የሴቶች መረዳጃ ማህበር እና የሽማግሌዎች ቡድን
የአጠቃላይ ጉባኤ መልዕክቶችን ማስተማር፣ መማር እና መተግበር


ኑ፣ ተከተሉኝ

የአጠቃላይ ጉባኤ መልዕክቶችን ማስተማር፣ መማር እና መተግበር

የሽማግሌዎች ቡድን እና የሴቶች መረዳጃ ማሀበራት በመዳን እና በዘላለማዊ ህይወት የማደግ ስራ ውስጥ ጠቃሚ ሚና ይጫወታሉ። በእሁድ ስብሰባቸው በዚህ ስራ ጥረታቸው ውስጥ የቅርብ ጊዜ የአጠቃላይ ጉባኤ መልዕክቶችን እንዴት ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ይወያያሉ። የሽማግሌዎች ቡድን እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራሮች የአባሎችን ፍላጎት እና የመንፈስ ቅዱስን ምሪት መሰረት በማድረግ በእያንዳንዱ የሰንበት ስብሰባ እንዲማሩ አንድ የጉባኤ መልዕክትን ይመርጣሉ። አልፎ አልፎ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማው ፕሬዚዳንት መልዕክት ሊጠቁምም ይችላል። በአጠቃላይ፣ መሪዎች መልዕክቶችን የቀዳሚ አመራር እና የአስራሁለቱ ሐዋርያት አባላት ካቀረቧቸው መካከል መምረጥ አለባቸው። ይሁን እንጂ፣ ከቅርቡ አጠቃላይ ጉባኤ ማንኛውንም መልዕክት መወያየት ይችላል።

አስተማሪዎች የአጠቃላይ ጉባኤ መልዕክቶችን አባላት በሕይወታቸው ውስጥ እንዴት ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በመርዳት ላይ ያተኩራሉ። መሪዎች እና አስተማሪዎች አባላት ከስብሰባው አስቀድሞ የተመረጡ መልዕክቶችን እንዲያጠኑ የማበረታቻ መንገዶችን ይፈልጋሉ።

ስለካህናት ቡድን እና ስለሴቶች መረዳጃ ማህበር ስብሰባዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት General Handbook: Serving in The Church of Jesus Christ of Latter-day Saints፣ 8.2.1.29.2.1.2ChurchofJesusChrist.orgይመልከቱ።

ለማስተማር ማቀድ

አስተማሪዎች የአጠቃላይ ጉባኤ መልዕክትን ለማስተማሪያነት ለመጠቀም ሲያቅዱ የሚከተሉት ጥያቄዎች ሊረዷቸው ይችላሉ። እንደ አስፈላጊነቱ፣ አስተማሪዎች እነዚህን ጥያቄዎች ሲያሰላስሉ፣ ከሽማግሌዎች ቡድን ወይም ከሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር ጋር ይማከራሉ።

  • የሽማግሌዎች ቡድን ወይም የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር ይህን መልዕክት ለመወያየት ለምን መረጡ? ይህንን መልዕክት አባሎች ከተወያዩ በኋላ ምን እንዲያውቁ እና እንዲያደርጉ ተስፋ ያደርጋሉ?

  • ተናጋሪው አባላት ምን እንዲረዱ ይፈልጋል? የሚያስተምረን ወይም የምታስተምረን የትኛውን የወንጌል መርሆ ነው? እነዚህ መርሆዎች ለሽማግሌዎች ቡድን ወይም ለሴቶች መረዳጃ ማህበር እንዴት ተግባራዊ ይሆናሉ?

  • ተናጋሪው/ዋ መልእክቱ/ቷን ለማጠናከር የትኞቹን ቅዱሳን ጽሁፎች ነው የተጠቀመው/ችው? የአባላትን ግንዛቤ ጥልቅ የሚያደርጉ ሊያነቡት የሚችሉት ሌሎች ቅዱሳን ጽሁፎች አሉን? (ጥቂቶቹን ከመልዕክቱ የመጨረሻ ማስታወሻዎች ውስጥ ወይም በቅዱሳት መጽሐፍት መምሪያው ውስጥ ልታገኙ ትችላላችሁscriptures.ChurchofJesusChrist.org]።)

  • አባላት በመልዕክቱ ላይ እንዲያሰላስሉ እና ተግባራዊ እንዲያደርጉ የሚረዱ ምን አይነት ጥያቄዎች ልጠይቅ እችላለሁ? እነዚህ ትምህርቶች በራሳቸውና በቤተሰባቸው ህይወት እንዲሁም በጌታ ስራ ውስጥ ያለውን ተገቢነት ማየት እንዲችሉ ምን አይነት ጥያቄዎች ሊረዷቸው ይችላሉ?

  • መንፈስን ወደ ስብሰባችን ለመጋበዝ ምን ማድረግ እችላለሁ? ታሪኮችን፣ ምስያዎችን፣ ሙዚቃዎችን ወይም የስነጥበብ ስራዎችን ጨምሮ ውይይቶችን ለማሻሻል ምን ልጠቀም እችላለሁ? ተናጋሪው አባላት የእሱን ወይም የእሷን መልዕክት እንዲረዱ ምን አደረገ/ገች?

  • ተናጋሪው ግብዣዎች አድርጓል? አባላት በቀረቡት ግብዣዎች ላይ ተግባራዊ እርምጃ የመውሰድ ፍላጎት እንዲሰማቸው እንዴት ልረዳቸው እችላለሁ?

ለእንቅስቃሴ የሚሆኑ ሃሳቦች

አባላት የአጠቃላይ ጉባኤ መልዕክቶች መማር እና መተግበር እንዲችሉ ለመርዳት የሚቻልባቸው አስተማሪዎች ማድረግ የሚችሉት ብዙ መንገዶች አሉ። ጥቂት ምሳሌዎች እነሆ፤ በሽማግሌዎች ቡድን ወይም በሴቶች መረዳጃቸው ውስጥ በተሻለ ሁኔታ ሊሰሩ የሚችሉ ሌሎች ሀሳቦች አስተማሪዎች ሊኖራቸው ይችላል።

  • እውነቶችን በሕይወታችን ላይ መተግበር። እንደግለሰቦች ወይም እንደ የሽማግሌዎች ቡድን ወይም እንደ የሴቶች መረዳጃ ማህበር እግዚአብሔር የሰጣቸውን ስራ ለማከናወን መርዳት የሚችሉ እውነታዎችን እንዲመለከቱ አባላትን የጉባኤ መልዕክትን እንዲከልሱ ጋብዙ። ለምሳሌ፣ እንደ አገልጋዮች፣ እንደ ወላጆች፣ እንደ የአባል ሚስዮናዊ ሊረዱን የሚችሉ ምን እንማራለን? ይህ መልዕክት በአስተሳሰባችን፣ በስሜታችን እና በተግባራችን ላይ እንዴት ተፅዕኖ ያደርጋል?

  • በቡድን መወያየት። አባላትን በትንንሽ ቡድኖች ከፋፍሉ ከዚያም እያንዳንዱ ቡድን የተለያየ የጉባኤውን መልዕክት ክፍል እንዲያነብ እና እንዲወያይ መድቡ። ከዚያም እያንዳንዱ ቡድን ስላገኙት አንድ እውነት እና እንዴት ለእነሱ ተግባራዊ እደሚሆን እንዲያካፍሉ ጠይቁ። ወይም የመልዕክቱን የተለያዩ ክፍሎችን ባጠኑ አባላት የተመሰረተ ቡድኖችን መፍጠር እና ያገኙትን እርስ በእርስ እንዲያካፍሉ ማድረግ ትችላላችሁ።

  • ለጥያቄዎች መልስን ፈልጉ። አባላቶት ስለ ጉባኤው መልዕክት እንደዚህ ያሉ ጥያቄዎችን እንዲመልሱ ጋብዟቸው፦ በዚህ መልእክት ውስጥ ምን አይነት የወንጌል እውነት እናገኛለን? እነዚህን እውነቶች እንዴት ተግባራዊ ልናደርጋቸው እንችላለን? የትኞቹ ግብዣዎች እና ቃል የተገቡ በረከቶች ተሰጥተዋል? ይህ መልዕክት እግአብሄር እንድንሰራ ስለሚፈልግብን ስራ ምን ያስተምረናል? ወይም ስለ መልዕክቱ ወይም የሚያስተምረውን እውነታዎች ስለመተግር አባላት በጥልቀት እንዲያስቡ የሚያበረታቱ ግላዊ የተወሰኑ ጥያቄዎችን ፍጠሩ። አባላት ከእነዚህ ጥያቄዎች አንዱን እንዲመርጡ እና መልሱን ከመልዕክቱ እንዲፈልጉ ፍቀዱላቸው።

  • ከመልዕክቱ ዓረፍተ-ነገሮችን አካፍሉ። አባላት የመዳን እና የከፍ ማለትን ስራ ሃላፊነቶቻቸውን እንዲፈጽሙ የሚያነሳሷቸው ከጉባኤው መልዕክት የተገኙ ዓረፍተ-ነገሮችን እንዲያጋሩ ጋብዙ። እነዚህን ዓረፍተ-ነገሮችን ወዳጆቻቸውን እና የሚያገለግሏቸውን ሰዎች ጨምሮ አንድን ሰው ለመባረክ እንዴት ማካፈል እንደሚችሉ እንዲያስቡ አበረታቷቸው።

  • ቁሳቁስን በመጠቀም ትምህርት ማካፈል። በቅድሚያ ስለ ጉባኤው መልዕክት ለማስተማር ሊጠቀሙ የሚችሏቸው ቁሳቁሶችን ከቤታቸው እንዲያመጡ ጥቂት አባላትን ጋብዙ። በስብሰባው ወቅት እነዚህ ቁሳቁስ ከጉባኤው መልእክት ጋር እንዴት እንደሚያያዙ እና በሕይወታቸው ውስጥ እንዴት ተግባራዊ እንደሚያደርጉት እንዲያብራሩላችሁ አባላትን ጠይቁ።

  • በቤት ለማስተማር ትምህርትን ማዘጋጀት። አባላት በጉባኤው መልዕክት ላይ የተመሰረተ የቤት የምሽት ትምህርት እቅድ ላይ ጥንድ ጥንድ ሆነው እንዲሰሩ ጠይቋቸው። እንደነዚህ አይነት ጥያቄዎችን መመለስ ይችላሉ፦ መልዕክቱ ለቤተሰባችን የሚስማማ እንዲሆን እንዴት ማድረግ እንችላለን? ይህን መልዕክት ለምናገለግላቸው ሰዎች እንዴት ማካፈል እንችላለን?

  • ተሞክሮዎችን ማካፈል። ከጉባኤው መልእክት ብዙ ምንባቦቸን አብራችሁ አንብቡ። ከምንባቦቹ የተማሩትን ትምህርት የሚገልጹ ወይም የሚያጠናክሩ ምሳሌዎችን ከቅዱሳን ጽሁፎች እና ከህይወታቸው ውስጥ እንዲያካፍሉ አባላትን ጠይቋቸው።

  • ሃረግ መፈለግ። አባላት ለግላቸው ትርጉም ያላቸውን ሃረጎች በጉባኤ መልዕክቱ ውስጥ ለማግኘት ፍለጋ እንዲያደርጉ ጋብዟቸው። ሃረጎቹ ምን ምን እንደሆኑ እና ከእነሱ ምን እንደተማሩ እንዲያካፍሉ ጠይቋቸው። እነዚህ ትምህርቶች የጌታን ስራ ለማከናወን እንዴት እንደሚረዷቸው እንዲያካፍሉ ጠይቋቸው።

ከአጠቃላይ ጉባኤ መልዕክቶች ለጥናት እና ለማስተማር የሚሆኑ የበለጡ ሃሳቦችን ለማግኘት “Ideas for Learning and Teaching from General Conference” የሚለውን ይመልከቱ። (“Ideas for Study” በ “General Conference” ስር በወንጌል ቤተ መጽሐፍት ውስጥ ይጫኑ።)