“የልጆች ንጥረ ምግብ አመጋገብ፣” የልጆች ንጥረ ምግብ አመጋገብ [2023 (እ.አ.አ)]
የልጆች ንጥረ ምግብ አመጋገብ
እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል፣ በአለም ዙሪያ ያሉትን ሁሉንም የእግዚአብሔር ልጆች ለመንከባከብ ቃል ገብተናል። ልጆች ሙሉ አቅማቸው ላይ እንዲደርሱ ማገልገል እና ማሳደግ ግባችን ነው። የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት ካሚል ኤን. ጆንሰን፣ “የተራቡትን ከመመገብ የበለጠ ለክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሰብአዊ ጥረት የለም። “ከአስደናቂ ድርጅቶች ጋር ለመተባበር እና ለህጻናት እና ለወጣት እናቶች እርዳታ ለመስጠት የሚያስችል መንገድ በማግኘታችን አመስጋኞች ነን። አብረን ስናገለግል፣ የክርስቶስ አፍቃሪ ክንዶችን ተደራሽነት እናሰፋለን” በማለት ተናግረዋል።
በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት በአለም ላይ ብዙ ህፃናት ይሰቃያሉ። ልጆች፣ በተለይም ከተፀነሱበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሁለት ወይም ሶስት አመት ድረስ፣ በቂ ንጥረ ምድብ መመገብ ያስፈልጋቸዋል። የሚመገቧቸው ምግቦች ንጥረ ነገሮች ለትክክለኛ አንጎል፣ አካል እና የበሽታ መከላከያ ስርዓት እድገት ወሳኝ ናቸው። ይህ ወቅት ለልጅ እድገት በጣም ወሳኝ በመሆኑ፣ ቤተክርስቲያኗ የተመጣጠነ ምግብ፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ፣ በድገፋ የአካባቢ የህክምና አገልግሎት እና ሌሎች ህጻናት በትክክል እንዲያድጉ የሚረዱ ነገሮችን በማቅረብ ብዙ ህጻናት የተመጣጠነ የንጥረ ምግብ እንክብካቤ እርዳታ እንዲያገኙ የመርዳት ጥረቶች ላይ ትኩረት አድርጋለች።
በጣም የተሳካላቸው የንጥረ ምግብ ፕሮግራሞች የሚሰሩት በአካባቢው ማህበረሰብ ውስጥ በተለይም በሴቶች ተሳትፎ መሰረታዊ ጥረት ነው። እነዚህን ዓይነት መፍትሄዎች ለማቅረብ ቤተክርስቲያኗ በልዩ ሁኔታ በአጥቢያ ሸንጎ፣ በአገልግሎት እና በሴቶች መረዳጃ ማህበር ተደራጅታለች። በተጨማሪም፣ ቤተክርስቲያኗ ለተቸገሩ ህፃናት ሁሉ የንጥረ ምግብ አመጋገብን ለማሻሻል ከአለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ትሰራለች።
ስለ ልጆች ንጥረ ምግብ አመጋገብ፣ ይህ ቤተሰባችን ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያሳድር እና የቤተሰባችሁን ንጥረ ምግብ አመጋገብ እንዴት ማሻሻል እንደምትችሉ የበለጠ ለመረዳት ከታች ባለው መገናኛ ውስጥ ያለውን መረጃ ተጠቀሙ።