2023 (እ.አ.አ)
ለመንፈስ ቅዱስ ልባችሁን ክፈቱ
ሚያዝያ 2023 (እ.አ.አ)


“ለመንፈስ ቅዱስ ልባችሁን ክፈቱ፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ሚያዚያ 2023 (እ.አ.አ)።

ወርሀዊ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ሚያዝያ 2023 (እ.አ.አ)

ለመንፈስ ቅዱስ ልባችሁን ክፈቱ

በዚህ የፋሲካ ሰሞን ቤዛችን ለመሆን በፈቃዱ ወደ ምድር ለመጣው ለውድ ልጁ ስጦታ የሰማይ አባታችንን አመሰግናለሁ። ለኃጢያቶቻችን ክፍያ ማድረጉን እና በትንሳኤ መነሳቱን በማወቄም አመስጋኝ ነኝ። በየቀኑ፣ በኃጢያት ክፍያው ምክንያት፣ ከምወዳቸው ቤተሰቦቼ ጋር ለመኖር አንድ ቀን ከሞት እንደምነሳ በማወቄ የተባረኩኝ ነኝ።

እነዛን ነገሮች የማውቀው ማንኛችንም እነሱን ማወቅ በምንችለው ብቸኛ መንገድ ነው። መንፈስ ቅዱስ ወደ አዕምሮዬ እና ልቤ እውነት እንደሆኑ—አንዴ ብቻ ሳይሆን ለብዙ ጊዜ—ተናግሯል።

መንፈስ ቅዱስ እንደ ጓደኛችን የሚሆንበት ዋጋ የማይተመንበት ቃል ኪዳን አለን። የእኛ ግዴታ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ቀጣይነት ያለውን መንፈሳዊ ምሪ እና ምቾት ለመቀበል ልባችንን ለመክፈት መምረጥ ነው።

ምስል
አበባ

ምስል በኤምሊ ኢ. ጆንስ

የመጀመሪያው ምርጫ ከእግዚአብሔር ፊት ትሁት መሆን ነው።

ምስል
የሚጸልዩ እጆች

ሁለተኛው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን መጸለይ ነው።

ምስል
ኮምፓስ

ሶስተኛው በትክክል ታዛዥ መሆን ነው።

ምስል
የልብ ቅርጽ

አራተኛውም የሌሎችን ፍላጎቶች እና ልቦች ለማወቅ እና ለጌታ እንዴት እንደምንረዳቸው ለማወቅ መጸለይ ነው።

በደግነት ወደ እናንተ የተላከውን የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ እንድትሰሙ በሙሉ ልቤ እጸልያለው። እናም መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል እና እርሱን ቋሚ ጓደኛ በማድረግ ደስታ ይኖራችሁ ዘንድ ልባችሁን ሁሌም እንድትከፍቱ እጸልያለው።

አትም