስጥ የቤት እመቤት ከሆንኩ በኋላ ወደ ሥራ የምመለስበትን መንገድ ለማግኘት በምጥርበት ጊዜ በገንዘብ እቸገር ነበር። ምንም እንኳን ከወጣትነት ጀምሮ በቤተክርስቲያን ውስጥ እግሬን አስገብቼ ባላውቅም፣ እውነት እና እምነትን በመፈለግ፣ በመንፈሳዊነትም እቸገር ነበር።

አንድ እሑድ በቤተክርስቲያኗ ንቁ አባል በሆነችው በታላቋ እህቴ ፕሪሲላ ቤት ውስጥ ልብሴን አጥብ ነበር። እዚያ በነበርኩበት ጊዜ፣ ፕሪሲላ ከቤተሰቧ ጋር ወደ ቤተክርስቲያን እንድሄድ ጋበዘችኝ—ይህም ከ15 ዓመታት በላይ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የነበረኝ ግብዣ ነበር።

መጀመሪያ ላይ ፍቃደኛ አልነበርኩ፣ ነገር ግን ከዚያ በፊት በነበረው ምሽት ወደ እርሱ እንዴት መቅረብ እንደምችል እንዲያሳየኝ እግዚአብሔርን ለምኜ ነበር። የውስጣዊ የመጎተት ስሜት ከተሰማኝ በኋላ፣ “በአዋቂነትሽ በገዛ ልብሽ እና ዐይንሽ ለመስማት እና ለማየት ለምን አትሄጂም?” ብዬ የመጨረሻ ውሳኔ አደረኩኝ።

በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ እያለን፣ በእሁድ ማስታወቂያ ላይ የግል ገንዘብ መቆጣጠርን በሚመለከት ራስን የመቻል ትምህርትን የሚያስተዋውቅ በራሪ ጽሑፍ አስተዋልኩኝ። ወደ ቤተክርስቲያን ለመመለስ ዝግጁ አልነበርኩም፣ ነገር ግን ወደ 12-ሳምንት ትምህርቱ የሚስብ ስሜት ተሰማኝ። በእህቴና በባለቤቷ ማበረታቻ፣ በጀት መመደብ እና ዕዳን እንዴት እንደሚከፈሉ ብቻ ለመማር በመጠበቅ ተመዝገብኩኝ። ነገር ግን፣ ትምህርቶቹ በመንፈሳዊው ቀየሩኝ።

በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንት የክፍል ትምህርቶች መንፈሳዊ መልእክቶች ተገርሜ ነበር፣ ነገር ግን በሦስተኛው ክፍል ውስጥ፣ ቤት እንደሆንኩ እና አዲስ ቢሆኑም የተለመዱ የማውቃቸውን እውነቶች እንደሰማሁ በሚያረጋግጥ ስሜት ተሞላሁ። ከክፍሉ ወጣሁ እና ፕሪሲላን ለማየት በቀጥታ ሄድኩ። እያለቀስኩም፣ “በሕይወቴ ውስጥ ይህን አይነት ስሜት እንዴት ማግኘት እችላለሁ?” ብዬ ጠየቅኋት። ሚስዮናውያን እኔን ማስተማር እንዲጀምሩ ዝግጅት አደረገች።

የእኔ ራስን-መቻል ክፍል አባላት ወደ ሚሲዮናዊ ትምህርቶቼ መጥተው ይረዱኝ ነበር። በመንፈሳዊነቴ ላይ ዘላቂ ተፅእኖ አሳድረዋል እናም የወንጌልን እና የዘመኑ ነቢያትን ምስክርነት እንዳዳብር አግዘውኛል።

ትምህርቱን ለማጠናቀቅ በወሰደኝ ጊዜ፣ ብዙ ጊዜያዊ እና መንፈሳዊ ለውጦችን አደረግሁ። በጥሩ ኩባንያ ውስጥ አዲስ ሥራ ጀመርኩ፣ እናም በርካታ ብድሮችን ከፈልኩኝ።

ነገር ግን ከትምህርቱ የመጡት ጥልቅ፣ ውድ በረከቶች ቢኖርም የሚያምር ጓደኝነትን መፍጠር፣ ከሚያበረታታ ኤጲስ ቆጶስ ጋር መልካም ግንኙነትን ማጎልበት፣ የአስራት ምስክርነትን ማግኘትን፣ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድን መቀበል፣ መንፈሳዊ ስጦታን መቀበል፣ እና ሁለቱ ታላላቅ ልጆቼ ሲጠመቁ ማየት ነበሩ።

የራስን-መቻል ጉዞዬ አሁንም እየተከፈተ ነው፣ ለተቀረው ጉዞዬ ግን ለተማርኳቸው ትምህርቶች እና ለነበሩኝ ጓደኝነቶች ከፍተኛ ዋጋ እሰጣለሁ።

“ከእያንዳንዱ ክፍልም እንደምወደድ ስሜት እየተሰማኝ እወጣለሁ”

በታህሳስ 2016 (እ.አ.አ)፣ በሶልት ሌክ ሲቲ፣ ዩታ ውስጥ የቤተመቅደሱን አደባባይ በጎበኘችበት ወቅት፣ ከ10 ዓመት ልጅዋ ቪንሰንት ጋር ኬቲ ፋንክ ስለእራሷ “ምቾት ያላት ተጠራጣሪ” ነኝ ብላ ታስብ ነበር። በቤተክርስቲያኗ ተሳታፊነትን ያቆመችውም በ16 ዓመቷ ነበር፣ በ17 ዓመቷ ያላገባች እናት ሆነች፣ መነቀስ ጀመረች፣ እናም ለቡና ጣዕምም አዳበረች። ነገር ግን በዚያ የቤተመቅደስ አደባባይ ጉብኝት ወቅት፣ ቪንሰንት መንፈስ ቅዱስ ተሰማው እናም የወንጌል ሰባኪዎችን ትምህርት መውሰድ ይችል እንደሆነ እናቱን ጠየቃት።

በሳምንት ውስጥ 80 ሰዓት የሚያሰሯት ሁለት ስራ የምትሰራ ብትሆንም፣ ለጥያቄዎቹ መልስ ለማግኘት በመፈተሽ ኬቲ ከቪንሰንት ጋር ወንጌልን አጠናች። በ2017 (እ.አ.አ) የበጋ ወቅት፣ በቤተክርስቲያኗ ስብሰባዎች ላይ መገኘት ጀመረች፣ በዚያም ስለ ቤተክርስቲያኗ የራስን-መቻል ትምህርቶች ተማረች።

“እኔን ሊረዱኝ የሚችሉ ነገሮች እንደሆኑ ተገነዘብኩ” አለች። “ምናልባት እስከ ሕይወቴ ሙሉ ሁለት ሥራ መሥራት ወይም በወላጆቼ ላይ በህይወቴ በሙሉ መመካት አያስፈልገኝም ይችል ይሆናል።”

ኬቲ ስለተማረችበት ብቻ ሳይሆን የራስን-መቻል ቡድኗ እንዴት እንደተቀበለባት እና እንዳገለገላትም ጭምር ምክንያት፣ ትምህርቷን “በሚያስደንቅ ሁኔታ በጊዜያዊ እና በመንፈሳዊ ሁኔታ አጠናካሪ” በማለት ጠርታለች።

ማስታወሻ

  1. “ከቀዳሚ አመራር መልእክት”፣ በPersonal Finances for Self-Reliance [ራስን-በመቻል የግል ገንዘብን መቆጣጠር] ውስጥ [2016 (እ.አ.አ)]፣ i።

አትም