“የጥበብ ቃል፣” ጓደኛ፣ ነሐሴ 2021 (እ.አ.አ)
ወርሃዊ የ ጓደኛ መልእክት፣ ነሐሴ 2021 (እ.አ.አ)
የጥበብ ቃል
ጆሴፍ ስሚዝ ሰዎችን ስለ ወንጌል ለማስተማር ስብሰባዎችን አካሂዷል። አንዳንድ ጊዜ ሰዎቹ ትምባሆ ያጨሱ እና ያኝኩ ነበር።
ይህም ኤማ ስሚዝን አሳስቧት ነበር። ጭሱ እና ትምባሆው ትልቅ ውጥንቅጥ ፈጠሩ እናም አንድ ትክክል ያልሆነ ነገር እንደነበረ ያስታውቅ ነበር። ኤማ እና ጆሴፍ እግዚያብሔር ስለዚህ ነገር እንዴት ይሰማዋል ሲሉ አሰቡ።
ጆሴፍ ጸለየ፣ እናም ጌታ መለሰ። ጌታ የቤተክርስቲያኗን አባላት ስለማጨስ እና ትምባሆ አስጠነቀቀ። ለሰውነታችን ጥሩ እንዳልሆኑ ተናገረ። ሻይ፣ ቡና፣ እና አልኮል ስለመጠጣትም አስጠነቀቀ።
ፍራፍሬ፣ አትክልት እና ሌሎች ጤናማ ምግቦችን እንዲበሉ እግዚአብሔር ተናገረ። እነዚህን ትምህርቶች የጥበብ ቃል ብለን እንጠራቸዋለን።
የጥበብ ቃልን ለመኖር እችላለሁ። ሰውነቴን ስንከባከብ የሰማይ አባት ይባርከኛል።
© 2021 by Intellectual Reserve, Inc. መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው። በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Friend Message, August 2021ትርጉም። Amharic. 17471 506