“ብዙዎቹ የኢየሱስ ስሞች፣” ወርሃዊ የ ጓደኛ መልእክት፣ ታህሳስ 2022 (እ.አ.አ)
“ብዙዎቹ የኢየሱስ ስሞች”
ወርሃዊ የ ጓደኛ መልእክት፣ ታህሳስ 2022 (እ.አ.አ)
ብዙዎቹ የኢየሱስ ስሞች
ብዙ ነቢያት ስለኢየሱስ ክርስቶስ አስተምረዋል። እንዴት መኖር እንደምንችል ሊያሳየን እንደሚወለድ ተናግረዋል። ስለእርሱ ለማስተማር ብዙ ስሞችን ተጠቅመዋል።
አንዳንድ ጊዜ በቅዱሳት መጽሃፍት ውስጥ ኢየሱስ አማኑኤልተብሎ ተጠርቷል። የዚያ ስም ትርጉም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” ማለት ነው፡፡
ኢየሱስ መሲሁሲባልም ተጠርቷል፡፡ መሲህ ማለት “የተቀባ“ ማለት ነው ኢየሱስ የሞተልን እንደገና ከእግዚያብሄር ጋር መኖር እንድንችል ነው፡፡
ኢየሱስ አዳኛችንነው። ከሃጢያታችን እና ከሞት ያደድነናል፡፡
ሌላው የኢየሱስ ስም የሰላም ልዑልነው። ስንፈራ ወይም ስንናደድ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ሰላም እንዲሰማን ሊረዳን ይችላል።
ኢየሱስ ክርስቶስን እወደዋለሁ። በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ስለህይወቱ እና ስለፍቅሩ መማር እችላለሁ።
© 2022 በ Intellectual Reserve, Inc. መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። የ ወራዊ የጓደኛ መልዕክት፣ ታህሳስ 2022 (እ.አ.አ)ትርጉም። Amharic። 18318 506