2022 (እ.አ.አ)
የሚሰቃየዉ አዳኝ
ሚያዝያ 2022 (እ.አ.አ)


“የሚሰቃየው አዳኝ፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ሚያዝያ 2022 (እ.አ.አ)።

ወርሀዊ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ሚያዝያ 2022 (እ.አ.አ)

የሚሰቃየዉ አዳኝ

ኢየሱስ ክርስቶስ ከመምጣቱ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ዓመታት በፊት ኢሳይያስ ለኃጢአታችን የሚሰቃየትበትን አስቀድሞ አይቷል።

የተጠላና የተናቀ

ምስል
የኢየሱስ ክርስቶስ እጆች ታስረው

ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር ሲመጣ፣ አንዳንድ ሰዎች በእርሱ አመኑ፣ ግን አብዛኞቹ አላደረጉም። እርሱን እንኳ ይንቁ ነበር፣ ብዙዎችም ይጠሉት ነበር። በመጨረሻ፣ ሰዎች እሱ እንዲሰቃይ እና እንዲገደል መረጡት። (1 ኔፊ 19፥9ይመልከቱ።)

እርሱ ስቃያችንን ተቀበለ

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ በጌቴሴማኒ ተንበርክኮ

ኢየሱስ ክርስቶስ ሕመማችንን፣ በሽታችንን፣ እና ድክመታችንን ሁሉ በራሱ ላይ ወሰደ። ይህን ያደረገው በእኛ ላይ ምህረት እንዲኖረው እና እንዴት እንደሚረዳን እንዲያውቅ ነው። አልማ 7፥11–13 ይመልከቱ።

እርሱ ስለ መተላለፋችን ቆሰለ

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ

ኢየሱስ ክርስቶስ ለኃጢያቶቻችንን ተሰቃየ። ይህን ያደረገው ንስሐ ስንገባ ይቅር እንድንባል ነው። (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥1119፥15–19 ይመልከቱ።)

እናም በቁስሉ ተፈወስን።

ምስል
ሰዎች ከሞት የተነሳው የኢየሱስ ክርስቶስ እጅ ሲዳስሡ

“ቁስሉ” የእርሱ ቁስሎቹ ናቸው። እነዚህ ደሙን ማፍሰስ እና ሞቱን ጨምሮ ለእኛ በመሰቃየት የጸናበትን ሁሉ የሚወክሉ ናቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ስለተሰቃየ፣ እንደገና ልንድን እንችላለን። የእሱ መስዋዕትነት ኃጢያታችን ይቅር ለመባል እንዲቻልልን አድርጓል። ንስሀ ስንገባ እና ቃል ኪዳኖቻችንን ለመጠበቅ ስንሞክር፣ እርሱ ይፈውሰናል እናም ይለውጠናል። (ሞዛያ 3፥7–11የእምነት አንቀጽ 1፥3 ይመልከቱ።)

አትም