“ኔፊ ለህዝቡ ፀለየ፣” ጓደኛ፣ መስከረም 2024 (እ.አ.አ)፣ 26–27።
ወርሃዊ የጓደኛ መልዕክት፣ መስከረም 2024 (እ.አ.አ)
ኔፊ ለህዝቡ ፀለየ
ኔፊ ነቢይ ነበር። እርሱ የተሠየመው የነሐስ ሰሌዳዎችን ባገኘው በኔፊ ሥም ነበር። ለህዝቡ ተጨንቆ ነበር። እግዚአብሔርን መከተል አቁመው ነበር።
ኔፊ ወደ አትክልት ሥፍራው ሄደ። በአትክልት ሥፍራው በሚገኘው ግንብ ላይ በመውጣት በዚያ ወደ እግዚአብሔር ፀለየ። ስለህዝቡ ፀለየ።
አንዳንድ ሠዎች ኔፊን በግንቡ ላይ አዩት። ለመስማት ቆሙ እንዲሁም ሌሎችም እንዲሠሙ ሠበሰቧቸው። ኔፊ ጸሎቱን ሲጨርስ፣ እየተመለከቱ እንደነበረ አስተዋለና እነርሱን ማስተማር ጀመረ።
ኔፊ ህዝቡ ንስሐ እንዲገቡ ጠየቃቸው። አንዳንዶቹ ኔፊ ያስተማራቸውን አልወደዱትም ነበር። ሆኖም ሌሎች ብዙዎች አዳመጡት። ንሥሃ መግባትን መረጡ እንዲሁም መንገዳቸውን ቀየሩ።
© 2024 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Friend Message, September 2024 ትርጉም። Amharic. 19357 506