“የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተክርስቲያን ማቋቋም፣” ጓደኛ፣ መጋቢት 2021 (እ.አ.አ)
ወርኃዊ የ ጓደኛ መልእክት፣ መጋቢት 2021 (እ.አ.አ)
የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተክርስቲያን ማቋቋም
ሚያዚያ 6 ቀን 1830 (እ.አ.አ) በአንድ የእንጨት ቤት ውስጥ ልዩ ስብሰባ ተደርጎ ነበር። ጆሴፍ ስሚዝ የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተክርስቲያን ዳግመኛ በምድር ላይ አቋቋማት።
ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውድሪ ቅዱስ ቁርባኑን ባርከው አስተላለፉ።
ስብሰባው ካበቃ በኋላ፣ በርካታ ሰዎች ተጠመቁ።
ከጥቂት ወራት በኋላ፣ ለቤተክርስቲያኗ የመዝሙር መጽሐፍ እንድታዘጋጅ እግዚአብሔር ኤማ ስሚዝን ጠራት። በዚህ መንገድ ሰዎች በቤተክርስቲያን ጉባዔዎች ወቅት መዘመር ይችላሉ።
እኔ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል ነኝ። መዝሙር መዘመር እና በየሳምንቱ ቅዱስ ቁርባንን መቀበል እችላለሁ።
© 2021 በ Intellectual Reserve, Inc. መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Friend Message, January 2021 ትርጉም። Amharic. 17466 506