“በገና በዓል የአዳኙን ብርሃን ማካፈል” ሊያሆና ታህሳስ 2020 (እ.አ.አ.)
የአገልግሎት መርሆች፣ ታህሳስ 2020 (እ.አ.አ.)
በገና በዓል የአዳኙን ብርሃን ማካፈል
የምታገለግሏቸውን ሰዎች አስቡ በዚህ የገና በዓል ወደ ክርስቶስ እንዲቀርቡ እንዴት ልትረዷቸው ትችላላችሁ?
አዳኙ ኢየሱስ ክርስቶስን ዓመቱን በሙሉ ማስታወሳችንእንዳለ ሆኖ፣ ገና እስከዛሬ ከተሰጡት ታላቅ የሆነውን ስጦታ የምናከብርበት ወቅት ነው፦ “እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና”ዩሐንስ 3፡16 በገና ስናገለግል፣ እኛም ሌሎች ወደ አዳኙ እንዲቀርቡ የሚረዳቸውን ስጦታዎች መስጠት እንችላለን። እራሳችንን በሰማይ አባት የተሰጠን ስጦታ እንደምናንፀባረቅ አድርገን ማሰብ ድንቅ ነው።
አሁንም ቢሆን ስጦታውን ከፍ አድርጌ እመለከተዋለሁ
ሱዛን ሀርዲ፣ ካሊፎርኒያ፣ አሜሪካ
የ 11 ዓመት ልጅ ሳለሁ፤ የሰንበት ትምህርት ቤት አስተማሪዬ፤ ወንድም ዲትስ ፣ የእምነት አንቀጾችን በቃላችን ብንይዝ እና ትርጉማቸው ምንእንደሆነ ለእሱ ብናስረዳ የራሳችንን የቅዱሳን መጻሕፍት ስብስብ እንደሚገዛልን ነገረን።
ወንድም እና እህት ዲትስ ገና ጀማሪ ወጣት ጥንዶች ነበሩ፡፡ ወንድም ዲትስ ለማንም ሰው ስጦታ የመግዛት አቅም እንደነበረው እርግጠኛ አልነበርኩም፡፡ ነገር ግን የእምነት አንቀጾችን ማስታወስ አስፈላጊ ነው ብሎ ካሰበ ፈተናውን እወስዳለሁ ብዬ ወሰንኩ።
13 ቱን ሁሉ ከጨረስኩ በኋላ ጊዜው ሄደ፣ እናም የገባውን ቃል ረሳሁት፡፡
ከዚያ በገና ቀን፣ ስሜን የያዘ አንድ እሽግ ተቀበልኩ። ከፈትኩትና የቅዱሳን መጻሕፍት ስብስብ ሁልጊዜ እንዳነባቸው ከሚያበረታታኝ ካርድ ጋር አገኘሁኝ፡፡ ያ በ1972 ነበር እናም እስከዛሬ ድረስ እነዚያ ቅዱሳን መጻሕፍት አሉኝ። እነሱ ለእኔ ውድ ናቸው፡፡
የስጦታው ዋጋ አልነበረም ነገር ግን እሱ ያሳየኝ ደግነት እና የእግዚአብሔርን ቃል ለማጥናት ከፍተኛ ፍላጎት እንዲያድርብኝ ያደረገውን ለእኔ ሲል ለመክፈልየፈቀደው መስዋእትነት እንጂ፡፡ በዙሪያዬ ላሉት ትርጉም ያላቸውን ስጦታዎች በመስጠት፣ የእኔን ሕይወት እንደባረከው የሌሎችን ሕይወት እንደምባርክ ተስፋ በማድረግ የወንድም ዲትስን የአገልጋይነት ምሳሌ ለመከተል እሞክራለሁ።
አንድ ክፍል እንዲጫወቱ የቀረበ ግብዣ
ሪቻርድ ኤም ሮምኒ፣ ዩታ፣ ዩኤሰኤ
የአጥቢያችንን የገና ማህበራዊ ዝግጅት እያቀዱ የነበሩት አንድን ንቁ ተሳታፊ ያልሆነ አባል እንድጎበኝና በፕሮግራሙ ውስጥ እንዲሳተፍ እንድጋብዘው ሲጠይቁኝ፣ በጣም ደንግጬ እንደነበረ ማመን አለብኝ፡፡ ዳረንን ከዚህ በፊት አንድ ጊዜ ብቻ አግኝቼው የነበረ ሲሆን እሱም ቀደም ብሎ ተከናውኖ በነበረው የአጥቢያ እንቅስቃሴ ተሳትፎ በነበረበት ጊዜ ነበር፡፡ በግንባሩ ላይ የሞተር ብስክሌት ሻሽ አስሮ ነበር፡፡ ረዥም ነጭ ፀጉሩ በፀጉር ማስያዣ ታስሮ ነበር፣ ሙሉ ነጭ ጢም ነበረው፣ እንዲሁም ክንዶቹ በንቅሳት ተሸፍነው ነበር።
አሁን ምን ሊል እንደሚችል በማሰብ ከኮሚቴ አባል ጋር በመሆን በዳረን በር ላይ ቆሜ ነበር፡፡ ወደ ውስጥ እንድንገባ ጠየቀን እናም እዚያ ለምን እንደመጣን ነገርነው፡፡ እሱም “ኦህ፣ ያንን ማድረግ እፈልጋለሁ!” አለ፡፡
እንቅስቃሴውን ለብዙዎች ትርጉም እንዲኖረው በማገዝ አስገራሚ ሥራን ሠራ፡፡ ከአጭር ጊዜ በኋላ እኔና የአገልግሎት ጓደኛዬ ዳረንን አዘውትረን እንድንጎበኝ ተጠየቅን። እሱ እኛን ሲያየን ሁልጊዜ ደስ የሚለው ይመስል ነበር፣ እና አንዳንድ አስደሳች ውይይቶችም አድርገናል። ከፍ ያለ ግምት ወደሚሰጠው ግንኙነት ስለመራን በአጥቢያ እንቅስቃሴ ፕሮግራሙ ውስጥ እንዲሳተፍ ለመጋበዝ መነሳሳትን በማግኘታችን አመስጋኝ ነኝ።
በገና በዓል ላይ ሌሎችን ማገልገል
የሚያገለግሏቸው ሰዎች እያሰቧቸው መሆንዎን ማወቅ እንዲችሉ የሚያደርጉ አንዳንድ ነገሮች እነሆ፣ በተለይ በዚህ የዓመቱወቅት፡፡
-
አንዳንድ ጊዜ የስልክ ጥሪ ወይም የጽሑፍ መልእክት በሚያስደንቅ ሁኔታ ይሠራል። “ታዲያስ፣ እንዴት ነህ?” በሚል ቀለል ያለ ቃል ውይይትን መጀመር ልዩነት ሊፈጥር ይችላል።
-
ተገቢ በሚሆንበት ጊዜ በበዓላቸው ላይ ይሳተፉ። ገና በጋራ ስላሉን እምነቶች ለመማር አስደሳች ጊዜ ሊሆን ይችላል፡፡ እምነቶችን ለሌሎች ሲያካፍሉ እና ሌሎችን ሲያዳምጡ ለበለጠ ግንዛቤ በር ይከፍታሉ፡፡
-
ለእነሱ በስም ጸልዩላቸው። ወደ ልጁ ለመቅረብ የሚያስችሏቸውን መንገዶች እንዲያስቡ እንዲረዳዎት የሰማይ አባትን ይጠይቁ።
-
ቀላል ስጦታዎች ብዙውን ጊዜ በተሻለ ይታወሳሉ። ስጦታዎች ለመወደድ የረቀቁ መሆን የለባቸውም። የጊዜ ስጦታ፣ የማዳመጥ ስጦታ፣ የፎቶ ወይም የትውስታ መጋራት—እነዚህ ሁሉ የልብ ስጦታዎች ሊሆኑ ይችላሉ።
-
የምስክርነት ስጦታ ይስጡ፡፡ ለአዳኙ ያላቸውን ፍቅር ለእርስዎ እንዲያጋሩዎት ጠይቋቸው እናም ለእሱ ያለዎትንን ፍቅር ለእነሱ አካፍሉ፡፡
-
ሌሎች በገና አገልግሎት ላይ እንዲገኙ ይጋብዙ። አንዳንድ ሰዎች ማምለክ ይፈልጋሉ ነገር ግን ወዴት መሄድ እንዳለባቸው አያውቁም፡፡ እንዲመጡ እና ከአንተ ጋር እንዲያመልኩ ጋብዟቸው።
-
ቤታቸውን በሰላም ይሙሉ፡፡ በልባቸው ውስጥ ተስፋን እና ፍቅርን የሚያመጣ ሚስዮናውያን ሊያካፍሏቸው የሚችሉት ልዩ የገና መልእክት እንዳላቸው አሳውቋቸው።
እንደ አንድ ጉባኤ ሁሉንም ማገልገል
የእያንዳንዱ ጉባኤ ፍላጎቶች ልዩ ናቸው። አንዳንዶች ትልቅ እንቅስቃሴ በማደራጀት ይጠቀማሉ፡፡ ሌሎች ጉባኤዎች አነስተኛ እና ቀላል ከሆነው ጥቅም ሊያገኙ ይችሉ ይሆናል፡፡ እንቅስቃሴዎችን በማቀድ እና በማደራጀት ላይ የሚሳተፉ ሰዎች በጸሎት መንፈስ ያሉትን ፍላጎቶች እንዴት ማሟላት እንዳለባቸው ያስባሉ፡፡
-
በፓሪስ፣ ፈረንሳይ ውስጥ ከሦስቱ ካስማዎች የተውጣጡ አባላት ተሰጥኦ ማሳያ እና የፋሽን ትርዒትን ያካተተ የብርሃን ለዓለምን ሶአሬ ለመደገፍ አግዘዋል፡፡ ለስደተኞች እና በጎዳና የመኖር እጣ ለገጠማቸው ሰዎች የተሰጡ እቃዎችን አዘጋጅተው ነበር፡፡
-
ክርስቶስን በምግብ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በገና ወግ ማሳያዎች፣ በሙዚቃ፣ በአገልግሎት ፕሮግራሞች እና በልጆች ልደት ማህበራዊ ተግባሮች የሻርሎት ሰሜን ካሮላይና ማዕከላዊ ካስማ ለማህበረሰቡ የ“ገና በዓለም ዙሪያ ” ዝግጅት አከበረ፡፡
-
የቬሮ የባህር ዳርቻ ፍሎሪዳ ካስማ አባላት ገናን ለምን እንደምናከብር በሚያስታውስየማህበረሰብ ማሳሰቢያ ውስጥ ተቀላቀሉ፡፡ አሻንጉሊቶች ለማህበረሰብ በጎ አድራጎቶች ተሰጡ፡፡ የልጆች የመዘምራን ቡድን ዝግጅቱን አቅርቦ ነበር፣ እንዲሁም ብዙ አብያተ-ክርስቲያናት መረጃ የሚያሳዩ ዳሶች ነበሯቸው።
-
የጃክሰንቪል ፍሎሪዳ ደቡብ ካስማ የአለም አዳኝ ሙዚቃዊ ድራማለማህበረሰቡ አቀረቡ።
© 2020 (እ.አ.አ) በ Intellectual Reserve, Inc. መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፥ 6/19 (እ.አ.አ)። ትርጉም የተፈቀደበት፥ 6/19 (እ.አ.አ)። የአገልግሎት መርሆች፣ ታህሳስ 2020 (እ.ኤ.አ) ትርጉም። ቋንቋ። 16727 506