አትዘግዩ! “እንደእረኞቹ ሁኑ፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)
ወርሀዊ የ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ታህሳስ 2022 (እ.አ.አ)
አትዘግዩ! እንደ እረኞቹ ሁኑ
ከረጅም ጊዜ በፊት አንድ ፀጥ ባለ ምሽት እረኞች መንጎቻቸውን በትጋት ይጠብቁ ነበር።
እረኞቹ አንድ ጠቃሚ ስራ ነበራቸው። በጎቹ ምግብ ውሃ እና ከአደጋ ጥበቃ ያስፈልጋቸው ነበር።
በድንገትም አንድ መልአክም ተገለጠ።
“እነሆ፥ ታላቅ ደስታ የምስራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፥ … ዛሬ …መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።”
መልአኩ፣ ህፃኑ በጨርቅ ተጠቅልሎ በቤተልሔም በግርግም ተኝቶ እንደሚያገኙት ለእረኞቹ ነገራቸው።
የመላዕክት ዝማሬ ሰማዩን በመሙላት ከመልአኩ ጋር እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
“ክብር ለእግዚአብሄር በዓርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ።”
“እንግዲህ እስከ ቤተልሔም ድረስ እንሂድ እግዚአብሔር የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ።“
እረኞቹ አልዘገዩም። ይህ በጣም አስፈላጊ ነበር። ወደቤተልሄም “ፈጥነው መጡ።“
ልክ መልአኩ እንዳለው እረኞቹ ኢየሱስ በጨርቅ ተጠቅልሎ በግርግም ተኝቶ አገኙት።
አዳኝ እና የአለም ቤዛ ለመሆን የመጣው እንዲሁም እውነተኛ ደስታን ሊያመጣልን ተስፋ የተጣለበት መሲህ ይህ ነበር!
እረኞቹ በጣም ተደስተው ነበር! ሰምተው እና አይተው የነበሩትን አጋሩ።
“የአለም አዳኝ ተወለደ!“
“በመጨረሻ መሲሑ መጣ!“
እረኞቹ ወደ ኢየሱስ “ፈጥነው መጡ።“ እናንተም ትችላላችሁ!
ከእርሱ መማር ትችላላችሁ።
ሌሎችን በማገልገል እርሱን ማገልገል ትችላላችሁ።
ስለእርሱ መመስከር ትችላላችሁ።
© 2022 በ Intellectual Reserve, Inc. መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። የ ወራዊ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ታህሳስ 2022 (እ.አ.አ)ትርጉም። Amharic። 18318 506