“ኤልያስ እና አነስተኛ ለስላሳ ድምፅ፣” ወርሀዊ የጓደኛ መልእክቶች፣ የካቲት 2022 (እ.አ.አ)
“ኤልያስ እና አነስተኛ ለስላሳ ድምፅ”
ወርሃዊ የ ጓደኛ መልእክት፣ ሐምሌ 2022 (እ.አ.አ)
ኤልያስ እና አነስተኛ ለስላሳ ድምፅ
ኤልያስ ነብይ ነበር። የእግዚአብሔርን ድምጽ ለመስማት ፈለገ። የእግዚአብሔርን ድምጽ በተሻለ ለመስማት ወደ ተራራ ሄደ።
ሃይለኛ ነፋስ ነበር፡፡ በጣም ሃይለኛ ከመሆኑ የተነሳ አለቶችን ይሰብር ነበር። ነፋሱ ከፍተኛ ድምጽ ነበረው። ነገር ግን ያ የእግዚአብሔር ድምጽ አልነበረም።
ቀጥሎ የመሬት መንቀጥቀጥ ነበር። ምድርም ተንቀጠቀጠ። እሳትም ነበር፡፡ ትልቅ ነበልባል ነበረው። ነገር ግን የመሬት መንቀጥቀጡ እና እሳቱ የእግዚአብሔር ድምጽ አልነበሩም።
ከዚያም ጸጥታ ሆነ። ኤልያስ የእግዚአብሔርን ድምጽ ሰማ። አነስተኛ ለስላሳ ነበር። ነገር ግን ጥርት ያለ ነበር።
መንፈስ ቅዱስን በመስማት የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማት እችላለሁ። እርሱ በትንሽ እና በቀላል መንገዶች ያናግረኛል።
© 2022 by Intellectual Reserve, Inc. መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Friend Message, July 2022.ትርጉም። Amharic። 18298 506