2020 (እ.አ.አ)
በ ኑ፣ ተከተሉኝ በኩል ማገልገል
መስከረም 2020 (እ.አ.አ)


“በ ኑ፣ ተከተሉኝበኩል ማገልገል፣” ሊያሆና መስከረም 2020 (እ.አ.አ)

ምስል
አገልግሎት

የአገልግሎት መርሆች መስከረም 2020 (እ.አ.አ)

ኑ፣ ተከተሉኝበኩል ማገልገል

ኑ ፣ ተከተሉኝ በሌሎች ሕይወት ውስጥ ለውጥ እንዲያመጡ እንዴት ሊረዳዎት ይችላል?

ከቤተሰብዎ ጋር ይሁኑ፣ በሰንበት ትምህርት ቤት የትምህርት ክፍል ውስጥ እንደ አስተማሪ ወይም ተማሪ፣ ወይም በትምህርት ቤት፣ በሥራ ቦታ፣ ወይም በሌላ ቦታ፣ በ ኑ ፣ ተከተሉኝ በኩል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሌሎችን ለማገልገል በርካታ ዕድሎችን ይሰጣል። ከሁሉም በላይ፣ ማስተማር “እሁድ እለት ውይይት ከመምራት የበለጠ ነው፤ በፍቅር ማገልገል እና ሌሎችን በወንጌል መባረክን ያካትታል።”1

ከተማሪዎች ጋር ስምሙ መሆን

ኦፊሊያ ትሬሆ ዴ ካርዴናስ በሜክሲኮ ሲቲ ክፍሏ ውስጥ ወጣቶችን እንድታስተምር በተጠራችበት ጊዜ፣ ከእያንዳንዳቸው የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎቿ ጋር መቀራረቧ የማስተማር ችሎታዋን በመጨመር እነሱን እንደሚያጠነክራቸው ተሰማት።

“ከተማሪዎቼ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ከሌለኝ እና ፍቅሬ ካልተሰማቸው፣ አንድ ክፍል ሳስተምር ወይም ምስክርነቴን ስሰጥ ላያምኑኝ ይችላሉ፣” ትላለች። “የሰንበት ትምህርት ቤት መምህር ብቻ እንደሆንኩ ሊሰማቸው ይችላል።”

ነገር ግን እህት ካርዴናስ በየሁለት ሳምንቱ አንድ ጊዜ ብቻ የምታስተምር ከሆነ እንዴት እንደዚህ አይነት ግንኙነትን ልታዳብር ትችላለች? መልሱን በቴክኖሎጂ በኩል አገኘችው። WhatsApp የተሰኘውን የሞባይል ስልክ መተግበሪያ በመጠቀም፣ እሷና ተማሪዎችዋ ትንሽ ቆይተው በፅሁፍ እና በድምጽ መልእክቶች በየቀኑ እየተገናኙ ነበር። አሁን፣ ከሚቀጥለው ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት በፊት በየቀኑ፣ አንድ የክፍል ፈቃደኛ ለሌሎቹ የክፍል አባላት ከቀጣዩ ትምህርት ላይ አንድ የመፅሐፍ ጥቅስ ከተዛማጅ ግላዊ አስተሳሰብ ጋር ይልካል። ጥቅሱን እና ሀሳቡን ካነበቡ በኋላ፣ የክፍል አባላት ከራሳቸው ሀሳቦች ጋር ምላሽ ይሰጣሉ።

እህት ካርዴናስ፣ “መጽሐፉን ሲያነቡ፣ መጽሐፉን እንዳነበቡ ወይም እንዳጠኑት እና ስለሱ እንዳሰቡ እንዳውቅ የደስታ ፊት ምልክት ይልካሉ፣” ትላለች። የሚቀጥለው እሑድ ትምህርት ጊዜ ሲሆን፣ ተማሪዎቹ ለመሳተፍ ዝግጁ ናቸው።

ይህ ዕለታዊ ግንኙነት በቅርብ ጊዜ እንድ ወላጆቹ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የማይሳተፉ ወጣት አዋቂን ባርኳል።

እህት ካርዴናስ፣ “ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጣ ስመለከት በጣም ደስ ይለኛል ምክንያቱም እዚያ ለመድረስ፣ ብዙ ፈተናዎችን ማለፍ እንደነበረበት አውቃለሁ፣” ትላለች። “የክፍል ጓደኞቹ የላኳቸው ጥቅሶች እና ሀሳቦች እንዲሁም በተራው እሱ የላካቸው ጥቅሶች እና ሀሳቦች ብዙ እንዳጠነከሩት እርግጠኛ ነኝ።”

እህት ካርዴናስ በቅዱሳት መጻህፍት በኩል ማገልገል በእሁድ ትምህርቷ እና በክፍሏ የዕለት ተዕለት የቅዱስ ጽሑፋዊ ግንኙነት ብቻ አያቆምም ትላለች።

“ዝግጅቴ ለተማሪዎቼ መጸለይን ያካትታል፣” ትላለች። “ስለእነሱ እሁድ ብቻ ሳይሆን በሳምንቱ ባሉት በሁሉም ቀናትም አስባለሁ። እያንዳንዳቸው ልዩ እና የተለያዩ ፍላጎቶች አሏቸው። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ትምህርቶቼን በማዘጋጅበት ጊዜ ስለእነሱ አስባለሁ።”

እና ስታስተምር፣ ታዳምጣለች—ተማሪዎችዋን እና መንፈስ ቅዱስን።

በተማሪዎቿ ድምፆች በኩል ብዙውን ጊዜ የምትሰማው፣ “አስተማሪውን መንፈስ ነው።” “ትኩረት መስጠት አለብኝ ምክንያቱም የሚሉት ነገር መንፈስ ቅዱስ የሚሰጣቸውን መገለጥ ነው።”

ክፍላችን “እንደ የቤት ምሽት” ነው።

ካርላ ጉቴሬዝ ኦርቴጋ ኮርዶባ በተንከባካቢ እና አገልጋይ አካባቢው ምክንያት የእህት ካርዴናስ የሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል አባል በመሆኗ እንደተባረከች ይሰማታል። ካርላ ያ አካባቢ የሚከተሉትን ጨምሮ፣ በበርካታ ምክንያቶች ላይ የተመሠረተ እንደሆነ ታምናለች፡

  • ዝግጅት፦ ጥቅሶችን እና ሀሳቦችን ማካፈል ተማሪዎች ለሚቀጥለው ክፍል እንዲዘጋጁ ይረዳቸዋል። “የዕለት ጥቅሶች ይጠግኑናል እንዲሁም እውቀታችንን ያሰፉታል፣” ስትል ትገልጻለች።

  • ተሳትፎ፦ “ሁላችንም እንናገራለን። ይህ የክፍል ጓደኞቼን፣ እንደ ጓደኞች እና እንደ ወንድሞች እና እህቶች፣ በጥልቀት እንዳውቅ አስችሎኛል።”

  • ፍቅር፦ “እህት ካርዴናስ እጃችሁን ትይዛችኋለች። ክፍላችን ከብዙ ወንድሞችና እህቶች ጋር፣ የቤት ምሽት እንደሆነ ይሰማል። በጣም ልዩ ነው።”

  • መንፈስ ቅዱስ፦ “እኛ ከመንፈሱ ጋር ስምሙ ስለሆንን በክፍላችን ውስጥ አስደሳች፣ የስምምነት መንፈስ አለን።”

  • ምስክርነት፦ “ኑ ፣ ተከተሉኝ ምስክርነቴን ለማካፈል ዝግጁ እንድሆን ረድቶኛል። ስለ መፅሐፈ ሞርሞን እና ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ጥልቅ እውቀት አለኝ። ያ የተማርኩትን በትምህርት ቤት አብረውኝ ለሚማሩ እና በሥራ ቦታ ላሉት ሰዎች ለማካፈል ያስችለኛል።”

ለመንፈሳዊ ፍላጎቶች ማገልገል

በዩናይትድ ስቴትስ፣ ኬንታኪ፣ ግሬግ እና ኒኪ ክሪስተንሰን ከሶስት ወንድ ልጆቻቸው ጋር በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ስለ አብርሃም ቃልኪዳን ሲያነቡ፣ ለእነርሱ መግለፅ ከባድ ሆኖባቸው ነበር። እንደ ቤተሰብ እያንዳንዳቸው የአብርሃም ቃል ኪዳንን በራሳቸው ለማጥናት እና ያገኙትን ለማካፈል ወሰኑ።

ግሬግ፣ “አንዳንድ አስደሳች አስተያየቶች አግኝተናል፣” ይላል። “የስምንት ዓመት ልጃችን የአብርሃም ስም አብራም እንደነበረ እወቀ። ከኃጢአት ዘወር ለማለትና የጽድቅ ሕይወት ለመኖር ለፈጣሪ ቃል ስለገባ ስሙ ወደ አብርሃም ተቀየረ። እዚያ ውሳኔ ላይ መድረስ በመቻሉ በእውነቱ ተገርሜ ነበር።”

ሁሉም አዲስ ነገር ተማሩ እንዲሁም የአብርሃም ቃልኪዳን ምን እንደሆነ እና ዛሬ ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን ምን ማለት እንደሆነ ጥሩ ውይይት እደረጉ።

ኒኪ፣ “በክፍሉ ዙሪያ እየሄድን ለቤተሰብ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በየተራ እናነብ ነበር፣” ትላለች። “ኑ፣ ተከተሉኝ በመንፈስ በማስተማር ላይ የበለጠ ያተኮረ ነው። አሁን አብረን ስናጠና፣ በቤተሰባችን ፍላጎቶች ላይ በመመርኮዝ ውይይታችንን በሌላ አቅጣጫ ለመውሰድ ከመንፈሱ ትንሽ ግፊቶች ይሰሙኛል።”

ኑ፣ ተከተሉኝ ን መጠቀም ቤተሰባቸው በቤተሰብ ወንጌል ጥናት ውስጥ የበለጠ ተሳትፎ እና ፍላጎት እንዲኖረው መርዳት ብቻ ሳይሆን፣ ግሬግን እና ኒኪንም ለልጆቻቸው መንፈሳዊ ፍላጎት እንዲያገለግሉ ረድቷቸዋል።

ኑ፣ ተከተሉኝ ልጆቼን እንዳስተምር ይረዳኛል፣” ትላለች ኒኪ። “አንዳንድ ጊዜ ከልጆቼ ጋር የሚያጋጥሙኝን የተለያዩ ፈተናዎች እንድቋቋምም ይረዳኛል። ከመንፈሱ ጋር የበለጠ እንደተገናኘሁ ይሰማኛል፣ በጥሞና አዳምጣለሁ፣ እናም እያንዳንዱን ልጅ እንዴት መርዳት እንደምችል አቅጣጫዎች ደርሰውኛል።”

ግሬግ ኑ ፣ ተከተሉኝ በቤተሰብ ውስጥ እንዲመነጭ የሚረዳውን ረዥሞቹን የወንጌል ውይይቶች ይወዳቸዋል። “ሁሉም ወንድ ልጆቻችን በወንጌል ዕውቀታቸው ያሉበት ደረጃ የተለያየ ነው፣” ይላል. “ኑ፣ ተከተሉኝ እያንዳንዳቸውን በፍላጎታቸው መሰረት እንዲማሩ የምንረዳበትን መንገድ አቅርቦልናል። ለወንጌል ያላቸው ፍቅር እያደገ ሲሄድ እና የወንጌልን ዕውቀት በሕይወታቸው ውስጥ እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚችሉ ሲገነዘቡ መመልከቱ አስደናቂ በረከት ነበር።”

ማስታወሻ

  1. ኑ፣ ተከተሉኝ—ለሰንበት ትምህርት ቤት: መጽሐፈ ሞርሞን 2020 (2019) (እ.አ.አ)፣ 19።

አትም