ጓደኛ
ኔፊ ለህዝቡ ፀለየ
መስከረም 2024 (እ.አ.አ)


“ኔፊ ለህዝቡ ፀለየ፣” ጓደኛ፣ መስከረም 2024 (እ.አ.አ)፣ 26–27።

ወርሃዊ የጓደኛ መልዕክት፣ መስከረም 2024 (እ.አ.አ)

ኔፊ ለህዝቡ ፀለየ

ምስል
ነቢዩ ኔፊ

ስዕል በአንድሩ ቦዝሊ

ኔፊ ነቢይ ነበር። እርሱ የተሠየመው የነሐስ ሰሌዳዎችን ባገኘው በኔፊ ሥም ነበር። ለህዝቡ ተጨንቆ ነበር። እግዚአብሔርን መከተል አቁመው ነበር።

ምስል
ኔፊ በአትክልት ሥፍራ ግንብ ላይ እየጸለየ

ኔፊ ወደ አትክልት ሥፍራው ሄደ። በአትክልት ሥፍራው በሚገኘው ግንብ ላይ በመውጣት በዚያ ወደ እግዚአብሔር ፀለየ። ስለህዝቡ ፀለየ።

ምስል
ሕዝቡ ኔፊ ሲፀልይ እየተመለከቱ፤ ኔፊ ሕዝቡን እያስተማረ

አንዳንድ ሠዎች ኔፊን በግንቡ ላይ አዩት። ለመስማት ቆሙ እንዲሁም ሌሎችም እንዲሠሙ ሠበሰቧቸው። ኔፊ ጸሎቱን ሲጨርስ፣ እየተመለከቱ እንደነበረ አስተዋለና እነርሱን ማስተማር ጀመረ።

ምስል
ህዝቡ እየጸለዩ

ኔፊ ህዝቡ ንስሐ እንዲገቡ ጠየቃቸው። አንዳንዶቹ ኔፊ ያስተማራቸውን አልወደዱትም ነበር። ሆኖም ሌሎች ብዙዎች አዳመጡት። ንሥሃ መግባትን መረጡ እንዲሁም መንገዳቸውን ቀየሩ።

የሚቀባ ገፅ

ዶሮ የጫጩቶቿን እንደምትሠበስብ ኢየሱስም ህዝቡን ይሠበስባል

ምስል
Alt text

ሥዕል በአደም ኮፎርድ

ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚመጣ ፍቅር እንዴት ይሰማችኋል?

አትም